Monday 18 June 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 6 ) ክፍል አራት ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነን የውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ ወትቤ ማርያም ከመባሉ በፊት ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ የሚባል ነው ገጽ 132 ወይም በአሥመራው እትም ገጽ 399 የተወደዳችሁ ቅዱሳን በክፍል አራት ቁጥር ስድስት የተመለከትነው ሃሳብ በአጭሩ ድንግል ማርያም ከኢየሱስ ይልቅ የቀረበችን ሆና ጸሎትዋና ልመናዋ ከልጇ ቊጣ ሊያድነን እንደማይችል ፣ እንደገናም ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቁጣ ሊቀበልልን የመጣ ጌታ እንጂ ሊቆጣንና የእግዚአብሔርንም ቁጣ በእኛ ላይ ሊያወርድብን የመጣ ጌታ አለመሆኑን ፣ ከዚህም ሌላ ደግሞ ከማርያም ይልቅ በብዙ የሚቀርበን ፣ መቅረቡም ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለማርያምም ጭምር የሆነ በመሆኑ በአጠቃላይ ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራን ያላፈረብንና ከእንግዲህም ወዲህ ባሮቼ አልላችሁም ወዳጆቼ ብያችኋለሁ ከአብ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ ነገርኳችሁ ያለን መሆኑ ከእግዚአብሔር ቁጣ አዳነን ስንል ደግሞ ያዳነን በደሙ መሆኑን ከዚህ የተነሳ ደሙ ሥርየታችን ፣ ቤዛችን ፣ መታጠብያችንም ሆነ መጽድቅያችን መሆኑን ከእግዚአብሔር ቃል በማስረጃ ተምረናል አያይዘንም የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሠርያልና በመሰውያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተሥረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት ይለናል ( ዘሌዋውያን 17 ፥ 11 ) በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ለእኛ መስዋዕት መሆን አስፈለገው ታድያ ቃሉም እንደዚህ ይለናል እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ ዕብራውያን 10 ፥ 19 _ 25 ወገኖቼ የተመረቀ መንገድ አለ በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት የሆነን ታድያ ይሄ መንገድ የተመረቀው በኢየሱስ ደም ነው በመሆኑም ከዚህ ከኢየሱስ ደም ውጪ ሌላ መግቢያም ሆነ መተላለፍያ መንገድ እና በር በፍጹም የለም ትምህርቱ የሚያስታውሰን እንግዲህ ይህንን እውነት ነው ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ሰምታችሁ ተባረኩበት ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment