Saturday 28 December 2019

[ኦ አምላኬ አስደንጋጩ ሚስጥር ይፋ ሆነ] በእስራኤል ዳንሳ ገስት ሃውስ ውስጥ የሞቱ የ4 ሰዎችን አስክሬን ገንዣለሁ የሐዋርያነትንና የፓስተርነትን ስም ለብሰው ጉድ ያፈሉ ነጭ ዱርዬዎች አሳፋሪው ገበና የተጋለጠበት ይህችን ነጭ ዱርዬዎች የምትለዋን አባባል ያገኘሁት ወይዘሮ መዓዛና የተወደደው ወንድማችን አርቲስት ዳዊት ወልደ ዮሐንስ በየኔታ ቲዩብ ከሰጡት ኢንተርቪው ውስጥ ነው በመሆኑም ይህቺ ነጭ ዱርዬዎች የምትለዋ ቃል በነ እስራኤል ዳንሳ ሠፈር ብቻ ሳይሆን በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሁሉ ገቢራዊ ድርጊትን በመፈጸም ዓይን አውጥታና ፍጥጥ ብላ የሌባ ዓይነ ደረቅ ወይንም ዓይኔን ግንባር ያርገው የሚለውንም ስያሜ ተቀጽላ አድርጋ ያለ ፍርሃትና ያለ ይሉኝታ የምትኖር በመሆንዋ እጅግ በጣም የወደድኩዋት እና የተመቸችኝ የቃል ገለጣ ናት በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጉድ ወደ አደባባይ ብቅ ያደረጉልንን የየኔታ ቲዩብ ፕሮግራም አዘጋጅንም ሆነ ወይዘሮ መዓዛንና አርቲስት ዳዊት ወልደ ዮሐንስን ተባረኩ ዛሬም በዘመናችን እንደ እነዚህ ያሉ አስመሳይ አካኖችንም እንዲህ በማጋለጥ ነቢዩ ናታን ዳዊትን እንዳለው እናንተም እንዲህ በግላጭ በሚዲያ ያ ሰው አንተ ነህ ማለትን አታቁሙ እላለሁ መጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 7 በሙሉ ፤ 2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 12 በሙሉ ይነበብ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው አለ እንጂ ሲያጭበረብሩ ሲያታልሉ ሲዘርፉና ሲበዘብዙ ሲዋሹ ሲያስፈራሩም የሚያገኛቸው ብጹአን ናቸው አላለንም እስቲ መጽሐፉ የሚለውን አስተውለን እንመልከት የሉቃስ ወንጌል 12 ፥ 32 _ 48 ታድያ ይሄ ነገር እንዳይወጣባቸው መሣይ እስራኤል ዳንሳዎች ከጀሌዎቻቸው ጋር በመሆን እናንተን እንዳስፈራሩ እኛንም ከማስፈራራት አልቦዘኑም ከዚህ የተነሳ እኛም እንደ እናንተ እያለቀስን እንባችንንም ወደ ሰማይ እየረጨን ፍርዱን ለጌታ ሰጥተን ቁጭ ብለናል ይሁን እንጂ መስፈራራቱን ዛቻውንም ሆነ ግልምጫውን ችለን ስለ እውነት በተገፋንበት ጠባቡ ክፍላችን እውነቱ ይሰማ እያልን እና እየጮህን ነው መጽሐፋችንም እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት የሚል ቃል ነውና ያስነበበን ጫናው ቢኖርም እውነቱን ግን አንለውጠውም የተወደዳችሁ ወገኖች እነዚህ ወገኖች ኢንተርቪው ያደረጉበትን ሊንክ ከዚሁ ጽሑፌ ጋር አያይዤ አስቀምጠዋለሁ መስማትም ሆነ መከታተል ትችላላችሁ ተባረኩ https://youtu.be/dL0wgKv45XA

No comments:

Post a Comment