Friday 24 January 2020


ቅድስና በእብራይስጥ 'ቅዱስ' በግሪክ ቋንቋ 'ሐጋዮስ' ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ለእግዚአብሔር ክብር እና አገልግሎት የተለየ ማለት ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ አኳያ አንድ ስጋውን፣ መንፈሱን እና ነፍሱን ከሚያረክስ ሃጢአት መበራቅ እና በመነጠል ራሱን ለእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው ዕብ 1214 1ጴጥ 115 2ዜና 29
የቅድስና ምንነት
1.
ቅድስና የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው 1ተሰ 43
2.
ቅድስና የእግዚአብሔር አንዱ ባሕሪው ነው 1 ጴጥ 115 1ሳሙ 22
3.
ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚሆን ነው ዘፀ 2836
4.
ቅድስና ለአንድ ለታወቀ አላማና ግብ ላለው ሕይወት መለየት ነው 2ዜና 295
5.
ቅድስና ከእግዚአብሔር አንድ የመጣና ለተቀዳሹ በረከት የሚሆን ስጦታ ነው
6.
ቅድስና ሶስት መሰረታዊ ትርጉሞች አሉት
. መለየት - ይህም ከሃጢአት፣ ከራስ ምኞት እና ከሰይጣን አሰራር ኢሳ 5211-12
. መሰጠት - ለእግዚአብሔር ብቻ ራስን መስጠት 2ዜና 295
. ንጽህና - ከሃጢአት እና ከሚያረክሱ ነገሮች ንጽህ መሆን ዘፃ 910

የቅድስና ደረጃዎች
1.
የመዳንን ደረጃ የሚያስገኝ ቅድስና 1ቆሮ 611
2.
ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል የተደረገ ፈጣን የመቀደስ (መለየት፣ መሰጠት፣ ንጽህና) ስራ ነው - 1ቆሮ 12 ኤፌ 11 ቆላ 12 ዕብ 1010 ይሁዳ 3
3.
አማኞች ቅዱሳን ተብለው ተጠርተዋል። ምንም እንኳን በስጋ ቢኖሩም ቅድስና አግኝተዋል 1ቆሮ 33 611 2ተሰ 213 ሮሜ 829
4.
የሚያድግ ቅድስና (progressive sanctification)
. በቅድስና ሕይወት ተጠብቆ መኖር ዕብ 1214
. የቅድስናን ፍሬ በማፍራት መኖር መዝ 13218
. ቅድስናን ፍጹም ለማድረግ ራስን ከሚያረክስ ነገር በማንፃት መኖር 2ቆሮ 71
. ዘወትር ራስን ለእግዚአብሔር በመስጠት መኖር ሮሜ 813 1ጴጥ 122
5.
ፍጹም እንከን የሌለበት ቅድስና (complete sanctification)
ይህ አይነቱ ቅድስና የሚገኘው ምድራዊ የሆነውን የሰውነት መኖሪያ ለቀን ሰማያዊ አካል በምንለብስበት ጊዜ ነው 1ዮሐ 32 ዕብ 1223 1ተሰ 313
በቅድስና የማደጊያ መንገዶች፦
1.
የእግዚአብሔር ቃል
. ቃሉን በማጥናት ዮሐ 177-9 ኤፌ 526 ያዕ 121-25
. ቃሉን ከሚያውቁ አገልጋዮች ስር ሆኖ በመማር ኤፌ 411-13 ገላ 66 ዕብ 137 ይኸውም ቃሉን ቀሚያብራራልን ከመንፈስ ቅዱስና የቃሉ እውቀት ካላቸው አገልጋዮች ስር ሆኖ በመማር 1ዮሐ 19
2.
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ዕብ 1312 1ዮሐ 19
3.
የእግዚአብሔር መንፈስ ሮሜ 82-13 ገላ 522 1ቆሮ 611
4.
የእግዚአብሔር አባታዊ ቅጣት ዕብ 129-11
የቅድስና አቅጣጫዎች
1.
በሁለንተና (በስጋ፣ በነፍስ፣ በመንፈስ) 1ተሰ 523
2.
በኑሮ ሁሉ 1ጴጥ 115-16
የቅድስና በረከቶች
1.
እግዚአብሔርን በክብሩ ማየት ዕብ 1214
2.
የተስፋውን በረከት መውረስ ኢያ 35
3.
የድል ሕይወት መኖር ኢያ 710-13
እግዚአብሔር አምላካችን ከአማልክት እና ከማንኛውም ክፉ ነገር ሁሉ የተለየ በመሆኑ፣ ቅዱስ በመሆኑ በእርሱ የእርሱ የተለዩ ሰዎችም ሁሉ ቅዱሳን ይባላሉ። ሰው በክርስቶስ ስራ አምኖ አማኝ ሲሆን ቅዱስ ይሆናል፤ ይባላልም። ከዚህ በሕይወቱ ሁሉ በቅድስና ያድጋል። በክርስቶስ ዳግም መምጣት ቅድስናው ፍጹም ይሆናል።
0

