Friday 6 July 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 11 ) ክፍል አራት ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒት እርሱም ኢየሱስን አመጣ ( የሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 23 ) አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት ትርጉም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ( ምንጭ ቅዳሴ ማርያም ) ምንጭ ፦ ቅዳሴ ማርያም የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን የዚህን የቪዲዮ ትምህርት አንኳር አንኳር ሃሳብ እንደሚከተለው አቀርባለሁና ተከታተሉ የቅዳሴ ማርያም ደራሲ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት ትርጉም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ በማለት ተናገረ ( ምንጭ ቅዳሴ ማርያም ) እንዲህ ማለቱ ታድያ የቅዳሴ ማርያምን ሃሳብ በሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 23 ከተጻፈው ሃሳብ ጋር በትክክል አስተያይተን ከመረመርነው እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒት እርሱም ኢየሱስን ያመጣ አይደለም ወደሚለው የሚወስድ ነው ለምን ስንል እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒት እርሱም ኢየሱስን አመጣ ብሎ ያመነ ሰው በመድኃኒቱ በኢየሱስ ላይ ብቻ ሕይወቱ ያረፈ ነው ነገር ግን ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ሲል የቅዳሴ ማርያምን መጽሐፍ ያመነ ሆኖ ሳይቀር ከዚህ በተጨማሪ ይህንኑ ቃል እንዲሁ ተስፋው አድርጎ እየቀደሰና እያስቀደሰ የሚኖር አማኒ ከሆነ ግን ለአዳም ብቻ ሳይሆን ዛሬም ላይ ለእኔ የገነት በር መግቢያ ተስፋዬ ማርያም አንቺ ነሽ ብሎ የሚያስብ ነውና እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒት ሆኖ የመጣበትን የኢየሱስ መምጣትና እግዚአብሔርም በዚሁ በተስፋው ቃል መሠረት መድኃኒት አድርጎ ኢየሱስን ያመጣበት ምሥጢር አይገባውም ከዚህ በመቀጠል ጌታ እግዚአብሔር ኢየሱስ የተባለውን መድኃኒት የሆነውን እውነት ያመጣበትን ወደ ሰባት የሚደርሱ ነጥቦችን እንደሚከተለው በዝርዝር አቀርባለሁ 1ኛ ) ጌታ እግዚአብሔር ኢየሱስ የተባለውን መድኃኒት ሲያመጣ በቅድሚያ ለሰው ዘር በሙሉ የሚሆንን ተስፋ ሰጥቶ ነው 2ኛ ) እርሱ የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው 3ኛ ) ይህንን ተስፋ ያረጋገጥነው በእምነት ነው 4ኛ ) ይህ በእምነት ያረጋገጥነው ተስፋ እርሱ ንጹሕ እንደሆነ እኛንም ንጹሐን ያደርገናል 5ኛ ) ይህ ተስፋ ታድያ በቅድምና ለአባቶችም የተሰጠ ተስፋ ነው 6ኛ ) እግዚአብሔር የሰጠን ተስፋ የታመነውንና የተፈጸመውን የዳዊትን ተስፋ ነው 7ኛ ) ይህ ተስፋ በአብርሃም በዳዊትና በእስራኤል ሕዝብ ሳይቀር አሕዛብም ሁሉ ተስፋ ያደረጉት ነው የተወደዳችሁ ወገኖች በተራ ቁጥር የተዘረዘሩት ነጥቦች አስረጂ ጥቅሶች አሏቸው እነዚህን አስረጂ ጥቅሶች የምታገኙት በቪዲዮ ከተለቀቀው ትምህርት ነው ስለዚህ ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ተከታተሉ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment