Friday 24 January 2020





666 ኢሊሚናቲ የአዲሱ የአለም መንግስት ምልክቶች, Usa, Southern Highlands, Papua New Guinea. 9K likes. News Personality.

People also search for














Web results



666 ኢሊሚናቲ የአዲሱ የአለም መንግስት ምልክቶች, Usa, Southern Highlands, Papua New Guinea. 9K likes. News Personality.




Nov 8, 2018 - መጠቀም የሌለብን እና ድብቅ ትርጉማቸውን ማወቅ ያለብን ምልክቶች.




Oct 30, 2018 - ... ሳያውቁ የሚጠቀሙባቸው አስደንጋጭ 666 ምልክቶች BqzBzwaANHo ... ሳናውቀው በእለት ተዕለት ኑሯችን የምንሰራቸው ስህተቶች የአውሬው 666 ተግባራት:: ...




በራእይ መጽሐፍ ላይ የተጠቀሰው አውሬ 666 የሚል ቁጥር የተሰጠው ለምንድን ነው? ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመመርመር 666 የአውሬው ምልክት ምን እንደሚያመለክቱ ማወቅ ...
You've visited this page 3 times. Last visit: 31/08/19




Sep 16, 2017 - Watch ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ሳያውቁ የሚጠቀሙባቸው አስደንጋጭ 666 ምልክቶች - video dailymotion - Rasdashen Tube on dailymotion.



የመደመር ምልክት፡ ደምሮ መቀንስ አሪትሜት። የመቀነስ ምልክት፡ ቀንሶ መደምር ወይም መደመርና መቀነስ የማባዛት ምልክት፤ የማካፈል ምልክት። የእኩሌታ ምልክት፡ የቅንፍ ...



Dec 8, 2016 -  ዜና ምናልባት ለሁላችንም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው። መቶ በመቶ የተረጋገጠ እኛ የመጨረሻው ዘመን ኗሪዎች ነን። ብዙ ምልክቶች በዓለማችን ላይ የጌታ ...



Ethiopia- የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ያለው 666 (ኢሉሚናቲ) ምልክት እና 666 ምልክቶች. Watch on YouTube · Show annotations. Download as: 720p - video/mp4, 360p ...
Ads
  1. 666 Number | Search & Find Quick Results‎
  2. Adwww.info.com/666+Number‎

    Search multiple engines for 666 Number.
  3. Are You A Starseed? | Seeing 11:11, 222, 333?‎
  4. Adwww.starseedsunited.com/‎

    It's Time To Wake Up To Who You Really Are And Why You Are Here.


Searches related to 666 ምልክቶች

Page navigation



666 ትርጉም ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
የመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻ መጽሐፍ እንደሚጠቁመው ይህ ቁጥር፣ ከባሕር የወጣው እንዲሁም አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ያሉት አውሬ ቁጥር ወይም ስም ነው። (ራእይ 13:1, 17, 18) አውሬውበነገድ፣ በሕዝብ፣ በቋንቋና በብሔር ሁሉ ላይሥልጣን የተሰጠውን በዓለም ላይ ያለውን አጠቃላይ የፖለቲካ ሥርዓት የሚወክል ነው። (ራእይ 13:7) አውሬው 666 የተባለ ቁጥር የተሰጠው መሆኑ ደግሞ አውሬውን የሚወክለው የፖለቲካ ሥርዓት በአምላክ ዓይን ሲታይ በከፍተኛ ሁኔታ እንከን ያለበት መሆኑን ያመለክታል። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?
ቁጥሩ መጠሪያ ብቻ አይደለም። አምላክ የሚሰጣቸው ስሞች ከመጠሪያነት ባለፈ ትርጉም ያላቸው ናቸው። ለምሳሌ አምላክ፣ የአብራም ስም (“አባት ተከበረማለት ነው) ተቀይሮ አብርሃም (“የብዙ ሕዝቦች አባትማለት ነው) ተብሎ እንዲጠራ አድርጓል፤ አምላክ ይህን ስም የሰጠው አብርሃምንየብዙ ሕዝቦች አባትእንደሚያደርገው ቃል በገባለት ወቅት ነው። (ዘፍጥረት 17:5) በተመሳሳይም አምላክ ለአውሬው ያወጣው 666 የሚለው ስም አውሬው ምን ባሕርይ እንዳለው የሚያመለክት መግለጫ ነው።
ስድስት ቁጥር እንከንን ያመለክታል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ቁጥሮች አብዛኛውን ጊዜ ምሳሌያዊ ትርጉም አላቸው ሰባት ቁጥር አንድ ነገር የተሟላ ወይም ፍጹም መሆኑን ያመለክታል። ስድስት ደግሞ ከሰባት በአንድ ስለሚያንስ አንድ ነገር በአምላክ ዓይን ሲታይ ጉድለት ወይም እንከን እንዳለበት ይጠቁማል፤ ቁጥሩ ከአምላክ ጠላቶች ጋር ተያይዞ የተሠራበት ወቅትም አለ።1 ዜና መዋዕል 20:6 ዳንኤል 3:1
ሦስት ጊዜ መደጋገም አንድን ነገር ለማጉላት ይሠራበታል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድን ነገር ለማጉላት ሐሳቡ ሦስት ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰባቸው ጊዜያት አሉ። (ራእይ 4:8 8:13) በመሆኑም 666 በሚለው ቁጥር ላይ ስድስት ቁጥር ሦስት ጊዜ መደጋገሙ የሰዎች አገዛዝ በአምላክ ዓይን ሲታይ ከፍተኛ እንከን እንዳለበት የሚያጎላ ነው። እነዚህ ሰብዓዊ መንግሥታት ለሰው ልጆች ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲሁም ደኅንነት ማምጣት አልቻሉም፤ እነዚህ ነገሮች ሊያስገኝ የሚችለው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው።
የአውሬው ምልክት
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው ሰዎችየአውሬውን ምልክትይቀበላሉ፤ ይህም ሰዎች ለአውሬው አምልኮ እስከ ማቅረብ ድረስበአድናቆት እንደሚከተሉትየሚያሳይ ነው። (ራእይ 13:3, 4 16:2) ይህን የሚያደርጉት ለአገራቸው፣ ለአገራቸው ባንዲራ ወይም አርማ እንዲሁም ለወታደራዊ ኃይሉ የአምልኮ ያህል ክብር በመስጠት ነው።  ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ ሪሊጅን በዘመናችን ብሔራዊ ስሜት ራሱን የቻለ ዋና ሃይማኖት ሆኗልብሏል።

*
ታዲያ ሰዎች የአውሬውን ምልክት በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ላይ የሚያደርጉት እንዴት ነው? (ራእይ 13:16) አምላክ ለእስራኤላውያን የሰጣቸውን ሕግጋት በተመለከተበእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፣ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑብሏቸው ነበር። (ዘዳግም 11:18) ይህም ሲባል እስራኤላውያን ቃል በቃል በእጆቻቸውና በግምባራቸው ላይ ምልክት ያድርጉ ማለት አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ በድርጊታቸውም ሆነ በአስተሳሰባቸው በአምላክ ሕግጋት መመራት እንዳለባቸው የሚያሳስብ ነበር። በተመሳሳይም ሰዎች የአውሬውን ምልክት ያደርጋሉ ሲባል ሰውነታቸው ላይ 666 የሚል ምልክት እንደሚነቀሱ የሚያሳይ አይደለም፤ ሰዎች የአውሬውን ምልክት ማድረጋቸው የፖለቲካው ሥርዓት ሕይወታቸውን እንዲቆጣጠር መፍቀዳቸውን የሚጠቁም ነው። የአውሬውን ምልክት የሚያደርጉ ሰዎች የአምላክ ተቃዋሚዎች ናቸው።ራእይ 14:9, 10 19:19-21
ተዛማጅ ርዕሶች

Accessibility links
Skip to main content

Accessibility feedback






ኢሉሚናቲ በኢትዮጵያ pdf










Search modes

SettingsTools

About 711 results (0.33 seconds) 




Ethiopia: የዝነኞቻችን ድብቅ ገመና እና ቢዮንሴ በኢትዮጵያ 666 እንጠንቀቅ ንቁ | Beyonce


ኢሉሚናቲ መሆኗን ያመነችው ቢዮንሴ 
Beyonce in Ethiopia

ይሄንን ጥያቄአዎብለው የሚመልሱና ይህ ስሜት የተጋባባቸው የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ፀሐፊዎችና የቤተክርስቲያን ሰዎች ስለ ሚስጥራዊ ማህበራቱ የሚያስገነዝቡ መጽሐፎችንና ቪሲዲዎችን በአማርኛ አዘጋጅተው ለገበያ አቅርበዋል፡፡ ሁሉም ጉዳዩ የኢትዮጵያም ስጋት እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ በሚስጥራዊ ማህበራቱ ውስጥ አሉ የሚባሉ ሠዎች በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ብለዋል፡፡ በመንግስትና በህዝቡም ደማቅ አቀባበል ጠብቋቸዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የኢሉሚናቲ አባላት መካከል ቢዮንሴና የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ይገኙበታል፡፡ ከታዋቂ የቴሌቪዥን ሾው አቅራቢዋና ራሷም ኢሉሚናቲ እንደሆነች ከሚነገርላት ኦፕራ ዊንፍሬይ ጋር በቅርቡ ባደረገችው ቃለ ምልልስ ወቅት ኢሉሚናቲ መሆኗን ያመነችው ቢዮንሴ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ በመንግስትና በወቅቱ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ የተደረገላት አቀባበል ደማቅ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በነበራት ቆይታም የኢሉሚናቲ ምልክቶቹን በኮንሰርቷ ላይ ከማሳየቷ በተጨማሪ በገጠር ለሚኖሩ ህፃናት ስታሳያቸውና እሷ የምታደርገውን እንዲያደርጉ ስታስተምራቸው ታይቷል፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ዝነኛ ሰዎች የሚያስተላልፉት መልዕክትና ሙዚቃዎቻቸውና ፊልሞቻቸው በወጣቱ ትውልድ ያገኘው ተቀባይነት ለሚስጥራዊ ማህበራቱ ዓላማ መሳካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለው እንደሚያምኑ ስለሚስጥራዊ ማህበራቱ የሚገልጽ ሁለት ቪሲዲዎችን ለእይታ ያበቁት ኢትዮጵያውን ወጣቶች ይናገራሉ፡፡ ሁለቱ ወጣቶች ደቀመዝሙር ሜሎስ ተሾመ እና ዲያቆን እዮኤል ጌታቸው እንደሚሉት ወደሃገራችን ብቅ ያሉ የውጭ ሀገር ድምጻዊያን የሰይጣን አምልኮታቸውንና የኢሉሚናቲ ምልክቶችን በተለያ መንገድ ሲያሳዩ ነበር፡፡ በሃገራችንምየሰይጣን መጽሀፍ ቅዱስበአማርኛ ተተርጉሞ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በብዛት እንደሚነበብ ወጣቶቹ ገልጸዋል፡፡ እንደወጣቶቹ ገለጻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ተማሪዎች እጅ መጽሐፉን በተደጋጋሚ ተመልክተውታል፡፡
ክፍል 2 (ከወጣቶቹ ጋር ተደረገውን ሙሉ ቃለምልልስ እዚህ ይመልከቱ)
የዶ/ ሮበርት ሂሮኒመስን Founder Father, The Secret Societies መጽሐፍ መነሻ በማድረግ ስለሚስጥር ማህበራት ሁለት ተከታታይ የአማርኛ መፅሐፍትን ለንባብ ያበቃው ተርጓሚና ጋዜጠኛ ወርቃፈራሁ አሰፋ እንደሚለው ደግሞ ኢትዮጵያ የዓለም አንድ አካል እንደመሆኗ መጠን ጉዳዩ ለሷም ያሰጋታል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የነዚህ ማህበራት መረብ አለ ወይም የለም ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ መሆኑንና ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልጉት ወርቃፈራሁ ይገልጻል፡፡





ኢሉሚናቲ በኢትዮጵያ 2008

Search Results
Web results


  1. https://youtu.be/6bdw_lc_TKE 
Aug 29, 2015 - ክፍል 1 የሰይጣን አምላኪዎች ማህበር በኢትዮጵያ? - የሚስጥር ማህበርተኞችኢሉሚናቲ - ሰይጣን አምላኪዎች ምንኖርባት ዓለም በብዙ እንቆቅልሾች የተሞላች ...




