Tuesday 24 July 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 1 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም 1ኛ ቆሮንቶስ 5 : 7 እና 8 1ኛ ) ፋሲካ የእግዚአብሔር ነው ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው ኦሪት ዘጸአት 12 : 11 ፋሲካ የእግዚአብሔር ነው :: በመሆኑም ማርያምን ፋሲካዬ ሊላት ፣ ፋሲካውም ሊያደርጋት እግዚአብሔር ፕሮግራም አላደረጋትም :: የእግዚአብሔር የፋሲካው ፕሮግራምና ፋሲካው ፣ ፋሲካችን የሆነው ፣ የታረደልንም ክርስቶስ ኢየሱስ ነው :: ይሁን እንጂ ማርያምም የእግዚአብሔር የፋሲካው ፕሮግራም ልሁን ብትልና የአዳምም ሆነ የሰው ልጆች ሁሉ ፋሲካ መሆንዋን ብትናገር የአዳም በደል እርስዋንም ስለሚመለከት የእግዚአብሔር ፕሮግራምም ሆነ የእግዚአብሔር ፋሲካ ልትሆን አትችልም :: ይልቁንም ማርያም የእግዚአብሔር ፋሲካ የሚያስፈልጋት ስለሆነች ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች የባርያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና ስትል ፋሲካዋ ክርስቶስ እንደሆነ ተናገረች ( የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 47 ) :: የተወደዳችሁ ወገኖቼ ፋሲካ የእግዚአብሔር ነው :: በመሆኑም ፋሲካ የእግዚአብሔር መሆኑን አውቀን እዚህ የእግዚአብሔር ፋሲካ ውስጥ ስንገባ እንደ ሙሴ ፋሲካንና ደምን መርጨት በእምነት እናደርጋለን:: ከዚህም ሌላ አምላካችን ስሙ በእኛ ላይ ይጠራል :: እንደገናም በዚህ በእግዚአብሔር ፋሲካ ከፍ ባለ እጅ እንወጣለ :: ለዚህም ነው ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም በማለት አምላካችን በራዕይ መጽሐፍ ላይ የነገረን :: ትምህርቱ እንግዲህ እነዚህን ሃሳቦች ሁሉ አካቶ የያዘ ነው በይበልጥ ቪዲዮውን ብትሰሙ ደግሞ ትባረኩበታላችሁ :: ዘመናችሁ ይባረክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

No comments:

Post a Comment