Monday 2 July 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 10 ) ክፍል አራት ተስፋችን ማነው ? ድንግል ማርያም ወይስ ክርስቶስ ? የቅዳሴ ማርያም ደራሲ እንዲህ አለን ፦ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት ትርጉም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ( ምንጭ ቅዳሴ ማርያም ) መጽሐፍቅዱሳችንስ ምን አለን ፦ «እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፥ አለበሳቸውም »… አዳምንም አስወጣው፥ «ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ » ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ ( ኦሪት ዘፍጥረት 3 ፥ 21 ፣ 24 ) ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ ( ሮሜ 13 ፥ 14 ) ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና ( ገላትያ 3 ፥ 27 ) የተወደዳችሁ ወገኖች ከነዚህ ጥቅሶች በመነሳት እንግዲህ በዚህ ዓለም ተስፋ ያጣና ያለክርስቶስ በመሆኑ ምክንያት ከእግዚአብሔር እንደተለየ የተገነዘበና የሚሰማው ሁሉ በክርስቶስ ደም ሰላም የተመሠረተ ከመሆኑ የተነሳ አንድን አዲስ ሰው በመፍጠር ሰላም ይደረግ ዘንድ የጥሉ ግድግዳ ፈርሶ ሁለታቸው በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀዋል ስለዚህ አይሁድ አለበለዚያም አሕዛብ ብቻ ሳይሆኑ ዛሬም ላይ ወደዚህ እውነት ያልመጣን ሁላችን በክርስቶስ ኢየሱስ ተስፋ ወደሚገኝበት ፣ ከእግዚአብሔርም ጋር አንድ ወደምንሆንበት ወደዚህ ወደተባረከው ሕይወት እንምጣ ኤፌሶን 2 ፥ 11 _ 18 ማርያምም የሰው ዘር ስለሆነች ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው እኔ ነኝ አላለችንም ይልቁንም ተስፋዋም ሆነ መድኃኒትዋ ክርስቶስ መሆኑን ተናገረች የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 47 ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment