Wednesday 29 January 2020

በገድለ አቡነ አረጋዊ ዙርያ ለኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችም ሆነ አገልጋይ ካህናት የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት IN...ለኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችም ሆነ አገልጋይ ካህናት የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት  በገድለ አቡነ አረጋዊ ዙርያ ለኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችም ሆነ አገልጋይ ካህናት የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት ሁሉም ሰው ቢማረው ይጠቀማል - አቡነ አረጋዊ ማናቸው ? - ትውልዳቸው - የነገሥታት ልጅ መሆናቸው - የቀድሞ ስማቸው - አረጋዊ ተብለው የተጠሩበት ምክንያት የማስተምራቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው 1ኛ ) በምናኔ ሕይወቱ የራሱን ጽድቅ በማቆሙ ምክንያት ለእናቱ ሰላምታ የነፈጋት አቡነ አረጋዊ 2ኛ ) መጽሐፍቅዱሳችን ሀ ) ለአባትና ለእናት የሚሰጠው ቦታ ለ) ለቤተሰብ የሚሰጠው ቦታ ሐ ) ለልጆች የሚሰጠው ቦታ መ) ለጋብቻ የሚሰጠው ቦታ 3ኛ ) ሰዎችን መማረክ ያለብን ለምናኔ ወይንም ወደ ምናኔ ሳይሆን ለክርስቶስና ወደ ክርስቶስ ነው 4ኛ ) የተላከ የት ልሂድ አይልም ተጭኖ ሊወሰድ የተላክለት የመልአክ ክንፍም አላየንም 5ኛ ) ለብዙ ጊዜ የሆነ የአቡነ አረጋዊ በዓት ወይንም መቀመጫን የመፈለግ ድካም 6ኛ ) አቡነ አረጋዊን ቀጥ ወዳለው ተራራ ሊያወጣ የታዘዘው የዘንዶው ምስጢር 7ኛ ) ሰማያዊ ኅብስትም ሆነ ሰማያዊ መና በታዘዘ ዘንዶ ወደ ተራራ ለወጡ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተልከው ለወጡ የሚላክ ነው 8ኛ ) አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮጵያ ( በኢትዮጵያ የመነኮሳት አባታቸው ) አቡነ አረጋዊ የተባለበት ጉዳይ 9ኛ ) አቡነ አረጋዊ አወርስሃለሁ የተባለውና የተሰጠው ኪዳን ሰማያዊውን ሀገር ከናፈቁት የእምነት አባቶች እምነትና የእምነት አቋም ጋር የፈጠረው ግጭት የተወደዳችሁ ወገኖች እነዚህ ትምህርቶች ተዘጋጅተው የሚለቀቁት በዩቲዩብ አድራሻዬ ሲሆን በፌስቡክና በሌሎች አድራሻዎቼም ላይ ፖስት ይደረጋሉ ስለዚህ ውድ የዚህ ትምህርት ተከታታይ ወገኖቼ በሙሉ ይህ ትምህርት ሁላችሁንም የሚመለከት ስለሆነ ብትከታተሉት ብዙ እውቀት ታገኙበታላችሁ ከዚህ በተጨማሪ ለኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ደግሞ በይበልጥ የሚጠቅም በመሆኑ ለእነርሱም ይህንን ትምህርት ሼር ብታደርጉአቸው ብዙዎቹ ወደ ጌታ ማዳን እንዲመጡ እድሉን ታመቻቹላቸዋላችሁ ስለዚህ ትምህርቱን ሼርና ሰብስክራይብ ማድረጉን እንዳትረሱ ላሳስባችሁ እወዳለሁ አዘጋጅቼ ያቀረብኩላችሁ ወንድማችሁ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ጌታ ይባርካችሁ

No comments:

Post a Comment