Saturday 30 June 2018

ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ተሰጠ ተብሎ የእግዚአብሔር ቃል ያላረጋገጠው እምነት ሁሉ አልታደስም ቢል እንኳ ፈጥኖ ይታደሳልለክርስቲያኖች ሁሉ የሚጠቅም ድንቅ ውይይት ፦ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ተሰጠ ተብሎ የእግዚአብሔር ቃል ያላረጋገጠው እምነት ሁሉ አልታደስም ቢል እንኳ ፈጥኖ ይታደሳል የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን ፣ ሃይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠ ነውና ኦርቶዶክስ አትታደስም በሚል ሽፋን ፣ በሀገራችን ፣ በተለይም በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከልካይ ሳይኖራቸው ተዘፍዝፈውና ተወዝፈው ያሉ የገድላትና የድርሳናት ጥርቅሞች እንዲሁም ባዕዳን የሆኑ የጥንቆላና የአስማት ልምምዶች የቆሻሻ ያክል ተጠርገው ጋርቤጅ የሚጣሉበት ፣ ጊዜያቸውም ደርሶ የሚቃጠሉበት ዘመን እየመጣ ስላለ ይህ ትምህርት ቃሉ የተጻፈበትን ሃሳብ ተከትሎ በእንዲህ መልኩ ዛሬ ወደ እናንተ ቀርቦአል :: ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠው መጽሐፉ እንደሚነግረን ሃይማኖት ሳይሆን እምነት ነው :: ለዚህም አስረጂ እንዲሆነን መደበኛውን የመጽሐፍቅዱስ ትርጉምና የእንግሊዘኛውን መጽሐፍ ቅዱስ መመልከት በቂ ነው( የይሁዳ መልዕክት 1 ፥ 3 ):: እግዚአብሔር ሃይማኖተኛ ሰዎችን ማፍራት አይፈልግምና ሃይማኖትን ለሰዎች አልሰጠም ፣ ሰጥቶም አያቅም ፣ ወደፊትም አይሰጥም :: እግዚአብሔር የሰጠን ግን እምነት ስለሆነ ፣ በቃሉ የሆነውን እምነት የሰጠን አንድ ጊዜ ነው :: ታድያ ከእግዚአብሔር አንድ ጊዜ የተሰጣትን በቃሉ የሆነን እምነት ያላወቀች ይህቺው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፣ ከያዘቻቸው ደባል ተረቶችና ጥንቆላዎች የተነሳ ይኸው የተሃድሶ ነፋስ ከዛሬ ነገ ያገኘኝና ሥር ነቀል በሆነ ለውጥ ያድሰኛል የሚል ፍርሃት ይዞአት እንቅልፍ የነሳት በመሆኑ እውነትን የያዘች ለመምሰል ሃይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠ ነውና ኦርቶዶክስ አትታደስም ስትል መከላከያ የመሰሉ ቃሎችን ልታቀርብ ትሞክራለች :: የተሃድሶ ንቅናቄ ግን በእግዚአብሔር ችሎትና በመንፈስቅዱስ ጉልበት ጉያዋ ውስጥ ገብቶ ሃይማኖት አንድ ጊዜ ተሰጥቶኛልና አልታደስም ስትል ብታቅራራም እንኳ ላይቀርልሽ ሲል እያደሳትና ተረትዋንም ሆነ ጥንቆላዋን እያስጣላት ይገኛል :: ክብሩ ለወደደን ፣ ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለነገሥታቱ ንጉሥ ለኢየሱስ ይሁንለት አሜን:: ታድያ የዛሬውም ትምህርት የሚያመላክተው ይህንኑ ነው :: ከዚህም ሌላ መናፍቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ መናፍቅ ማን እንደሆነ ፣ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ መናፍቅ በሚለው ዙርያ ምን ዓይነት አቋም እንደነበራቸውና ምን እንደተባሉ ትምህርቱ በሰፊው ያትታል ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ተከታተሉ በትምህርቱም ተባረኩ ፣ ለሌሎችም ሼር ማድረግን አትርሱ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከተሃድሶ ለኦርቶዶክስ አገልግሎት

No comments:

Post a Comment