Sep 18, 2012 - በግደይ ገብረኪዳን በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ስለ ኢሉሚናቲ ማውራት ከአመት በፊት ከነበረው ሁኔታ እንኳ በእጅጉ ተቀይሯል፡፡ አሁን ቢያንስ ስሙን እንኳ ...















Web results





Jun 10, 2014 - ኢሉሚናቲ ( Illuminati 666 ) ስውሩ እጅ ... የሚያካሂደውን መሰሪ አላማና እቅድ እኛንም ስለነካን ነው 97 ምርጫን መነሻ ያደረኩትበኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ትልቅ ...

People also search for



Nov 20, 2017 - DOWNLOAD PDF - 1.4MB. Share Embed Donate. Report this link. Short Description. Download ሉላዊ ሴራ - የተሸሸጉ ታሪኮች_ መጽሐፍ ቅዱስ እና ...




Posts about ኢሉሚናቲ ( Illuminati ) ምንድነው? በኢስላም እንዴት ... በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ የተቀመጠውን ባለ አምስት ጎን ኮከብ ብዙዎቹ ይቃወሙታል። ምልክት(symbol) ...



በምስጢር አጋንንታዊ የሆነ 666 ቁጥር ተጽፎበት የተሻሻለ የእስራኤል ባንዲራሲሰቀልበት፣በኢትዮጵያ በሚገኘው የራስ ዳሽን ተራራ ላይ ደግሞ የመስቀል ምልክት ያለበት ...
[PDF]




Mar 19, 2015 - ይዘት ምንነታቸው የሚታወቁ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህ ኢሉሚናቲ በመባል .... ቤት አስገዝታዋለች አሉ - ይሄንኑ የአጋንንት ወኪል በኢትዮጵያ፡፡ በነገራችን ላይ.





Nov 12, 2012 - November 11, 2012 · 0 Comments. images. Chief Commander of the Order of the Star of Ethiopia – 1909. Grand Cordon of the Order of ...




Apr 6, 2016 - ቢልጌትስ ወደ ፊት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በኢትዮጵያ በመመደብ ኢትዮጵያዊ ህፃናትንና ሌሎችን በተለይም በገጠራማው ክፍል ያሉትን ማህበረሰቦች የአስተሳሰብ ...

Ads
  1. Fill & Sign PDF Documents | #1 Easiest e-Signature Service‎
  2. Adwww.hellosign.com/SignPDF‎

    Get Your PDF Signed in Seconds. Secure, Trusted by Millions. Sign Up For Free! Clean And Paperless. eSign From Any Device. Types: Insurance, FinTech, Real Estate Technology, HR Technology, On-Demand Marketplace.
  3. PDF In PDF | Find PDF In PDF‎
  4. Adwww.info.com/PDF+In+PDF/results‎

    Search PDF In PDF. Visit & Lookup Immediate Results Now.
  5. Free Online PDF Editor | Convert PDF [Free]‎
  6. Adwww.pdfsimpli.com/to-convert/pdf-jpg-Free‎
    +1 800-429-9847
    Easiest and Most User Friendly PDF Editor **PDFSimpli** Making PDF Conversion and Editing Simple. Convert, [Download] & Print For Free! Just point and click. Instant & Free. PDFs Made Simple. No Download. Services: Convert PDF to Word, Convert Word to PDF, Edit PDF.


Searches related to ኢሉሚናቲ በኢትዮጵያ pdf
የኢሉሚናቲ 666  ኒው ወርልድ ምልክቶች በስዎች ሲገለጥ 

https://www.youtube.com/watch?v=D68dr7wbdFQ የኢሉሚናቲ 666  ኒው ወርልድ ምልክቶች በስዎች ሲገለጥ 


European Union Has Sign 666 Mark of the Beast Law ? MUST SEE (New World Order is Complete ) በዩሮፕ ህብረት በግልጥ በእርግጠኝነት የታየው የአውሬው 666 ምልክት 