Like



404. That’s an error. 
The requested URL /u/0/se/0/_/+1/fastbutton was not found on this server. That’s all we know. 

Share



     
0
Tags:






እጃችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ" (፪ዜና ፴፥፰)

ከሰንበት //መምሪያ ድረ ገጽ የተገኘ
ከዶ/ አምሳሉ ተፈራ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፊሎሎጂ ዲፓርትመንት
ረዳት ፕሮፊሰር
ለሁሉ ፈጣሪ ለእግዚአብሔር ራስን መቀደስና ከኃጢአት መለየት ለሰው ሁሉ የቀረበ ጥሪ ነው። ይህን ዘንግተው የነበሩ ሕዝበ እስራኤል ወደ አምላካቸው እንዲመለሱና ሁለንተናቸውን ለእርሱ እንዲሰጡ የተላከላቸው መልእክት ነው ርእሳችን እኛንም ይመለከታልና እንደሚከተለው በዝርዝር እንየው።
የሚታየውንም የማይታየውንም የፈጠረ፣ በባሕርም በየብስም ያሉትን ያስገኘ፣ ሰውን ለክብሩ ወራሽነትና ለስሙ ቀዳሽነት የወሰነ፣ ዓለምን ሲፈጥር አማካሪ ያልፈለገ፣ ፍጡሩን በመመገብና በመውደድ ወደር የሌለው፣ ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ የሰጠ ነው ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር። ይህን ጌታ በምንም ልንለውጠውና ልንተካው አንችልም። አምላክ ነውና ተወዳዳሪ የለውም (ኢሳ፵፣ ፲፪ - ፲፬)
የርእሳችን መነሻ የሆነው «እጃችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ» የሚለው ትምህርት የተሰጠው፣ ሃያ ዘጠኝ ዓመታት በእስራኤል ላይ በነገሠው ንጉሥ ሕዝቅያስ ነው። ምክንያቱ ደግሞ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማድረግ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትን ይመለከታል። እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ስለሆነ፤ ወደ እርሱ መቅረብና ማገልገል የሚቻለው በንጽሕና ሆኖ ነው፤ አገልግሎትንም የሚቀበለው ያለቸልታ በትጋት ሲሆን ነው። «ልጆቼ ሆይ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ፤ ብሎ ያዘዘን ለዚህ ነው (፪ዜና፳፱፣፲፩)
«ንጉሡ ሕዝቅያስ ለእግዚአብሔር ፋሲካ እንዲደረግ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ለዐሥራ ሁለቱም ነገደ እስራኤል መልእክት ላከ። ነገር ግን ካህናቱ ገና በሚገባ ስላልተቀደሱ፣ ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ተጠቃለው ስላልተሰበሰቡ፤ ፋሲካው በደንብ ሲዘጋጁ በቀጣዩ ወር እንዲከበር ተወሰነ። ለቀጣዩ ወር ግን ሁሉም ከያለበት ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እንዲሰባሰብ እንዲህ የሚል ዐዋጅ ተነገረ፣ «የእስራኤል ልጆች ሆይ ... እግዚአብሔርን እንደ በደሉ እንደ አባቶቻችሁና እንደ ወንድሞቻችሁ አትሁኑ። አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ለዘላለም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፤ ጽኑ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ። (፪ዜና ፴፣፯-)
