Saturday 28 December 2019

በሰሜን አሜሪካና በአካባቢዋ ለምትገኙ አብያተ ክርስቲያናት





የቀናተኛን ሰው እንጀራ አትብላ ጣፋጭ መብልም አይመርህ በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና ብላ ጠጣ ይልሃል ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም ( ምሣሌ 23 ፥ 6 እና 7 )





ወተት አጠጥቶ መግደልም ሆነ መገደል  እንጀራ ቆርሶ አሳልፎ መስጠትም ሆነ መሰጠት አለና ክርስትና አብሮ በበላሽም ሆነ አብሮ በጠጣሽ አለመሆኑን ብንማርና ብንረዳ ፣ እንደገናም በአንድነት እንጀራ መቁረስ መጽሐፍቅዱሳዊና አንድ ልብንም ሆነ ጥሩ ልብን የሚጠይቅ ሆኖ የሚበረታታ ቢሆንም ምናልባትም ከላይ እንደገለጥኩት አሁንም ሰዎች በልዩ ልዩ ጉዳዮቻቸው የተለየውን ዓላማቸውንና ተልዕኮአቸውን ሊፈጽሙ ይህንን መንገድ ይጠቀሙበትና በዚሁ ጉዳይ ሰዎችን የሚጎዱበት ፣ እግዚአብሔርም የሚያዝንበት ቢሆንስ እላለሁ :: እንደገናም በሰሜን አሜሪካ ላለን ሰዎች አሁንም እንጀራውንም ሆነ ክትፎውን ማዘጋጀት እንደ ሀገር ቤቱ ሕዝባችን ብዙም ዳገት ስለማይሆንብን ድሆችን ከማሰብና ለሌሎችም ከማካፈል ጋራ ሲሆን እንጂ አብሮ ተሰባስቦ ስለተበላ ብቻ የተዋጣላቸው መንፈሳውያን ናቸው የሚያስብለን አይሆንምና  እናስብበት የሚል መልዕክትም አለኝ ከዚህ በመቀጠል ለሀሳቤ መነሻ ጥቅሶች የሆኑኝን የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች አስቀምጣለሁና መጽሐፍዎን ከፍተው ያንብቡ ( መጽሐፈ መሣፍንት 5 ፥ 24 - 31 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 13 ፥ 21 - 30 ፤ የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 41 - 47 ፤ የሉቃስ ወንጌል 7 ፥ 36 - 50 ፤ ምሣሌ 23 ፥ 6 እና 7 ፤ ሮሜ 14 ፥ 5  - 23 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 31 - 33 ፤ ገላትያ 2 ፥ 10 ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6 ፥ 17  - 20 ፤ ዕብራውያን 13 ፥ 16  ) ተባረኩ



አባ ዮናስ ሐዋርያዊ አገልጋይ

No comments:

Post a Comment