FALSE = New World Order & 666 Mark of the Beast, AntiChrist, False Prophet ኒው ወርልድ ኦርደር 666 የተሳሳተና አጥፊ መሆኑን የተሰጠ ትምህርት 
ጥንቆላ - በሀገራችን በቤተ ክርስቲያናቸን እንዲሁም
በእያንዳንዳችን ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ
Read in PDF
ራሳችንን ከጥንቆላ ስራዎች ለመጠበቅ ወይንም ሳናውቅ
የጥንቆላ ስራዎች ተባባሪ ከመሆን ለመዳን ስለ ሀገራችን
የጥንቆላ ዘዴዎች መጠነኛ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ጠንቋይ
ማለት ጠንቅ ዋይ ወይም ጠንቀኛ ማለት ነው። በሀገራችን
ሁለት ዓይነት የጠንቋይ አይነቶች አሉ። አንደኛው ወገን ባለ ዛር፣
ባለ አውሌ (ውቃቤ) የሆኑትን ሲያካትት ሁለተኛው ወገን ደግሞ
ደብተራ የሚባሉትን ያካትታል።
ባለ ዛር ወይንም ባለ ውቃቤዎች
አውሌ ወይም ዛር የሚባሉት በሰው ላይ ሰፍረው አምልኮን
ለራሳቸው የሚወስዱ የአጋንንት ወገን ናቸው። ባለ አውሌዎች
በመላው ኢትዮጵያ ይገኛሉ። በኦሮሞው፣ በአማራው፣ በጉራጌው
ወዘተ በየትኛውም ብሔር ብሔረ ሰብእ ዘንድ በብዛት አሉ።
ብዙዎቹ ሃይማኖታቸው እስልምና ወይም ኦርቶዶክስ ክርስቲያን
እንደሆኑ ይናገራሉ። ብዙውን ጊዜ አማኞች ለመምሰል የአላህን
ወይም የእግዚአብሔርን ስም ያነሳሉ። እንዲህ የሚያደርጉት
ብዙዎች ደንበኞቻቸው ከእስልምና ወይም ከክርስትና የመጡ
ስለሆኑ ይመስላል። ኢየሱስ የሚለውን ስም ግን ተሳስተውም
እንኳ አይጠሩትም።
«እስላም» ነኝ የሚለው ባለውቃቤም ሆነ «ክርስቲያን» ነኝ
የሚለው ባለ ውቃቤ ገብርኤልን ሚካኤልን እና አቡየ ገብረ
መንፈስ ቅዱስን ይወዳሉ። በየዓመቱ ዝክራቸውን ይዘክራሉ ቤተ
ክርስቲያናቸውን ይሠራሉ በየቤታቸውም ስእሎቻቸውን
አንጠልጥለው እጣን ያሳጥናሉ፤ በበአላቸው ቀን ጃንጥላ፤ በሬና
ጊደር የመሳሰሉ ስእቶችን ያደርጋሉ። ይህን የሚያደርጉት
ክርስቲያን ባለውቃቤዎች ብቻ አይደሉም፤ እስላሞችም ጭምር
ናቸው እንጂ። እኛ ካህናቱም ይህን እያወቅን መባቸውን
(ስዕለታቸውን) እልል ብለን እንቀበላቸዋለን። በቁልቢ ገብርኤል
ከሚገኘው መባእ ውስጥ አብዛኛውን የሚሰጡት የእስላምናና
ክርስቲያን ባለውቃቤዎች ናቸው። በቁልቢ ገብርኤል ከመተካቱ
በፊት ባለ አውሌ ያሟርትበት የነበረ ሥፍራ ነበር ሲባል
ሰምቻለሁ። ዛሬም በስፍራው ባለውቃቤዎች አይታጡም። ባለ
ውቃቤዎች በሚካኤልና በገብርኤል ቀን ደመቅ ያለ ዘፈን
አላቸው ዝክርም ይዘክራሉ። ጽድቅን ለማግኘት ይሆን? የነሱ
ደግሞ እስከ ስንት ትውልድ ይማር ይሆን? ለምሳሌ ምእራብ
ሽዋ ውስጥ የሚገኘው የሙገሩ ታዋቂ ጠንቋይ የሚካኤልን ቤተ
ክርስቲያን አሠርቶ ህዳር ሚካኤልን ሞቅ ባለ ድግስ ይዘክራል።
በዚያ ቀን ከአዲስ አበባ ወደ ባለ ውቃቤው የሚጓዘው ሕዝብ
እጅግ ብዙ ነው። በጎጃም አዲስ ቅዳም ውስጥ የሚገኘው
ታዋቂ ጠንቋይ የገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን አሠርቷል። በወሎ
ያለው ታዋቂ ባለዛር ግን መስጊድ አሰርቷል። ታዋቂ ጠንቋዮችን
ለምሳሌ ያህል ጠቀስሁ እንጂ ሁሉም ባለውቃቤ የራሱ የሆነ
ታቦት አለው። ነገር ግን በሚካኤልና በገብርኤል ስም
የሚነግደው ጥንተ ጠላታችን ሰይጣን እንደሆነ ጥርጥር
የለውም።
ዛሩ በነርሱ ላይ የሚወርደው በልዩ ልዩ አምልኮ ሲለማመጡት
ነው። ቡና ይፈላለታል ዶሮ ወይም በግ ይታረድለታል፤ ስግደት
ይቀርብለታል፤ ዘፈን ይዘፈንለታል፤ አታሞና ከበሮ ይመታለታል።
በዚህ ጊዜ ባለውቃቤው ከመጋረጃ ውስጥ ሆኖ ያጓራል። በዚህ
ጊዜ መንፈሱ ወረደ ይባልና እልልታ ይደረጋል። እርሱም
የሚረግመውን ይረግማል የሚመርቀውን ይመርቃል። ከዚያም
ለማስጠንቆል የመጡ ደንበኞቹ ሁሉ በተራ እየሰገዱ እጣ
ፈንታቸውን ይጠይቃሉ የተጣሉትን ያስረግማሉ። እባክህ አትርሳኝ
እያሉ ይማጸናሉ። በማግስቱ ደግሞ በማርያም ስእል ፊት
ወድቀው እባክሽ አማልጅኝ እያሉ ይጸልያሉ። ወይ ያላረፈች
ነፍስ!
ደብተራ
ደብተራ ማለት ድንኳን ማለት ነው። ደብተራ የሚለው ስያሜ
ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የተሰጠው በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን
ነው ይባላል። በድንኳን ውስጥ በጽሑፍና በድርሰት በማህሌት
የሚያገልግሉ የዘርዓ ያዕቆብ ሰራተኞች ካህናተ ደብተራ ይባሉ
ነበር። በድንኳን ውስጥ ስለሚኖሩ ስማቸው ደብተራ ተብሎ
ይጠራ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በማህሌት ክፍለ አገልግሎት
የሚመሰማሩ አገልጋዮች ደብተራ ይባላሉ። ሚስታቸው
የሞተችባቸው ቄሶች ወደ መቅደስ ገብተው መቀደስ አይችሉም፤
ቅኔ ማህሌት ገብተው ግን ማገልገል ይችላሉ። በዚህ ምክንያት
ደብተራ ይባላሉ።
የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የጸነነባቸው ማለት ቅኔው
ያልገባቸው፤ ዜማው ያልተቃኘላቸው ሰዎች በአቋራጭ ዘወር
ብለው የሰሎሞን ጥበብ የሚሉትን ጥንቆላ ይማራሉ። ትምህርቱ
የገባቸውም አንዳንዶች ጥንቆላውን ይማሩታል። በጥንቆላ
ትምህርት የታወቀ መሪጌታ፣ ቄስ ወይም ገበሬ ያልተማረ እንኳ
ቢሆን ደብተራ ይባላል።
የደብተራ ጥንቆላ ከድግምት ጋር የተያያዘ ነው። ድግምቱ
ትርግሙ የማይታወቅ ስም ቋንቋና አሠራር አለው። ሆኖም
ሥራው የሚሠራው በአጋንንት ኃይል ነው። ከአጋንንት ጋር ቃል
ኪዳን በማድረግ ከፍተኛ መተቶችን ይሠራሉ። ብዙ ጊዜ
ደብተራዎች ቃል ኪዳን ለማድረግ የሚመርጧቸው የአጋንንት
አለቆች በደብተራዎች አጠራር የሚከተሉት ታዋቂዎች ናቸው።
አየረ ጴጥሮስ፦ አየረ ጴጥሮስ የሚባለው ሰውን ለመግደል፤
ለማፍዘዝ፤ ለማሳበድ፤ የሚዋረሱት አደገኛ የአየር ጋኔን ነው።
አየረ ጴጥሮስን የተዋረሱ ደብትራዎች ሴትና ሽቱ ይወዳሉ።
ገንዘብ ያገኛሉ ግን አይበረክትላቸውም። በየጊዜው ለጋኔኑ ደም
የሚገብሩ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን ገብተው ማገልገል በጣም
ይወዳሉ።
አፈ ሕጻን፦ አፈ ሕጻን የሚባለው ደግሞ የምድር ጋኔን ነው።
ልክስክስ ደካማ ጋኔን ሲሆን በሰው ላይ የሚፈጽመው ተንኮል
ግን ከባድ ነው። በቡና በአረቄና በጠላ የሚሳብ ነው፤ አፈ ሕጻን
የተባለበት ምክንያት በሕጻን ልጅ የሚሳብና በሕጻኑ አንደበት
የሚናገር ስለሆነ ነው። ጋኔን የተሳበበት ሕጻን የኋላ የኋላ እብድ
ሊሆን ወይም የአእምሮ ዝግመት ሊያጋጥመው ይችላል።
ስሙ ለአብ፦ ይህ ጋኔን ለአቃቤ ርእስ ለሀብትና ለሥልጣን
የሚዋረሱት ሰይጣን ነው። ባለ ሥልጣን ባለሀብት ሆነው
ትዕቢተኞች ይሆናሉ፤ ጠባያቸው ከማንም ጋር አይስማማም።
ይህን ጋኔን የተዋረሱ ሰዎች እጅግ አመንዝራዎች ናቸው። በዚህ
ጋኔን የሚገለገሉ ጠንቋዮችም ሆኑ አስጠንቋዮች በብዛት
ታንቀው ይሞታሉ። ወይም በድንገት ሞተው ይገኛሉ። በነገራችን
ላይ ደብተራዎች ስሙን እየቀያየሩ ይጥሩት እንጂ ያው አንዱ
ዲያብሎስ ነው።
ደብተራዎች የተለያየ ዓይነት ናቸው። ሰይጣንን ሳይዋረሱ
በድግምትና በሟርት የሚሠሩ፤ ሰይጣንን ተዋርሰው [ቃልኪዳን
ገብተው] የሚሠሩ፤ መናፍስትን የሚጠሩ፤ ምሕሳበ ቅዱሳን
የሚደግሙ፤ መልክአ ሳጥናኤል ብቻ በመድገም የፈለጉትን
የሚያደርጉ አሉ። እንዲህ ዓይነት ሥራ አይሠራም ሰይጣንም
ይህን ያህል አይሰራም የምትሉ አንባብያን ካላችሁ ሰይጣንም
የሚፈልገው እንዲህ አይነቱን መዘናጋት እንደሆነ
እንድትረዱትና እንድታስቡበት እጠይቃለሁ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ጠንቋዮችና መናፍስት ጠሪዎች የተወገዙ
ናቸው።
«ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ
እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው እኔ እግዚአብሔር
አምላካችሁ ነኝ» ዘሌ 1931
«መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን በሚከተል በሥራቸውም
በሚያመነዝር በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ ከሕዝቡም
መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ» ዘሌ 206
«ወንድ ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ
ፈጽመው ይገደሉ በድንጋይ ይውገሯቸው በማቸው በላያቸው
ነው» ዘሌ 2027
«አስማተኛም መተተኛም፣በድግምት የሚጠነቁልም፣
መናፍስትንም የሚጠራ፣ ጠንቋይም፣ ሙታን ሳቢም፣ ባንተ ዘንድ
አይገኝ» ዘዳ 1811
ከላይ እንደዘረዘርሁት አስማተኛ ማለት ትርጉማቸው የማይታውቁ
ስሞችን መጥራት ማለት ነው። እንዲህ ዓይነቱን አስማት
ለማየት «መልክአ ራጉኤል» እየተባለ የሚጠራውን በተስፋ ገብረ
ሥላሴ ማተሚያ ቤት የታተመውን የጸሎት መጽሐፍ እንደ ምሳሌ
ያህል መመልከት ነው።
መተት ማለት ማስመስል ማለት ነው። በአይን ላይ የሚደገም
አስማት ነው። ለምሳሌ ኢያኔስና እያንበሬስ የተባሉ የግብጽ
ጠንቋዮች መተት አዋቂዎች ነበሩ ዘጸ 711
ድግምት ደግሞ ፍለጠው ቁረጠው እያሉ በአጋንንት ስም
መራገም ነው። ድርሳነ ሚካኤል በጥቂቱ ይህ ዓይነቱ ድግምት
ይገኝበታል፤ የሕዳር ሚካኤል የሚነበበውን ይመልከቱ።
መናፍስትን መጥራት ከላይ እንዳየነው የተለያዩ አጋንንትን
መጥራት ሲሆን በቃል ኪዳን ተዋርሰው የታዘዙትን ሁሉ
ያደርጋሉ።
ሙታን ሳቢ፦ ይህ ጥንቆላ በአገራችን ደብተራዎች ቋንቋ
ምህሳበ ቅዱሳን ይባላል። የሞቱ ቅዱሳንን ለመጥራት
የሚያገለግል ድግምት ነው። እንዲህ አይነቱን አስማት
ባሕታውያን እየተባሉ የሚጠሩ ደብተራዎች አዘውትረው
ይጠቀሙበታል። ሆኖም ግን በሙታን ስም የሚመጣው ያው
የታወቀው ጠላታችን መሆኑ አያጠያይቅም። ሙታንን የሚስቡ
ሰዎች እራሳቸውን ከሰው አግልለው መኖር ይመቻቸዋል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ሙታንን መጥራት የቻሉ ጠንቋዮች እንደነበሩ
ተጽፏል 1 ሳሙ 289
ደስ የሚያሰኘው ነገር
እነዚህ በሰማይና በምድር ያሉ ኃይላት በባለ ውቃቤም ሆነ
በደብተራ ስም ይምጡ እንጂ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ
ስም ይንበረከካሉ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጋንንት
የማይቋቋሙት ስም ነው። «ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም
ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ
በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር
አብ ክብር ኢየሱስም ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው» ፊልጵ
210-11 ሟርትም አስማትም በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው
ስሙን በሚጠሩ ላይ ፈጽሞ አይሰራም። ወደ እግዚአብሔር
የተጠጉ ሁሉ ከሰይጣን ወጥመድ ያመልጣሉ።
«በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ
ያድራል።
እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ አምላኬና
መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።
በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ እውነት
እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ
ግን አይቀርብም።
አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ
አይገባም።
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ
ያዝዛቸዋልና
እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ አንበሳውንና ዘንዶውን
ትረግጣለህ።
በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ ስሜንም አውቆአልና
እጋርደዋለሁ» መዝ 90 [91]
አማላክችን ከጨላማው ስልጣን አድኖ ወደ መንግሥቱ
አፍልሶናል ቈላ 113 እባቡን እና ጊንጡን እንረግጥ ዘንድ
ሥልጣን ሰጥቶናል ሉቃ 1019።ጠላታችን ከእግራችን በታች
ፈጥኖ የሚቀጠቅጠው እርሱ ጠላቶቹን ከግሮቹ በታችን
የረገጣቸው ዛሬም በደሙ ይሸፍነናል። ሮሜ1620
ክርስቲያኖች በዚህ እጅግ ደስ ልትሰኙ ይገባል።
ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ለመርዳት የምንፈልግ ሁሉ ወንጌልን
እንስበክ፤ ለነጻነት፤ ለልማት፤ ለዲሞክራሲ፤ ለፍትሕ እንታገል።
ሕዝባችን በመናፍስት ጠሪዎች እጅ ስለወደቀ በረከት ርቆት
በችግር ላይ ይገኛል። ነጻ የሚያወጣን የይሁዳ አንበሳ የናዝሬቱ
ኢየሱስ ነው።
በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ የዲያብሎስን
ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር
ሁሉ ልበሱ መጋደላችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምና
ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዥዎች
ጋር በሰማያዊም ሥፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር
ነው እንጂ ኤፌ 610-13