እስራኤላውያን ከያሉበት ተሰባስበው በኢየሩሳሌም እንዲያከብሯቸው ከታዘዙት አንዱና ዋናው በዓል የፋሲካ ወይም የቂጣ ነው። በእግዚአብሔር ቸርነት ከግብጽ ባርነት የወጡበትን ሁኔታ ይዘክሩበታል። ይህም በኒሳን ፲፬ ቀን (በእኛ ሚያዚያ ወርየሚከበር ሲሆን፤ በዓሉም ለሰባት ቀናት ይዘልቃል። ለዚህ ነው ይህን ታላቅ በዓል ሲያከብሩ በተለየ መልኩ ራሳቸውን መቀደስና እጃቸውንም ለፈጣሪ መስጠት የሚጠበቅባቸው። ይህ ታሪክ ለእኛ ምን ያስተምረናልይህንንም እንደሚከተለው እንመልከት፤
ለመሆኑ እጅን መስጠት ምንን ያሳያልእጅን መስጠት መማረክን፣ መሸነፍንና በሌላ ነገር አለመወሰድን ወዘተ... ያመለክታል። ሁኔታው ሁለንተናን እና አጠቃላይ ማንነትንም ይመለከታል። እጅን መስጠት የሰላምም ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። ለእግዚአብሔር እጅን መስጠት ለምን ሲባልምሰው እጁን ከሰጠ ሐሳቡም፣ ተግባሩም፣ እንቅስቃሴውም ወዘተ... ወደዚያው ነው የሚጠቃለለው። የፈጠረን፣ የሚያኖረን፣ የሚያዝንልን ሁሉ እርሱ ነውና እኛም ሲቸግረን ለማግኘት፣ ሲጎድለን እንዲሞላልን፣ ስንወድቅ እንዲያነሣን እጃችንን በመስጠት ወደ እግዚአብሔር እንጮኻለን።  «ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል፤ እጅን ለእግዚአብሔር የመስጠት ምልክቶችን ቀጥሎ እንመለከታለን። ቀዳሚው ራስን መቀደስና ከኃጢአት መጠበቅ ነው። ያኔ ሕዝቅያስ ለእስራኤላውያኑ ያወጀላቸው ካህናቱ ራሳቸውን በሚገባ እንዲቀድሱ፣ ሕዝቡም ከኃጢአት ተጠብቀው ፋሲካውን በንጽሕና እንዲያከብሩ ነው። የእግዚአብሔርን ፋሲካ ከኃጢአት ሳይነጹ ማክበር አይገባምና ለዚህ ቀን ተሰጥቷቸዋል። በዚያም መሠረት ሁሉም እንደሚገባ ተከናውኗል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ሁሉም እጅግ ተቀድሰው ነበርና የፋሲካው በዓል ለተጨማሪ ሰባት ቀናት በደስታ ተከበረ፤ ይህም ከሰሎሞን ዘመን ወዲህ የመጀመሪያው በዓል እንደሆነ ተመዝግቧል፤ (፪ዜና፴፣፳፬-፳፮) ዛሬም ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ሁሉ የሚወደድልን አብዝተን ስንቀደስና እጃችንን ለእርሱ ብቻ ስንሰጥ ነው። በዓላትን ስናከብር፣ ወደ ቅዱሳት መካናት ስንጓዝ፣ ለመንፈሳዊ ሥራ ስንሰማራ ወዘተ... ምን ያህል መንፈሳዊ ዝግጅት እናደርጋለንለወረት ያህል ጀምረን የተውናቸው ስንቶች ናቸውበመንፈስ ጀምረን በሥጋ የምንቋጫቸው ምን ያህል ይሆኑአንዴ መንፈሳዊ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሥጋዊ መሆን የሚያምረን ስንቶቻችን ነንበአንዱ እጃችን እግዚአብሔርን በሌላኛው ደግሞ ዓለምን የምንጨብጥ ከሆነ አንዱም አይሳካም። ስለዚህ ለፈጣሪያችን እኛነታችንን በመላ ነው ማስረከብ ያለብን። ከእርሱ ቀንሰን ለባእድ የምንሰጠው በፍጹም ሊኖር አይገባም።

ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችንን በተለይም ወጣቶችን እየተፈታተነን ያለው የምንቆምበትን ቦታ አለማወቅ ነው። ሁሉም ነገር ያምረናል። ባየነው ነገር ሁሉ እንማረክና በቀላሉ እጃችንን እንሰጣለን። ይህ ዓለም የውጊያ ዐውድ ነው። በቀረበልን ሁሉ የምንማረክና እጅ የምንሰጥ ከሆነ ግን ዓላማችንን ስተናል። ጌታችን የዓለምን ፈተና ድል ያደረገልን እኛም በአሸናፊነት መንገድ እንድንጓዝ ሲያጠይቀን ነው (ዮሐ፲፮፣ ፴፫) ስለዚህ ለሕይወት ፈተና እጅ እንዳንሰጥ፤ ለዓላማቢስነት እጅ እንዳንሰጥ፤ ለዝሙትና ርኩሰት እጅ እንዳንሰጥ፤ ለስሜታዊነት እጅ እንዳንሰጥ ወዘተ... መወሰን አለብን። እጅ መስጠት ለአምላክችን ለእርሱ ብቻ ይሁን።
ሁለተኛው ለአምላካችን እጅ የመስጠታችን ዐቢይ መገለጫ የእርሱን ፈቃድ ብቻ ስናደርግ ነው። በሕይወት ጉዞአችን ውስጥ ለሥጋዊ ፈቃድ ስኬት ብቻ ከሮጥን ትርፉ ድካም ብቻ ነው። የራስ ፈቃድ፣ የቤተሰብ ፍላጎት፣ የአለቃ ትእዛዝ፣ የባሕላችን ተጽእኖ፣ የአካባቢያችን ሁኔታ ወዘተ ... ዓይነቱና ኅብሩ ብዙ ነው። ይህን ሁሉ እናሟላለን ብለን ብንሞክርም ዓለም አትሞላምና /በዚያውም ላይ ዕድሜ ካልቀደመንበፍጹም አይሳካልንም። ስለዚህ ውጤቱ በኑሮ አለመርካት፣ ብጥብጥ፣ ተስፋ መቁረጥና የመሰለው ነው። ያንዱን ፈቃድ ትተን ሌላውን እንፈጽም ብንልም ውጤቱ አጉል ይሆናል። ነገር ግን የደጉ አምላካችንን ፈቃድ ብንከተል ለቀሪው ችግራችንና ምስቅልቅል ሕይወታችን መፍትሔ ነው። አንዱን የእግዚአብሔር ፈቃድ ስንፈጽም ሌላውን ያቃናልናል። በጀመርነው ጥቂት ነገር ብዙ በረከት ይሰጠናል። ይህን እውነት ሲመሰክር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል፤ «የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ይልቁንም ወጣቶች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ልባችንን ሰበር ማደረግ ይገባናል። የእርሱ ፈቃድ ሁል ጊዜ በጎና መልካም ነው። ፈቃዱን እንዴት ልወቀውብንል ዳዊት ምላሹን ይሰጠናል።
(መዝ፳፣፬፤ ፵፣፰፤ ፻፵፫፣፲እንመልከት።
ሦስተኛው መንገድ ወደ ቤቱ መምጣት ነው። የሚቀርቡልን ብዙ አማራጮች ጊዜያዊ ደስታን ብቻ የሚሰጡ ናቸውና አብረው አይዘልቁም። እንዲያውም ጸጸትና ቁጭት ያስከትላሉ። በእግዚአብሔር ቤት በቤተ ክርስቲያን መተከል ግን ድርብርብ መልካም ፍሬን ያስገኛል። ሰላም፣ ደግነት፣ ርኅራኄና ይቅርታ ወዘተ... ከቤተ እግዚአብሔር እንጂ ከዓለማዊ ቦታ (ማለትም መጠጥ ቤት፣ ዝሙት ቤት፣ ጥንቆላ ቤት፣ ወዘተ ) አይደለም። በኃጢአት ብንወድቅ በንስሐ፥ ራስን በመውደድ ብንሰቃይ ስለ ሌላው በማሰብ፥ በስርቆት ብንገኝ የራስንም መስጠትን ወዘተ... የምንማርባት ናት ቤተ ክርስቲያን። ስለዚህ በዓለም ካሉ መጠጊያዎች አብልጠን ራሳችንን የምናስጠጋባትና ለእሷም ብቻ እጃችንን ልንሰጥ የሚገባ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት። ክቡር ዳዊት «ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወዳለች፣ ትናፍቅማለች... ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች። በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ በማለት በቤተ እግዚአብሔር መኖር ያለውን ጠቀሜታ ያሳያል (መዝ፹፫፣ -)
ሌላው መመለስ ያለበት ጥያቄ እጃችንን ለእግዚአብሔር መስጠት ምን ምን ያስገኛልየሚለው ነው። አንድ ነገር ጥቅም ካልሰጠ መከወኑ ፋይዳ ቢስ ነው። ከዚህ አንጻር የተነሣንበትን ርእስ ስናየው፤ ምላሹንም እዚያው ምዕራፍ ላይ በቀጣዩ ቁጥር እናገኛዋለን። እንዲህ ይላል «አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነውና፥ ወደ እርሱም ብትመለሱ ፊቱን ከእናንተ አያዞርም። ... ልጆቻችሁ ... ምሕረትን ያገኛሉ። ደግሞም ወደዚህች ምድር ይመለሳሉ።» (፪ዜና፴፣፱) እጃችንን ለፈጣሪያችን ከሰጠንና መንገዳችን ከመንገዱ አንድ ከሆነ እርሱ በምሕረት ዐይኑ ይመለከተናል፤ በረከቱም ለልጅ ልጆቻችን ይተርፋል። የምንጓጓለት ሁሉ የሚሰጠን ቅድሚያ ራሳችንን ለእርሱ ስንሰጥ ነው። በፊቱ ሞገስ የምናገኘው ወለም ዘለም ሳንል ስናመልከው ነው። ወደርስት ቦታችን መንግሥተ ሰማያት የሚመልሰን፤ እንዲሁም የምንናፍቀውን ሕይወት የሚሰጠን በሐሳብም በተግባርም ለእግዚአብሔር ብቻ ስንገዛ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችንን ብቻ በማምለክና ለእርሱም እጃችንን በመስጠት ሕይወታችንን እንምራ። ወደእርሱ ከተጠጋን ፈጽሞ አይጥለንም። በነቢዩ አድሮ እንዲህ ብሎናልና፤ «አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።(ኢሳይያስ ፵፩፣ ) ለእርሱ ብቻ ታምነን እጃችንን እንድንሰጥ እርሱ ይርዳን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!
 ከሰንበት //መምሪያ ድረ ገጽ የተገኘ