መልክአ ሚካኤል + የቅዱስ ሚካኤል ድርሳን
==SHARE
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኖ ከአስማተ መለኮት ጋር በማስተባበር የሚጸለይ የቅዱስ ሚካኤል ድርሳን ይህ ነው።
እግዚአብሔር ስለ ትሕትናው ስለ ታማኝነቱና ስለ ፍጹም ክብሩ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ይህ አስማተ መለኮት ታላቅና ገናና ክቡርና አሸናፊ ነው።
ቀድሞ በሰማይ ሠልፍ በሆነ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ዘንዶውን ወግቶ ወደ መሬት የጣለው በዚህ አምላካዊ ስመ መለኮት ነውና። አቤቱ እኔም ረቂቃኑን ግዙፋኑን ጠላቶቼን ድል እመታ ዘንድ በትሁት ሰብእና ሁኜ እነዚህን ቃላቶች እጸልያለሁ እንዲህ እያልኩ ኤኮስ አሜዕ ኤኪ ኤንካዕ ካዜዕ አርናኬ ኬም ካዮን ፒካጊሎ አስኤሎት አስሶሙ አርኤም ያብስትጋ ፓኢርጋ ያብሲት ፌኤ ኤልካዕ ኢንካዕ ብዕላኪፍ አርኅሎ አዎፅ። እነዚህ የከበሩ ቃላትና የእግዚአብሄር ሕቡዕ ስሞች በቅዱስ ሚካኤል እጅ የተገኙና በዕብራይስጥ ቋንቋ ከቃላቶች ሁሉ የበላይ እንደሆኑ የታወቀ የተረዳ ሆነ።
ይህንን መጽሐፍ የጻፈ ሰው ይህንን ኅቡዕ ስም ከመጽሐፍ አይለየው በንጹህ ቦታ አስቀምጦ በክብር ይጠብቀው እንጂ ለዘለዓለሙ ጠላቱን አሸንፎ ለእርሱ ጋሻ መከታ ይሆነዋልና።
በመዓልትና በሌሊት ለጥፋት የሚዘዋወሩ የጸላዒ ዲያብሎስ ሠራዊቶች በአሸናፊው በእግዚአብሔር መቅሠፍተ መዓት ፈጽመው ይደምሰሱ አሜን።
በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ጸሎት በዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክትና በሃያ አራቱ ካሕናተ ሰማይ በአርባዕቱም እንስሳም ጸሎት ርኩሳን መናፍስት ጸዋጋን አጋንንት ይውደሙ አሜን።
የወልደ እግዚአብሔርን ቃለ ወንጌል በጻፉ በማቴዎስና በማርቆስ በሉቃስና በዮሐንስ ቃል በጴጥሮስና በጳውሎስ ስልጣን የተወገዙ ይሁኑ።
በነፍስ በሥጋ በውስጥ በአፍአ ንጽሕት በሆነች ከሴቶች ሁሉ ተለይታ ንዕድ ክብርት የምትሆን የፍጥረት ሁሉ መመኪያ በሆነች አምላክን በወለደች በቅድስት ድንግል ማርያም የጸሎት ኃይል የዲያብሎስ አበጋዞች እኩያን መሠርያን የዛር ውላጆች ሟርተኞች ፈጥነው ይወገዱ አሜን።
በመዓልትና በሌሊት በቀትርና በሰዓት ከጧት እስከ ማታ ከማታም እስከ ጧት የሰውን ሰውነት የሚያስደነግጡ የዲያብሎስ ሠራዊት አጋንንትና ሰይጣናትም ሁሉ የምድር ማዕዘኗን በሚያጸኑ በሰባቱ ኃይለ ነፋሳት እንደ ጢስ ተነው እንደ ጉም በነው ይጥፉ አሜን።
በኔና የጥምቀት ልጆች በምንሆን የክርስቶስ ወገኖች ሁሉ ላይ ግን ከላይ ከሰማይ የእግዚአብሔር ምሕረቱ ቸርነቱ ይቅርታው ይምጣልን አሜን።
የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ከእግዚአብሔር በተሰጠህ በዚህ የቃል ኪዳን ኃይለ ጸሎት ከሚቃወመኝና ከሚጻረረኝ ረቂቅና ግዙፍ ጠላት በመዓልትም በሌሊትም እኔን አገልጋይህን ______ ለዘለዓለሙ ጠብቀኝ አሜን።
አቡነ ዘበሰማያት
==//==
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ ከሰይጣን ወጥመድ ለማምለጥና ከአጋንንትም ሁሉ ጸብ ለመዳን ይህንን አስማተ መለኮት እጸልያለሁ እንዲህ እያልኩ።
ጓዕ ወአብሶላ አስቤክ አበስኩዕ አሜዕ አውጽእ ኤቃእ አዎፅ ካብዕሬው አርኅላዮን ያብሳት አቤቱ በነዚህ ኅቡዕና ሥውር በሚሆኑ ስሞችህ እና የመላእክት ሁሉ አለቃ በሚሆን በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ሁለተኛ ደስታን በሚያበስር በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ሦስተኛ በወላጅ እናትህ በቅድስት ድንግል ማርያም ይቅርታና ምሕረት ጠያቂነት እኔን አገልጋይህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውረኝ።
የደኅንነት መልእክተኛ ሚካኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ድኃውን የምትንከባከበው መልአክ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ችግረኛውን ለመርዳት
የምትላክ መልአክ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። በመታመን ለለመነህ ሁሉ ክንፈ ረድኤትህን የምትጋርድለት ሚካኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ለመውደቅ የሚፍገመገመውን እንዳይወድቅ ፈጥነህ የምትደግፈው መልአክ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ያዘነውን የምታረጋጋው መልአክ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። አምላካችን ቸርነትን በተመላ እጁ ይባርከን ዘንድ በፈጣሪህ ፊት በአድኖ ርእስ ሰግደህ ይቅርታን የምታሰጥ ሚካኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ።
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አምላክ ሆይ እኔን አገልጋይህን ________ ከተቃጣ መዓት ከታዘዘ መቅሠፍት ሠውረኝ ለዘለዓለሙ አሜን።
አቡነ ዘበሰማያት
=====//=======
መልክአ ሚካኤል
1᎐ለዝክረ ስምከ
ሚካኤል ሆይ የያሬድ ልጅ ኄኖክ እንደጻፈው። ከልዑል ስም አጠራር ጋር ለተባበረ ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ። የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ
ሆይ የተቸገሩትን የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልኝ።
2᎐ለስርእተ ርእስከ
ሚካኤል ሆይ ከፈጣሪህ በቀር ሥነ ባሕርዩን ማንም ተመራምሮ ለማይደርስብት ነበልባላዊ ስእርተ ርእስህ ሰላም እላለሁ። የእግዚአብሔር ባለሟል ሆይ በእግዚአብሔር ፊት በጎ መዓዛ ያለውን መሥዋዕት የምታሣርግ አንተ ሚካኤል ነህና። ከኅዘንና ከልቅሶ የተነሳ እኔን አገልጋይህን እርጅና እንዳይጫነኝ ሰውነቴ ባዘነችና በተከዘች ጊዜ ልቡናዬን ታረጋጋት ዘነድ ፈጥነህ ድረስላት።
3᎐ለርእስከ
ሚካኤል ሆይ መብረቅን ለተጎናጸፈ መልአካዊ ረቂቅ ርእስህ ሰላም እላለሁ። ተፈጥሯቸው ከእሳት የሆነ የሰማያውያን የመላእክት ሠራዊት አለቃቸው የምትሆን ሚካኤል ሆይ በኃጢአት ተሰነካክዬ ወድቄ እንዳልፍገመገም አንተን ድጋፍ አድርጌአለሁና። ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ።
4᎐ለገጽከ
ሚካኤል ሆይ መሬትና ውሃ ያልተቀላቀለበት ከነፋስና ከእሳት ብቻ ለተፈጠረው መልአካዊ ገጽታህ ሰላም እላለሁ። የምሕረት መልአክ ሆይ
የሊባኖስ ዛፎች በአፁቃቸው ታጅበው በልምላሜያቸው አሸብርቀው እንዲታዩ ልመናዬን በማቀርብበት ጊዜ ሁሉ መጭውን ዘመኔን በክንፈ ረድኤትህ ተንከባክበህ በቸርነትህ ጌጥ አስጊጠኝ።
5᎐ለቀራንብቲከ
ሚካኤል ሆይ የአገላለጥ እንቅስቃሴያቸው የቸርነትህ የየዋህነት ለሆነ ቀናብርትህ ሰላም እላለሁ። የእግዚአብሔር የቸርነቱ ጉዳይ አስፈጻሚ ሚካኤል ሆይ
ችግረኛን ለመርዳት በሁሉ ቦታ የምትገኝ አንተ ነህና። የተለመደውን ቸርነትህን በልቤ አወጣለሁ አወርዳለሁ ስለዚህም ትድግናህን ተስፋ አደርጋለሁ።
6᎐ለአዕይንቲከ
ሚካኤል ሆይ ለሰው ልጅ ይቅርታን ለማስገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልዱ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል። ሚካኤል ሆይ በጠላት ተማርከው ለሚጨነቁትና ለሚሰቃዩት ዋስ ጠበቃቸው አንተ ነህና። በኔ ላይ የሚተበትቡትን የጠላቶቼን የምክር መረብ በጣጥሰህ ጣልልኝ ነፍሴንም ሥጋዬንም ለአንተ አደራ ሰጥቻለሁና።
7᎐ለአዕዛኒክ
ሚካኤል ሆይ የችግረኛውን ሁሉ ጸሎት ፈጥነው ለሚሰሙ አዕዛኖችህ ሰላምታ ይገባል። የይቅርታ መልአክ ሆይ ችግሬን አቃልልኝ ጭንቀቴን አስወግድልኝ። ምክርን ትለግሰኝ ጥበብንም ታስተምረኝ ዘንድ አባት እንዳደረኩህ አንተም ልጅ አድርገኝ።
8᎐ለመላትሒከ
ሚካኤል ሆይ ፈጽሞ የሚያንጸባርቅ የፈገግታ ሽቱ ጠል ለረበረበባቸው ጉንጮችህ ሰላምታ ይገባል። መሰልቸት የሌለብህ መልአክ ሆይ የተለመደው ቸርነትህን አታጓድልብኝ በችግሬ ጊዜ በትምህርተ መስቀል አመሳቅዬ በምጸልይበት ጊዜ ትረዳኝ ዘንድ ፈጥነህ ድረስልኝ እንጂ።
9᎐ለአእናፊከ
ሚካኤል ሆይ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ከአንተ ጋራ መሥዋዕትን በሚያቀርቡ ጊዜ የጽርሐ አርያምን መዓዛ ለተመሉ አዕናፍህ ሰላምታ ይገባል። ቸር ጠባቂ መልአክ ሆይ የነገደ እሥራኤል (የያዕቆብ) ጠባቂ አንተ ነህና። ጓደኞችህ መላእክትን እኔን አገልጋይህን ወዳጄን ጎብኙ ብለህ ጋብዛቸው። በአንዱ ፍቅር ሌላው ይሳባልና።
12᎐ለአስናኒከ
ሚካኤል ሆይ መሰበር መጥረስ ለማያገኛቸው ረቂቃን አስናኖችህ ሰላም እላለሁ። ረዳቴ መልአክ ሆይ በባሕር ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ በየብስ ላይ ለሚመላለሱ ፍጥረታት ሁሉ ረዳታቸው አንተ ነህ። ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ካህን አድርጎ ሾሞሃልና። አንተ ቀሲሱ ሚካኤል ለኔ ለአገልጋይህ ምህረትን ትለምን ዘንድ ተገቢ ነው።
13᎐ለልሳንከ
ሚካኤል ሆይ ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በተደረገ ጊዜ የዘለፋ ቃል ላልተናገረ አንደበትህ ሰላም እላለሁ። ክቡሩ መልአክ ሆይ ክብርህ ከመላእክት ሁሉ ክብር ከፍ ያለ ነውና። በሥነ ሥዕልህ ፊት ቁሜ ልመናዬን በማቀርብበት ጊዜ ሁሉ። አይዞህ አለሁልህ በማለት ፈጥነህ ድምጽህን አሰማኝ።
14᎐ለቃልከ
ሚካኤል ሆይ የጽርሐ አርያምን የምስጋና ጠፈር አልፎ እስከሚሄድ ከፍታ ላለው ኃይለ ቃልህ ሰላም እላለሁ። ተራዳኢው መልአክ ሆይ ብስጭትና ፈተና ደርሰውብኝ ወደ አንተ በማመለክትበት ጊዜ ወዳጅ ለወዳጁ ለችግሩ እንደሚደርስለት። ወዳጅህን ለመርዳት ተፋጠን እንጂ የቸርነትህን በር አትዝጋብኝ።
15᎐ለእስትፋስከ
ሚካኤል ሆይ የነፍስ ቁስለኞችን ለማዳን መድኃኒተ ፈውስን እፍ ለሚለው እስትንፋስህ ሰላም እላለሁ። ድል አድራጊው መልአክ ሆይ የቀድሞው አመፀኛው አውሬ (ዲያብሎስ) የጥንት ተንኮሉን ሊተው አልቻለምና። የጦር መሣሪያህን ታጥቀህ። መጥተህ ድምጥማጡን አጥፋው።
16᎐ለጉርዔከ
ሚካኤል ሆይ ድምፀ ጉህናው በጽርሐ አርያም እስኪሞላ ድረስ የምስጋና ቃል ለሚያስተጋባው ጉርዔህ ሰላም እላለሁ። ትጉሁ መልአክ ሆይ በምርኮ ላይ ሆነው ለሚጨነቁት የምትደርስላቸው አንተ ነህና። ወደ አንተ በምማልድበት ጊዜ ፈጥነህ ሰላምን ስጠኝ እንጂ ዛሬ ነገ እንዳትለኝ እማልድሃለሁ።
17᎐ለክሣድከ
ሚካኤል ሆይ ከዕንቁ ባሕርይ ይልቅ የሚያስደንቅ የሥነ ተፈጥሮን ሐብል ለአጠለቀ ክሣድህ ሰላም እላለሁ። ርኅርኁ ሚካኤል ሆይ አዝማናትን በየክፍላቸው ጽፈህ የምታዘጋጅ ነህ። የሕዝብን ኃጢአት ለማቃለል ለካህን ስልጣን ተሰጥቶታልና በአማላጅነትህ መስዋዕተ ቁርባን ኃጢአቴን አቃልልኝ።
18᎐ለመትከፍትከ
ሚካኤል ሆይ የብርሃን ልብሰ ተክኖ ለተጎናጸፈ መትከፍትህ ሰላም እላለሁ። ፈጥኖ ደራሹ መልአክ ሆይ የሰውን ልጅ ለመርዳትና ለማዳን የእግዚአብሔር ልዩ መልክተኛ ነህና። አራሽ ገበሬ ወይፈኑን በቀምበር እንዲያቀና የጠላቴን ትከሻ በመዓት ቀምበር ቅጣው። ጀርባውንም በመቅሠፍት ጅራፍ ግረፈው።
19᎐ለአክናፊከ
ሚካኤል ሆይ ለይቅርታና ለቸርነት ረበው ለሚታዩ። እሳታውያን አክናፎችህ ሰላም እላለሁ የልዑላኖች ልዑል ሆይ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽብህ የኃይል መልአክ ነህና። የረድኤትህን ኃይል ከኔ አታርቅ። ይህ ካልሆነ ግን ጠላቶቼ እሰይ እሰይ አይመስሎ መስሎ አይሆኑ ሆኖ አየነው እያሉ ይሳለቁብኛልና።
20᎐ለአክናፊከ
ሚካኤል ሆይ እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ። በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችህ ሰላም እላለሁ። የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ሆይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተህ በምትመጣበት ጊዜ ሁሉ በሲኦል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ሆይ መጣህልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።
21᎐ለአክናፊከ
ሚካኤል ሆይ የፍጥረታት ሁሉ መጠለያ ለሆኑ አክናፎችህ ሰላም እላለሁ። ክቡር የሰማያውያን ካህናት አለቃ ሆይ ከእለት እስኪት አድነን። ከጥፋትም
ሁሉ ሠውረን።
22᎐ለዘባንከ
ሚካኤል ሆይ እሳታውያን ልብሰ ተክህኖ ተጎናጽፎ ነጸብራቃዊውን ሞጣሕት ለደረበ ዘንባህ ሰላም እላለሁ። የምሕረት አማላጅ ሆይ የስንዴ አዝመራ ያይደለ በአንደበቴ በከንፈሬ ምስጋና አቀርብልሃለሁና ጥቂቱን የምስጋና እጅ መንሻ ሳታቃልል ተቀበል።
23᎐ለእንግድዓከ
ሚካኤል ሆይ የሣርና ቅጠል ተክል የዛፍ ጥላ ካለበት ያይደለ የእግዚአብሔር ቸርነት ካለበት ለማሰማራት የልዑል በጎች ምዕመናንን ለተሸከመ እንግድዓህ ሰላም እላለሁ። ሁልጊዜ በፈጣሪ ፊት የምትቆም የአምላክ ባለሟል ሆይ እኔን ባርያህን በጸሎትህ ከማሰብ አትርሳኝ። ወዳጅ ወዳጁን ይረሳ ዘንድ አይቻለውምና።
24᎐ለሕፅንከ
ሚካኤል ሆይ እግዚአብሔር ወዶ የሚቀበለውን የቅዱሳንን ጸሎት በዕቅፉ ለታቀፈ ሕፅንህ ሰላም እላለሁ። ክቡሩ መልአክ ሆይ የአእላፍ መላእክት መስፍናቸው አንተ ነህና። በችግሬ ጊዜ ትረዳኝ ዘንድ በዓየር ላይ እንደሚበር ንስር በሁለቱ ክንፎችህ እየበረርክ ድረስልኝ።
25᎐ለአፅዳዊከ
ሚካኤል ሆይ የመብረቅ መስቀል ምልክት ያለበትን በትረ ወርቅ ለጨበጡ እጆችህ ሰላም እላለሁ። ሊቀ መላእክት ሆይ በገዳመ ራማ የምትኖር የዋህ ርግብ (ዋኖስ) ወይም ዋሊያ አንተ ነህና የሕፃናት ዕድገት በነጋው በነጋው እንዲጨምር ጽድቅህ በኔ በባሪያህ ላይ ዕድገቷን ታሳይ ትግለጽ።
26᎐ለመዝራዕትከ
ሚካኤል ሆይ ባልቴቶችና ድሀ አደጎች። ተፍገምግመው እንዳይወድቁ ድጋፍ ለምትሆናቸው መዝራዕትህ ሰላም እላለሁ። ረዳቴ መልአክ ሆይ ለሰማያዊት ሀገር የሀብቷ ግምጃ ቤት አንተ ነህና። ነገ የሚሆነውን ነገር ስለማላውቅ በዛሬው ዕለት የምለምንህን ተገቢ ድርሻዬን ስጠኝ።
27᎐ለኩርናዕከ
ሚካኤል ሆይ ለነበልባላዊ እጅህ መገጣጠሚያ ለሆነው ኩርናዕህ ሰላም እላለሁ። ቅዱሱ መልአክ ሆይ የእግዚአብሔር የመልእክቱ ጉዳይ አስፈጻሚ አንተ ነህ። ከጭንቀት የተነሣ ነፍስና ሥጋዬ በታወኩ ጊዜ። ጓደኛ ጓደኛውን እንዲረዳ። እኔን ባሪያህን ትረዳኝ ዘንድ ወዳንተ እማፀናለሁ።
28᎐ለእመትከ
ሚካኤል ሆይ በመርፌና በክር የሚሰፋ ልብስ ሳይሆን። የተራዳኢነት ልብስ ፀምር እየመጠነ ለሚያጎናጽፈው ረቂቅ ክንድህ ሰላም እላለሁ። ተራዳኢው መልአክ ሆይ አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፈቃድህን ለመጠየቅ ወደአንተ ድምፄን አሰምቼ እማልዳለሁ። እኔን አገልጋይህን ተግተህ አድነኝ። ማንኛውም ሁሉ ወገኑን ለማዳን ይተጋልና።
29᎐ለእራኅከ
ሚካኤል ሆይ የማይታበለውን የቃል ኪዳን ማኅተም ለጨበጠ እጅህ መዳፍ ሰላም እላለሁ። ረቂቁ መልአክ ሆይ ነበልባላዊ በሆነ መልካም መዓዛ ባለው በጸዓዳ ዖፍ እመስልሃለሁና መዓዛው የጣፈጠ ሽቱን ቅባኝ። ብዙዎች ብዙ ለማከማቸት ይፈልጋሉ። እኔ ግን ከቸርነትህ ጥቂት ድርሻ ብቻ ነውና የምፈልገው።
30᎐ለአጻብዒከ
ሚካኤል ሆይ በትጉሃን እረኞች ትጋት የተነሣ ደቂቀ አባግዕ በበረከቱ ጊዜ መጻሕፍትን ላዘጋጁ ጣቶችህ ሰላም እላለሁ። ጠባቂው መልአክ ሆይ የነገሥታት ንጉሥ የሚሆን የእግዚአብሔር የመሥዋቱ ካህን ነህና። በምሄድበት ጎዳና በሰላም እራመድ ዘንድ። በጥበብ የበለጸጉ ጣቶች ለእግሮቼ የሕይወት ጫማን ያዘጋጁልኝ።
31᎐ለአጽፋረ እደከ
ሚካኤል ሆይ እንደ ልዝብ የራስ ወርቅ ቀጸላ። በአርእስተ አጻብዕህ ላይ ለሚያንጸባረቁ አጽፋሮችህ ሰላም እላለሁ። ፈጥኖ ደራሹ ሆይ ከወራሪ ጠላት ታድናት ዘንድ ሰውነቴ እደ ኅሊናዋን ወደአንተ ዘርግታ ትማልዳለችና። ነፍሴን የረዳትሽ መልአክ እኔ ነኝ አይዞሽ ደረስኩልሽ በላት።
32᎐ሰላም ዕብል ለዘዚአከ ገቦ
ሚካኤል ሆይ በነበልባላዊ ክንፍ ለተከበበው መልአካዊ ጎንህ ሰላም እላለሁ። ክቡሩ መልአክ ሆይ ክብርህ ተነግሮ የማያልቅ ዕፁብ ድንቅ ነው እኔ አገልጋይህ ከምስጋናህ ምንጭ ጠጥቼ እረካ ዘንድ። በጥላህ ሥር ተጠልዬ መኖርን እፈቅዳለሁ።
33 ለከርሥከ
ሚካኤል ሆይ እንደማይጎድል የምንጭ ውሃ ቀና መንፈስ ለተከማቸበት ሆድህ ሰላም እላለሁ። ሰማያዊ ካህን ሆይ በሰባተኛው ሰማይ የመሠዊያ አዳራሽ ቆመህ በጸሎትህ ኃጢአቴን ታስተሠርይ ዘንድ እኔ አገልጋይህ ካህኑ ሚካኤል እያልኩ እማልድሃለሁ።
34᎐ለልብከ
ሚካኤል ሆይ ቂም በቀል የሌለበት የርኅራኄና የየዋሃት መዝገብ ለሆነ ልቡናህ ሰላም እላለሁ። የሰማያውያን ኃይላት አለቃ ሚካኤል ሆይ የእሥራኤልን ልጆች ባሕሩን ከፍለህ በባሕር መካከል እንዳሳለፍካቸው እኔንም አገልጋይህን ከሥውር ወጥመድ ሠውረህ በሰላም አሳልፈኝ።
35᎐ለኩልያቲከ
ሚካኤል ሆይ በውሳጤ ገበዋት አማክሎ አስተካክሎ እግዚአብሔር ለፈጠረው ለማይዳሰሰው ኩልያትህ ሰላም እላለሁ። ኃያሉ መልአክ ሆይ ኃይልህን የሰው ኃይል ሊተካከለው አይችልምና። እንግደለው እናጥፋው የሚሉትን ጠላቶቼን ጽጋግ በቀላቀለ ዓውሎ ንፋስ በታትነህ ከገጸ ምድር አጥፋቸው።
36᎐ለኅሊናከ
ሚካኤል ሆይ ከይቅርታና ምሕረት ብቻ በተቀር። ጥፋትንና ተንኮልን ለማያስብ ኅሊናህ ሰላም እላለሁ። ፈጣኑ መልአክ ሆይ አስቀድሞ የተጣላህን በቀል ባለመርሳት ጋሻህን አንሣ። ነበልባላዊ ሰይፍህንም በጠላቴ በዲያብሎስ ላይ መዘህ ተነሣሣበት።
37᎐ለንዋየ ውስጥከ