ፌስቡክ ላይቭ እስትሪሚንግhttps://www.youtube.com/watch?v=rapsYGqHsUA ፌስቡክ ላይቭ እስትሪሚንግ How to Live Stream on Facebook from your Desktop with OBS (open broadcaster software) - #owenvideo




https://youtu.be/OtJHX7O3p5U  How To Live Stream On YouTube With OBS | Fast Start Guide


How to Livestream PC on Facebook & Best Settings for OBS
https://youtu.be/qHodUCgvtfo important not live streaming in ops with facebook 

How to Live Stream on Facebook using OBS (Open Broadcast Software) From Your Computer



How to Live Stream on Facebook from your Desktop with OBS (Open Broadcast Software)

How to Green Screen with OBS! Easy & Free!
91,970 views•Sep 17, 2016 



https://youtu.be/3MufrAuDdvk For new commerces streaming 

Zoom Virtual Background Facebook Live OBS with a Green Screen Chromakey

How To Use a Green Screen With Live Video / Zoom | The XayLi Show

How To Setup A Green Screen with OBS Tutorial | Chroma Key Effects Settings | Equipment & Gear Guide

Facebook Live With OBS Studio
https://youtu.be/M3R9YUlQ7QM important Point to inter FB live

How to Stream to Facebook Live Using OBS Studio

How to do a Skype Interview and Stream it Live Using OBS Studio

OBS and Green Screen
https://youtu.be/b_3Ldk0enSU  ግሪን እስክሪን ለመቀየር
የጥቅምት ገድለ አቡነ አረጋዊ
https://youtu.be/lXRIhUa9qY4 የጥቅምት ገድለ አቡነ አረጋዊ

የጥቅምት ገድለ አቡነ አረጋዊ
https://youtu.be/lXRIhUa9qY4 የጥቅምት ገድለ አቡነ አረጋዊ

https://youtu.be/m-7SN0Pzfhw ክብረ ቅዱሳን - ገድለ አቡነ አረጋዊ


"ጌታችን በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ቃል ኪዳን ሰጠው ዳግመኛም ጸሎትህ እነሆ በኔ ዘንድ ደርሶ ተሰምቷል።
ስለዚህም ከድካም ወደዕረፍት ከኀዘን ደስታ ወዳለበት ከኃሣር ወደክብር በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደአንተ መጥቻለሁ አለው።
የዚህን የሀላፊውን ዓለም ክብር ስለናቅህ በመንግስተ ሰማያት የማያልፈውን የማይጠፋውን ክብር አቀዳጅሃለሁ።
በዚህ ዓለም የሐሩን ልብስ የወርቅና የብሩን ጌጥ እንደናቅህ እኔ አይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን አለብስሃለሁ አስጌጥሃለሁ።
ከትውልድ ሀገርህ ወጥተህ በባዕድ አገር ስለኖርክ እኔ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን እሰጥሃለሁ የሚያልፉ የሚፈርሱ የዚህን ዓለም ቤት ንብረት ስለናቅህ የማይፈርስ የማያልፍ የሕይወት ቤት እኔ እሰጥሃለሁ።
መታሰቢያህን ያደረገ በጸሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላእክት ፊት ሞገስን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ።
በእውነተኛ ሃይማኖት ሁኖ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ ያጻፈ የተረጎመ እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ።
መታሰቢያህ በሚደረግበት ዕለት የራበውን ያጠገበ የጠማውን ያጠጣ እኔ የሕይወት እንጀራ አበላዋለሁ የሕይወት ጽዋም አጠጣዋለሁ።
በዓልህ በሚከበርበት ዕለት ለራበው ምሳውን ያበላ እኔ በምሳሐ ደብረ ጽዮን የምሳ ግብዣ አደርግለታለሁ።
በስምህ በተሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ የጸለየ የለመነ ፈጥኜ ጸሎቱን እሰማዋለሁ ልመናውንም እቀበለዋለሁ ቤተ ክርስቲያንህንም ለሠራ ዐሥራ ሁለት የብርሃን አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ።
የገድልህን መጽሐፍ በመታመን በንጽሕና አድርጎ በቤቱ ያስቀመጠ ወረርሽኝ በሽታ ወይም ቸነፈር በቤቱ አይገባም ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም የእህል ችግርም አይኖርበትም።
በጥቡዕ ልብ ሆኖ የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ያለስንፍና በፍጹም መታመን የንባቡን ኃይለ ቃል የሰማ እኔ ለችግሩ ሁሉ ፈጥኜ እደርስለታለሁ።
ለቤተ ክርስቲያንህ መባ ያገባ ዕጣን ወይም ቅብዓ ሜሮን ወይም ዘይት የሰጠ እኔ በሰማያዊት መንግሥቴ አስገባዋለሁ።
ንጉሥም ቢሆን ለቤተ ክርስቲያንህ የሐር መጎናጸፊያ ቢሰጥ በዓልህ በሚከበርበት ዕለት ቢያከብር እኔ በመንግሥቴ አከብረዋለሁ በጠላቱም ላይ ድልን አቀዳጀዋለሁ ከመኳንንቱ ከመሳፍንቱ ጋር ሰላምን እሰጠዋለሁ በምድርም ላይ ዘመኑን ወይም ዕድሜውን አረዝምለታለሁ።
ከሁሉም ይልቅ የሞት ጥላ አያርፍብህም መልአከ ሞትም ሊያስደነግፅህ አይችልም እንደ ነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሠወራለህ እንጂ።
በቡሩካን እጆችህ የቀበርካት እናትህ ዕድናንም በትንሣኤ ሕይወት እስካስነሣት ድረስ መቃብሯን አፍርሶ ሌላ ሰው እንዳይቀበርበት ወይም ለማንም እንዳይታይ እንደ እንበረም ልጅ እንደሙሴ መቃብር ይሰወራል።
ይህቺን ቤተ መቅደስህንም ታላቅና የተከበረች አደርጋታለሁ የበቁ የደጋግ ነገሥታትና ጳጳሳት የመቃብራቸው ወይም የማረፊያቸው ቦታ ትሆናለች።