ሚካኤል ሆይ መጎናጸፊያው ነበልባላዊ ሕዋሰ ከርሥህ ለሆነ ንዋየ ውስጥህ ሰላም እላለሁ። ክቡሩ መልአክ ሆይ የእግዚአብሔር የትእዛዙ አስተላላፊ አዋጅ ነጋሪ አንተ ነህ እኮን። እኔን አገልጋይህን ከሞተ ኃጢአት አድነኝ። ያለመጠራጠር አንተን ያመነ ሁሉ የፈለገውን ሳያገኝ ተስፋ በመቁረጥ አዝኖ ተክዞ የሄደ የለምና።
38᎐ለሕንብርትከ
ሚካኤል ሆይ መብረቅ የተዋሃደው ረቂቅ የሆነ ለማይዳሰስ ሕንብርትህ ሰላም እላለሁ። ለጋሡ መልአክ ሆይ በነጋ በጠባ ትኩስ መናን በማዝነም የእሥራኤልን ልጆች በበረኃ እንደመገብካቸው እኔንም ባሪያህን ዕውነተኛውን ኅብስተ ሕይወት መግበኝ።
39᎐ለሐቌከ
ሚካኤል ሆይ መብረቅን በተመላ የነጸብራቅ ዝናር ለታጠቀ ወገብህ ሰላም እላለሁ። ታጋሹ መልአክ ሆይ ከመአት የራቅህ የምሕረት አማላጅ ነህና ከሥነ ገጽህ ነጸብራቅ ጥቂት ብልጭ አድርግና የነፍሴን የብርድ ቅዝቃዜ በላቦቱ ሞቅ አድርግላት።
40᎐ለአቁያጺከ
ሚካኤል ሆይ ጠቢበ ጠቢባን የተባለ አምላክ በወርቅ ዙፋን ላይ እንደ አምድ አስተካክሎ ያቆማቸው አጽንኖ አድንኖ ለሌለባቸው አቁያጽህ ሰላም እላለሁ። የሕይወት ጎዳና መሪ ሆይ እሥራኤልን በባሕር መካከል መንገድ ጠርገህ (ከፍተህ) ያሳለፍክ አንተ ነህና ከባዱን የኃጢአት ሸክም ከላዬ ታወርድልኝ ዘንድ በክንፍህ እየበረርክ ድረስልኝ።
41᎐ለአብራኪከ
ሚካኤል ሆይ የሰውን ልጅ ኃጢአት ስለማስተሥረይ ወደ ፈጣሪ በሰጊድ ለሚማልዱ አብራክህ ሰላም እላለሁ። የሁሉ ጠባቂ ሆይ በባሕርዩ ባለ ጥበብ ዓለምን የፈጠረ የእግዚአብሔር ልዩ መልክተኛ ነህና የራኄልንና የልያን ልጆች ከነሱ ባለመለየት ለዓርባ ዘመን እንደጠበቅሃቸው እኔን አገልጋይህን በጠላቶቼ እንዳልበዘበዝ ከኔ ሳትለይ ጠብቀኝ።
42᎐ለአእጋሪከ
ሚካኤል ሆይ የተገፉትን የተከፉትን ለመጎብኘት በነፋስ ሠረገላ ለሚሮጡ እግሮችህ ሰላም እላለሁ። ቅንነት ያለህ መልአክ ሆይ ከዓመፃ ከተንኮል ንጹሐ ልብ የዋህ ነህና እግሮቼን ከስህተት ጎዳና ጠብቀህ ወደ ጽድቅ ጎዳና መርተኸኝ። የሕይወትን ፍሬ ለመብላት አብቃኝ።
43᎐ለሰኳንዊከ
ሚካኤል ሆይ በስሕተት ጎዳና ለማይጓዙ ሁለቱ ሰኳንዊህ ሰላም እላለሁ። ቀልጣፋው መልአክ ሆይ ሥጋዊ ደማዊን ፍጡር ለመርዳት ፈጣን ነህና የሕይወቴን ተረፍ ተንከባክቤ እኖርባት ዘንድ። በቸርነትህ ጥላ ሥር አስቀምጠህ ጠብቀኝ።
44᎐ለመከየድከ
ሚካኤል ሆይ የሕይወትን የእሳት ግለት ለተጫማ መከየድህ ሰላም እላለሁ። ዋነተኛው መልአክ ሆይ ባሕረ እሳትን እየቀዘፍክ ማዕበሉን ጸጥ በማድረግ። ነፍሳትን የምታሻግር አንተ ነህና። መልካሙን ድምጽህን ለመስማት ጆሮውን ትከፍትለት ዘንድ። በጥቡዕ ልቡና ሆኖ የሚለምንህን ሁሉ ዕዝነ ልቡናውን ክፈትለት።
45᎐ለአጸብዒከ
ሚካኤል ሆይ ተፈጥሮአቸው ከነደ እሳት ለሆነ ጣቶችህ ሰላም እላለሁ። ኃያሉ መልአክ ሆይ ኃይል ሰማያዊን የተቀዳጀህ ነህና በፍጹም ረድኤትህ ከጥፋት እድን ዘንድ። ከቀድሞ ጀምሮ ከነበረ ከቅጽረ ጸሎትህ ሰውነቴን አስጠጋለሁ። አንተን የተጠጋ ደካማም ቢሆን ብርቱ ጽኑዕ በሚሆን ኃይልህ ይድናልና።
46᎐ለአጽፋረ እግርከ
ሚካኤል ሆይ የሰውን ልጅ ለመርዳት በእርዳታ ጎዳና በሚፋጠኑበት ጊዜ ዕቅፍተ ዕብን ለማያደናቅፋቸው ለእግርህ አጽፋር ሰላም እላለሁ። ትጉሁ መልአክ ሆይ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ለሚሆን አምላክ አርምሞ ጽርዓት ሳይኖርብህ ምስጋና ታቀርባለህ። ስለዚህም በዚህ ዓለም በምኖርበት ጊዜ ሁሉ እምነቴ በአንተ ላይ ስለሆነ ቸል አትበለኝ። ከሰው ወገን ማንም ቢሆን ወገኑን ቸል አይልምና።
47᎐ለቆምከ
ሚካኤል ሆይ በጽርሐ አርያም አደባባይ እንደዝግባ ዛፍ ለምልሞ ለሚታይ አካለ ቆሞህ ሰላም እላለሁ። ርኅሩሁ መልአክ ሆይ ሰማያዊ ርግበ ገነት አንተ ነህና። ከኃጢአት በረኃ ዋዕይ መጠለያ ይሆኑኝ ዘንድ ሁለቱ ክንፎችህን እንደ ድባብ በኔ ላይ ዘርጋቸው።
48᎐ለመልክአቲከ
ሚካኤል ሆይ በየስማቸው በየአንጻራቸው ጸንተው ለሚገኙ ለመልክእህ ባሕርያት ሰላም እላለሁ። ብርሃናዊው መልአክ ሆይ በልብሰ ብርሃን የተጌጥህ የተሸለምክ እንደመሆንህ። በዘመኑ ሁሉ ወዳጅነትህ እጅግ ጠቃሚ ነው። የወዳጅን ኃጢአት ለማስተሥረይ የታመንክ የነፍስ ወዳጅ ነህና።
49᎐ለመልክእከ በአምኆ
ሚካኤል ሆይ ለእግዚአብሔር በመስገድና ከፍ ባለ ድምጽ በማመስገን ለመልክእህ ሰላም እላለሁ የምሕረት አማላጅ ሆይ ቸርነት የዋህነት ልማድህ ነውና። ጠላት በመንገድ ሸምቆ እንዳያስደነግጠኝ ሰይፍህን መዘህ ተገለጥና በርግጎ ገደል ይግባ።
50᎐ለመልክእከ
ሚካኤል ሆይ በአራቱ ማዕርገ ኆኅት እንደ ተመለከትነው በዓይን ታይቶ ለማይመረመር መልክእህ ሰላም እላለሁ። የዋሁ ሚካኤል ሆይ በየዋህነትህ በንጽሐ ጠባይህ የማርያም ወንድም ተብለሃልና። በአምሳለ ክንፈ ርግብ በተመሰሉ ክንፎችህ አቅፈህ ከሞት ወደ ሕይወት ጎዳና ምራኝ።
51᎐አምኃ ሰላም አቀረብኩ
ሚካኤል ሆይ ለእያንዳንዱ በየክፍሉ ለተነገሩ መልኮችህ ሁሉ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርባለሁ። ልዑሉ መልአክ ሆይ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽብህ ኃያል መልአክ ነህና የምስጋናዬን እጅ መንሻ ተቀብለህ። ከላይ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት የጸሎቴን ዋጋ እጥፍ ድርብ አድርገህ ላክልኝ።
52᎐ኦ ሚካኤል ሚካኤል
አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ እኮን። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ እኮን። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና። በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።
53᎐ሰላም ለከ ሚካኤል
የተጨነቀውን የተጨቆነውን ነፃ የምታወጣው መልአክ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን ሠራተኛው ሠርቶ እንዲበላ ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን።
54᎐ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አዳኝነትህን በማመን የለመነህን ሁሉ በክንፈ ረድኤትህ የምትሰውረው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን።
55᎐በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን የሚንፈራገጠውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው ሚካኤል ሆይ አንገትህን ዘንበል ቀለስ አድርገህ በፈጣሪህ ፊት ሰግደህ እኛን ባሮቹን በቸርነቱ ይጎበኘን ዘንድ የማናዊት እጁን ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ ለምን አማልድ ለዘለዓለሙ አሜን።
56᎐አቤቱ የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ሆይ በአርአያህ በአምሣልህ የፈጠርከን ሕዝቦችህን ሁሉ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውረን ለዘላለሙ አሜን።
አቡነ ዘበሰማያት።
=====//=====
እንኳን ለኃያሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በተለያዩ መዘምራን የተዘመሩ #የቅዱስ_ሚካኤል የምስጋና መዝሙሮች ለአንድ ሰዓት ያህል #ያለ_ማቋረጥ ያዳምጡ ነፍስዎትን ያስደስቱ! የመልአኩ በረከት:ጥበቃና ተረዳኢነት አይለየን አሜን
ቅድስና በእብራይስጥ 'ቅዱስ' በግሪክ ቋንቋ 'ሐጋዮስ' ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ለእግዚአብሔር ክብር እና አገልግሎት የተለየ ማለት ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ አኳያ አንድ ስጋውን፣ መንፈሱን እና ነፍሱን ከሚያረክስ ሃጢአት መበራቅ እና በመነጠል ራሱን ለእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው ዕብ 1214 1ጴጥ 115 2ዜና 29
የቅድስና ምንነት
1.
ቅድስና የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው 1ተሰ 43
2.
ቅድስና የእግዚአብሔር አንዱ ባሕሪው ነው 1 ጴጥ 115 1ሳሙ 22
3.
ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚሆን ነው ዘፀ 2836
4.
ቅድስና ለአንድ ለታወቀ አላማና ግብ ላለው ሕይወት መለየት ነው 2ዜና 295
5.
ቅድስና ከእግዚአብሔር አንድ የመጣና ለተቀዳሹ በረከት የሚሆን ስጦታ ነው
6.
ቅድስና ሶስት መሰረታዊ ትርጉሞች አሉት
. መለየት - ይህም ከሃጢአት፣ ከራስ ምኞት እና ከሰይጣን አሰራር ኢሳ 5211-12
. መሰጠት - ለእግዚአብሔር ብቻ ራስን መስጠት 2ዜና 295
. ንጽህና - ከሃጢአት እና ከሚያረክሱ ነገሮች ንጽህ መሆን ዘፃ 910