ጌታችንም ይህን ቃል ኪዳን በሰጠው ጊዜ ክቡር አባታችን አቡነ አረጋዊ ጌታችንን አቤቱ በፊትህ ሞገስ አግኝቼስ ከሆነ እናገር ዘንድ ይፈቀድልኝ አለው።
ጌታም ወዳጄ አረጋዊ ሆይ ፈቅጄልሃለሁ ተናገር ከኔ የምትፈልገውንም ሁሉ ጠይቅ ወይም ለምን አለው።
ከዚያም አባታችን አቡነ አረጋዊ ይህን ሁሉ ለሰጠኸኝ እስከ ዘላለሙ ድረስ ስምህ የተመሰገነ የጌትነትህም ክብር የተባረከ ነው ብሎ አመሰገነ።
አሁንም ጌታ ሆይ መታሰቢያየን ያደረገ የገድሌን መጽሐፍ የጻፈ በጸሎቴ የተማመነ እስከ ስንት ትውልድ ድረስ ትምርልኛለህ አለው።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም አቤቱ ይህች ቦታ የነገሥታት የጳጳሳት የክቡራን መኳንንትና መሳፍንት ብቻ መቀበሪያ ሁና አትቅር ነገር ግን ለተገፉ ለነዳያን አባት እናት ለሞቱባቸው ለዕውራንና ለሐንካሳን መጠጊያ ትሆን ዘንድ ማንኛውም ግለሰብ ይቀበርባት እንጂ እኔ በዚች አገር እንግዳና ስደተኛ ነኝና አለው።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የተመሰገንህ አረጋዊ እንደ ቃልህ ይደረግልህ አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አቤቱ ከሩቅ ወይም ከቅርብ መጥተው ንስሐ ሳይገቡና በድንገተኛ ሞተው በዚች በአፀደ ቤተ ክርስቲያኔ የተቀበሩትን ሁሉ ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው አለ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳንስ በተራራው ጫፍ ላይ የተቀበረ ይቅርና ከተራራው ሥር እንኳ ቢሆን ይልቁንም በስምህ የተሰየመ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ በዚያ የተቀበረው ኃጢአቱ ይሠረይለታል እነዚህንም ሁሉ ዓሥራት አድርጌ ሰጠሁህ አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም አቤቱ ይህችን ቤተ መቅደስና በውስጡዋም የሚኖሩትን ባርክ አለው።
መድኃኒታችንም ይህች ቤተ መቅደስህ የተባረከች የተቀደሰች ትሁን በውስጧም ሰው አይታጣ መብራቷ አይጥፋ ሥጋዬና ደሜ በውስጧ በተዘጋጀ ጊዜ ልምላሜ ሙቀት ያልተለየው የሠመረ በፊቴም ተቀባይነት ያለው ይሁን አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም መልሶ አቤቱ ይህችን መንፈሳዊ ማኅበር ልጆቼንና ቅዱሳኖቼንም ሁሉ ባርክ አለው።
ይህች ማኅበር የተባረከች ትሁን የችግረኞች መጠጊያ የተራቡ የሚጠግቡባት የታረዙ የሚለብሱባት ወይም ለተራቡት ምግብ ለተራቆቱት ልብስ ትሁን አለው።
እሊህ ቅዱሳን ልጆችህም እልፍ አእላፋት ይሁኑ እንደባህር አሸዋ እንደሰማይ ከዋክብትም ትውልዱ ነገዱ እንደተስፋፋ ዘሩም እንደበዛ እንደ ያዕቆብ ልጆች የበዙ ይሁኑ።
ድንገተኛ በሽታ መቅሠፍት ሰውነትን የሚያዝግ የሚያጠወልግ ሕማም ወደነሱ አይቀርብም።
አባታችን አቡነ አረጋዊ አቤቱ ይህችን የማድርባትን በዓቴንና ከአንተም ጋር ቆሜ ቃል ኪዳን የተቀበልኩባትን ቦታ ባርክ።
ይልቁንም ይህቺ እግርህ ከቆመባት መሬት አፈሯን ወስደው በመቀባት መድኃኒት ትሆናቸውና ወይም ከሕመማቸው ይፈወሱ ዘንድ ባርካት አክብራትም።
ሕመም ያለበት ቢኖር ፈጥኖ ይወገድለት በፍጹም መታመን በአንገቱ ላይ እምነቱን ቢአሥር ከክፉ ደዌ ከሚያንቀጠቅጥ ወይም ከሚያንዘፈዝፍ በሽታ ይድን ዘንድ መሬቱን ወይም እምነቱን በተቀባ ጊዜ በሱ ላይ ድንቅ ድንቅ ተአምር ተፈጽሞ ከሕመሙ ነፃ ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን በማለት አባታችን አቡነ አረጋዊ ለመነ።
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይሁን ይደረግልህ በማለት በማይታበል ቃሉ ቃል ኪዳን ገባለት።"
+++አሜን+++
ምንጭ፦
ገድለ አቡነ አረጋዊ፤ ዘሰኔ፤ ምዕራፍ 2 ከቁጥር 1 – 36 1978 .