የቅድስና ደረጃዎች
1.
የመዳንን ደረጃ የሚያስገኝ ቅድስና 1ቆሮ 611
2.
ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል የተደረገ ፈጣን የመቀደስ (መለየት፣ መሰጠት፣ ንጽህና) ስራ ነው - 1ቆሮ 12 ኤፌ 11 ቆላ 12 ዕብ 1010 ይሁዳ 3
3.
አማኞች ቅዱሳን ተብለው ተጠርተዋል። ምንም እንኳን በስጋ ቢኖሩም ቅድስና አግኝተዋል 1ቆሮ 33 611 2ተሰ 213 ሮሜ 829
4.
የሚያድግ ቅድስና (progressive sanctification)
. በቅድስና ሕይወት ተጠብቆ መኖር ዕብ 1214
. የቅድስናን ፍሬ በማፍራት መኖር መዝ 13218
. ቅድስናን ፍጹም ለማድረግ ራስን ከሚያረክስ ነገር በማንፃት መኖር 2ቆሮ 71
. ዘወትር ራስን ለእግዚአብሔር በመስጠት መኖር ሮሜ 813 1ጴጥ 122
5.
ፍጹም እንከን የሌለበት ቅድስና (complete sanctification)
ይህ አይነቱ ቅድስና የሚገኘው ምድራዊ የሆነውን የሰውነት መኖሪያ ለቀን ሰማያዊ አካል በምንለብስበት ጊዜ ነው 1ዮሐ 32 ዕብ 1223 1ተሰ 313
በቅድስና የማደጊያ መንገዶች፦
1.
የእግዚአብሔር ቃል
. ቃሉን በማጥናት ዮሐ 177-9 ኤፌ 526 ያዕ 121-25
. ቃሉን ከሚያውቁ አገልጋዮች ስር ሆኖ በመማር ኤፌ 411-13 ገላ 66 ዕብ 137 ይኸውም ቃሉን ቀሚያብራራልን ከመንፈስ ቅዱስና የቃሉ እውቀት ካላቸው አገልጋዮች ስር ሆኖ በመማር 1ዮሐ 19
2.
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ዕብ 1312 1ዮሐ 19
3.
የእግዚአብሔር መንፈስ ሮሜ 82-13 ገላ 522 1ቆሮ 611
4.
የእግዚአብሔር አባታዊ ቅጣት ዕብ 129-11
የቅድስና አቅጣጫዎች
1.
በሁለንተና (በስጋ፣ በነፍስ፣ በመንፈስ) 1ተሰ 523
2.
በኑሮ ሁሉ 1ጴጥ 115-16
የቅድስና በረከቶች
1.
እግዚአብሔርን በክብሩ ማየት ዕብ 1214
2.
የተስፋውን በረከት መውረስ ኢያ 35
3.
የድል ሕይወት መኖር ኢያ 710-13
እግዚአብሔር አምላካችን ከአማልክት እና ከማንኛውም ክፉ ነገር ሁሉ የተለየ በመሆኑ፣ ቅዱስ በመሆኑ በእርሱ የእርሱ የተለዩ ሰዎችም ሁሉ ቅዱሳን ይባላሉ። ሰው በክርስቶስ ስራ አምኖ አማኝ ሲሆን ቅዱስ ይሆናል፤ ይባላልም። ከዚህ በሕይወቱ ሁሉ በቅድስና ያድጋል። በክርስቶስ ዳግም መምጣት ቅድስናው ፍጹም ይሆናል።
0

Like



404. That’s an error. 
The requested URL /u/0/se/0/_/+1/fastbutton was not found on this server. That’s all we know. 

Share



     
0
Tags:






እጃችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ" (፪ዜና ፴፥፰)

ከሰንበት //መምሪያ ድረ ገጽ የተገኘ
ከዶ/ አምሳሉ ተፈራ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፊሎሎጂ ዲፓርትመንት
ረዳት ፕሮፊሰር
ለሁሉ ፈጣሪ ለእግዚአብሔር ራስን መቀደስና ከኃጢአት መለየት ለሰው ሁሉ የቀረበ ጥሪ ነው። ይህን ዘንግተው የነበሩ ሕዝበ እስራኤል ወደ አምላካቸው እንዲመለሱና ሁለንተናቸውን ለእርሱ እንዲሰጡ የተላከላቸው መልእክት ነው ርእሳችን እኛንም ይመለከታልና እንደሚከተለው በዝርዝር እንየው።
የሚታየውንም የማይታየውንም የፈጠረ፣ በባሕርም በየብስም ያሉትን ያስገኘ፣ ሰውን ለክብሩ ወራሽነትና ለስሙ ቀዳሽነት የወሰነ፣ ዓለምን ሲፈጥር አማካሪ ያልፈለገ፣ ፍጡሩን በመመገብና በመውደድ ወደር የሌለው፣ ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ የሰጠ ነው ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር። ይህን ጌታ በምንም ልንለውጠውና ልንተካው አንችልም። አምላክ ነውና ተወዳዳሪ የለውም (ኢሳ፵፣ ፲፪ - ፲፬)
የርእሳችን መነሻ የሆነው «እጃችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ» የሚለው ትምህርት የተሰጠው፣ ሃያ ዘጠኝ ዓመታት በእስራኤል ላይ በነገሠው ንጉሥ ሕዝቅያስ ነው። ምክንያቱ ደግሞ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማድረግ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትን ይመለከታል። እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ስለሆነ፤ ወደ እርሱ መቅረብና ማገልገል የሚቻለው በንጽሕና ሆኖ ነው፤ አገልግሎትንም የሚቀበለው ያለቸልታ በትጋት ሲሆን ነው። «ልጆቼ ሆይ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ፤ ብሎ ያዘዘን ለዚህ ነው (፪ዜና፳፱፣፲፩)
«ንጉሡ ሕዝቅያስ ለእግዚአብሔር ፋሲካ እንዲደረግ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ለዐሥራ ሁለቱም ነገደ እስራኤል መልእክት ላከ። ነገር ግን ካህናቱ ገና በሚገባ ስላልተቀደሱ፣ ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ተጠቃለው ስላልተሰበሰቡ፤ ፋሲካው በደንብ ሲዘጋጁ በቀጣዩ ወር እንዲከበር ተወሰነ። ለቀጣዩ ወር ግን ሁሉም ከያለበት ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እንዲሰባሰብ እንዲህ የሚል ዐዋጅ ተነገረ፣ «የእስራኤል ልጆች ሆይ ... እግዚአብሔርን እንደ በደሉ እንደ አባቶቻችሁና እንደ ወንድሞቻችሁ አትሁኑ። አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ለዘላለም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፤ ጽኑ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ። (፪ዜና ፴፣፯-)
እስራኤላውያን ከያሉበት ተሰባስበው በኢየሩሳሌም እንዲያከብሯቸው ከታዘዙት አንዱና ዋናው በዓል የፋሲካ ወይም የቂጣ ነው። በእግዚአብሔር ቸርነት ከግብጽ ባርነት የወጡበትን ሁኔታ ይዘክሩበታል። ይህም በኒሳን ፲፬ ቀን (በእኛ ሚያዚያ ወርየሚከበር ሲሆን፤ በዓሉም ለሰባት ቀናት ይዘልቃል። ለዚህ ነው ይህን ታላቅ በዓል ሲያከብሩ በተለየ መልኩ ራሳቸውን መቀደስና እጃቸውንም ለፈጣሪ መስጠት የሚጠበቅባቸው። ይህ ታሪክ ለእኛ ምን ያስተምረናልይህንንም እንደሚከተለው እንመልከት፤
ለመሆኑ እጅን መስጠት ምንን ያሳያልእጅን መስጠት መማረክን፣ መሸነፍንና በሌላ ነገር አለመወሰድን ወዘተ... ያመለክታል። ሁኔታው ሁለንተናን እና አጠቃላይ ማንነትንም ይመለከታል። እጅን መስጠት የሰላምም ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። ለእግዚአብሔር እጅን መስጠት ለምን ሲባልምሰው እጁን ከሰጠ ሐሳቡም፣ ተግባሩም፣ እንቅስቃሴውም ወዘተ... ወደዚያው ነው የሚጠቃለለው። የፈጠረን፣ የሚያኖረን፣ የሚያዝንልን ሁሉ እርሱ ነውና እኛም ሲቸግረን ለማግኘት፣ ሲጎድለን እንዲሞላልን፣ ስንወድቅ እንዲያነሣን እጃችንን በመስጠት ወደ እግዚአብሔር እንጮኻለን።  «ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል፤ እጅን ለእግዚአብሔር የመስጠት ምልክቶችን ቀጥሎ እንመለከታለን። ቀዳሚው ራስን መቀደስና ከኃጢአት መጠበቅ ነው። ያኔ ሕዝቅያስ ለእስራኤላውያኑ ያወጀላቸው ካህናቱ ራሳቸውን በሚገባ እንዲቀድሱ፣ ሕዝቡም ከኃጢአት ተጠብቀው ፋሲካውን በንጽሕና እንዲያከብሩ ነው። የእግዚአብሔርን ፋሲካ ከኃጢአት ሳይነጹ ማክበር አይገባምና ለዚህ ቀን ተሰጥቷቸዋል። በዚያም መሠረት ሁሉም እንደሚገባ ተከናውኗል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ሁሉም እጅግ ተቀድሰው ነበርና የፋሲካው በዓል ለተጨማሪ ሰባት ቀናት በደስታ ተከበረ፤ ይህም ከሰሎሞን ዘመን ወዲህ የመጀመሪያው በዓል እንደሆነ ተመዝግቧል፤ (፪ዜና፴፣፳፬-፳፮) ዛሬም ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ሁሉ የሚወደድልን አብዝተን ስንቀደስና እጃችንን ለእርሱ ብቻ ስንሰጥ ነው። በዓላትን ስናከብር፣ ወደ ቅዱሳት መካናት ስንጓዝ፣ ለመንፈሳዊ ሥራ ስንሰማራ ወዘተ... ምን ያህል መንፈሳዊ ዝግጅት እናደርጋለንለወረት ያህል ጀምረን የተውናቸው ስንቶች ናቸውበመንፈስ ጀምረን በሥጋ የምንቋጫቸው ምን ያህል ይሆኑአንዴ መንፈሳዊ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሥጋዊ መሆን የሚያምረን ስንቶቻችን ነንበአንዱ እጃችን እግዚአብሔርን በሌላኛው ደግሞ ዓለምን የምንጨብጥ ከሆነ አንዱም አይሳካም። ስለዚህ ለፈጣሪያችን እኛነታችንን በመላ ነው ማስረከብ ያለብን። ከእርሱ ቀንሰን ለባእድ የምንሰጠው በፍጹም ሊኖር አይገባም።

ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችንን በተለይም ወጣቶችን እየተፈታተነን ያለው የምንቆምበትን ቦታ አለማወቅ ነው። ሁሉም ነገር ያምረናል። ባየነው ነገር ሁሉ እንማረክና በቀላሉ እጃችንን እንሰጣለን። ይህ ዓለም የውጊያ ዐውድ ነው። በቀረበልን ሁሉ የምንማረክና እጅ የምንሰጥ ከሆነ ግን ዓላማችንን ስተናል። ጌታችን የዓለምን ፈተና ድል ያደረገልን እኛም በአሸናፊነት መንገድ እንድንጓዝ ሲያጠይቀን ነው (ዮሐ፲፮፣ ፴፫) ስለዚህ ለሕይወት ፈተና እጅ እንዳንሰጥ፤ ለዓላማቢስነት እጅ እንዳንሰጥ፤ ለዝሙትና ርኩሰት እጅ እንዳንሰጥ፤ ለስሜታዊነት እጅ እንዳንሰጥ ወዘተ... መወሰን አለብን። እጅ መስጠት ለአምላክችን ለእርሱ ብቻ ይሁን።
ሁለተኛው ለአምላካችን እጅ የመስጠታችን ዐቢይ መገለጫ የእርሱን ፈቃድ ብቻ ስናደርግ ነው። በሕይወት ጉዞአችን ውስጥ ለሥጋዊ ፈቃድ ስኬት ብቻ ከሮጥን ትርፉ ድካም ብቻ ነው። የራስ ፈቃድ፣ የቤተሰብ ፍላጎት፣ የአለቃ ትእዛዝ፣ የባሕላችን ተጽእኖ፣ የአካባቢያችን ሁኔታ ወዘተ ... ዓይነቱና ኅብሩ ብዙ ነው። ይህን ሁሉ እናሟላለን ብለን ብንሞክርም ዓለም አትሞላምና /በዚያውም ላይ ዕድሜ ካልቀደመንበፍጹም አይሳካልንም። ስለዚህ ውጤቱ በኑሮ አለመርካት፣ ብጥብጥ፣ ተስፋ መቁረጥና የመሰለው ነው። ያንዱን ፈቃድ ትተን ሌላውን እንፈጽም ብንልም ውጤቱ አጉል ይሆናል። ነገር ግን የደጉ አምላካችንን ፈቃድ ብንከተል ለቀሪው ችግራችንና ምስቅልቅል ሕይወታችን መፍትሔ ነው። አንዱን የእግዚአብሔር ፈቃድ ስንፈጽም ሌላውን ያቃናልናል። በጀመርነው ጥቂት ነገር ብዙ በረከት ይሰጠናል። ይህን እውነት ሲመሰክር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል፤ «የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ይልቁንም ወጣቶች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ልባችንን ሰበር ማደረግ ይገባናል። የእርሱ ፈቃድ ሁል ጊዜ በጎና መልካም ነው። ፈቃዱን እንዴት ልወቀውብንል ዳዊት ምላሹን ይሰጠናል።
(መዝ፳፣፬፤ ፵፣፰፤ ፻፵፫፣፲እንመልከት።
ሦስተኛው መንገድ ወደ ቤቱ መምጣት ነው። የሚቀርቡልን ብዙ አማራጮች ጊዜያዊ ደስታን ብቻ የሚሰጡ ናቸውና አብረው አይዘልቁም። እንዲያውም ጸጸትና ቁጭት ያስከትላሉ። በእግዚአብሔር ቤት በቤተ ክርስቲያን መተከል ግን ድርብርብ መልካም ፍሬን ያስገኛል። ሰላም፣ ደግነት፣ ርኅራኄና ይቅርታ ወዘተ... ከቤተ እግዚአብሔር እንጂ ከዓለማዊ ቦታ (ማለትም መጠጥ ቤት፣ ዝሙት ቤት፣ ጥንቆላ ቤት፣ ወዘተ ) አይደለም። በኃጢአት ብንወድቅ በንስሐ፥ ራስን በመውደድ ብንሰቃይ ስለ ሌላው በማሰብ፥ በስርቆት ብንገኝ የራስንም መስጠትን ወዘተ... የምንማርባት ናት ቤተ ክርስቲያን። ስለዚህ በዓለም ካሉ መጠጊያዎች አብልጠን ራሳችንን የምናስጠጋባትና ለእሷም ብቻ እጃችንን ልንሰጥ የሚገባ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት። ክቡር ዳዊት «ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወዳለች፣ ትናፍቅማለች... ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች። በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ በማለት በቤተ እግዚአብሔር መኖር ያለውን ጠቀሜታ ያሳያል (መዝ፹፫፣ -)
ሌላው መመለስ ያለበት ጥያቄ እጃችንን ለእግዚአብሔር መስጠት ምን ምን ያስገኛልየሚለው ነው። አንድ ነገር ጥቅም ካልሰጠ መከወኑ ፋይዳ ቢስ ነው። ከዚህ አንጻር የተነሣንበትን ርእስ ስናየው፤ ምላሹንም እዚያው ምዕራፍ ላይ በቀጣዩ ቁጥር እናገኛዋለን። እንዲህ ይላል «አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነውና፥ ወደ እርሱም ብትመለሱ ፊቱን ከእናንተ አያዞርም። ... ልጆቻችሁ ... ምሕረትን ያገኛሉ። ደግሞም ወደዚህች ምድር ይመለሳሉ።» (፪ዜና፴፣፱) እጃችንን ለፈጣሪያችን ከሰጠንና መንገዳችን ከመንገዱ አንድ ከሆነ እርሱ በምሕረት ዐይኑ ይመለከተናል፤ በረከቱም ለልጅ ልጆቻችን ይተርፋል። የምንጓጓለት ሁሉ የሚሰጠን ቅድሚያ ራሳችንን ለእርሱ ስንሰጥ ነው። በፊቱ ሞገስ የምናገኘው ወለም ዘለም ሳንል ስናመልከው ነው። ወደርስት ቦታችን መንግሥተ ሰማያት የሚመልሰን፤ እንዲሁም የምንናፍቀውን ሕይወት የሚሰጠን በሐሳብም በተግባርም ለእግዚአብሔር ብቻ ስንገዛ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችንን ብቻ በማምለክና ለእርሱም እጃችንን በመስጠት ሕይወታችንን እንምራ። ወደእርሱ ከተጠጋን ፈጽሞ አይጥለንም። በነቢዩ አድሮ እንዲህ ብሎናልና፤ «አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።(ኢሳይያስ ፵፩፣ ) ለእርሱ ብቻ ታምነን እጃችንን እንድንሰጥ እርሱ ይርዳን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!
 ከሰንበት //መምሪያ ድረ ገጽ የተገኘ




No comments:

Post a Comment