ጻድቁ አቡነ አረጋዊ




እኚህ አባት ከተሰሐቱ ቅዱሳን (ከሮምና ኤሽያ ከመጡት 9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበር፡፡ እናታቸው ንገሰተ እደና ትባላለች፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳዊ ሲማሩ አድገው ወደ እሰከነድረያ ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውነ አውቀው መዓርገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡
ንጉስ የሆኑ ቤታቸው የሞቀ ቤተ ሰቦቻቸውነ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አበምኔቱም ወደዚህች የሕየወት መንገድ ስለመራሀን ብፁህ አረጋዊ መባል ይገባሃልብለዋቸዋል፡፡ አረጋዊ የተባሉት ከዚያ ወዲህ ነው፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ መዐረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል። በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ ሲያስተምሩየሀገራችንን ዜና ሰምተው ለመምጣት 480 . ከአባ ፍሪሚናጦስ | መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በክነፉ ተሸክሞ አክሱ አድርሷቸዋል፡፡ ተመልሶ ሄደው ስለ ኢትዮጵያ ቅድስት ሀገር መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበውመነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱ ሁሉ ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም 480 . ወደ ኢትዮጵያ ራሳቸውን ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡ አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀመዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረመንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሱ፡፡ ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/9111-16 ላይበመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡
ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላች ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላ ግን ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡ ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል፡፡

በረከታቸው፣ ቃልኪዳናቸው፣ አማላጅነታቸው በሁላችን ይደር አሜን።

Copy and paste one of these options to share this book elsewhere.
Link to this page view:
http://digitalscholarship.utsc.utoronto.ca/islandora/object/gundagunde%3A6822
Link to the book:


No comments:

Post a Comment