Tuesday 26 June 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 8 ) ክፍል አራት ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳየማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነንየውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ ወትቤ ማርያም ከመባሉ በፊት ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ የሚባል ነው ገጽ 132 ወይም በአሥመራው እትም ገጽ 399 መጽሐፈ ሰዓታት የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን ማለቱ ኢየሱስ የተቆጣ ፣ መዓትንም ሊያወርድ የተዘጋጀ ስለሆነና ከዚህም የተነሣ የማርያም ምልጃ ያስፈለገው ሆኖ አይደለም :: እርሱ ከቁጣ ሊያድነን ፣ የእግዚአብሔርን ቁጣ የተቀበለልን ጌታ ነው :: ነገር ግን አሁም መጽሐፈ ሰዓታት የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን ማለቱ የተአምረ ኢየሱስን ድርሳን ለመቀበልና ሃሳቡንም ትክክል ነው ሲል በመስማማት ሊያጸድቀው ፈልጎ ነው :: ከዚህ በመቀጠል የተአምረ ኢየሱስን መጽሐፍ ውሸትና ቅጥፈት በሙሉ የሚደረምስ የአምላክ ቃል በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ይገኛል ተአምረ ኢየሱስ ኢየሱስ በልጅነቱ ምልክቶችን ( ተአምራትን ) ሰርቷል ሲል ውሸቱን ይናገራል መጽሐፍቅዱስ ደግሞ እንዲህ ሲል እውነቱን ይናገራል ኢየሱስ በልጅነቱ ምንም ምልክት ( ተአምር ) አልሰራም እርሱ ምልክት ተአምር የሚሰራው ሰዎችን ወይም ራሱን ለማዝናናት ሳይሆን ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑበት ብቻ ነው ዮሐንስ 2 ፥ 11 የተአምረ ኢየሱስ መጽሐፍ እውነተኛና ጥንታዊም ነው እንዲባል በቶማስ ስም ተጠርቷል :: የቶማስ ወንጌልም ተብሎአል :: ታድያ ኢየሱስ በዚህ ድርሳን ላይ እንደ ተአምረኛ ሳይሆን እንደ አዝናኝ ( ሰዎችን እንደሚያዝናና ) አስማተኛ ሆኖ ቀርቦአል :: ከዚህም ሌላ ነፍሰ ገዳይም ሆኖ ቀርቦአል :: አንድ የሰፈራቸውን ልጅ ከሞት ካስነሳ በኋላ የአንዲት ጥያቄ መልስ ከእርሱ ጠይቆ ሰማና ወዲያውኑ መልሶ ገድሎታል ይላል ልብ ወለዱ የተአምረ ኢየሱስ መጽሐፍ:: ታድያ ለዚህ ይመስላል የመጽሐፈ ሰዓታት ጸሐፊ የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን ያለው :: አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የሰውን ዘር ለማዳን የመጣ ፣ ማንንም ከቶ ያልገደለ ፣ ነገር ግን ለጠላቶቹ ሳይቀር ምሕረትን የለመነ የፍቅር ጌታ ነው :: በመሆኑም ነፍሰ ገዳይ ነው ሲሉ ለኢየሱስ ስም መስጠት ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን በጎ ባሕርይ ሳይቀር አለመረዳትና ስሙንም ማጥፋት ነው :: ከዚህ የተነሣ ይህን የመሠለ ተአምር መሠል ተረት ለሰማው ሰው ሳይቀር እጅግ አሳፋሪ በመሆኑ የሀገራችን ሰዎች እንኳ ወንጌል ብለው ለመጥራት ቀፎአቸዋል :: ከወንጌል ጋር ተዳብሎ እንዳይሰበክ በማሰብም ተአምረ ኢየሱስ ሲሉ በልዩ ስም ሰይመውታል :: በተጨማሪም የወንጌልን መደብ ከልክለውት የድርሳናትን መደብ አስይዘውታል :: ይሁን እንጂ ታድያ መጽሐፍ ቅዱስ አሁንም ጎደሎ አይደለም ፣ ስለ ኢየሱስ የልጅነት ዘመን በቂ መረጃን ይሰጠናል ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር የጀመረው በሠላሳ ዓመቱ ሲሆን የመጀመርያውንም ተአምራት ያደረገው በገሊላ ቃና ሠርግ ላይ ነው :: መጽሐፍቅዱሳችንም ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመርያ በገሊላ ቃና አደረገ ክብሩንም ገለጠ ደቀመዛሙርቱም በእርሱ አመኑ ይለናል የዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 1 _ 11:: ታድያ ከዚያ በፊት የት ነበር ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ በአጭሩ ናዝሬት ነበር ነው :: የናዝሬት ሰዎችም የኢየሱስን ድንቅ ትምህርት ሰምተው ያልተቀበሉት ፣ በመሀከላቸው ስላደገና ስለኖረ ነው :: ኢየሱስም ነቢይ በሀገሩ አይከበርም ያለባት ከተማ ናዝሬት ስለሆነች ኢየሱስ ናዝሬት ከተማ ውስጥ እንደነበረ ያሳየናል ማቴዎስ 13 ፥ 53 _ 58 መልዕክቴን ስጠቀልለው ዛሬም ታድያ በአሁኑ ዘመን ባለች በማንኛዋም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመሀላችን ወገኖች ሲቀቡ የቅናት መንፈስ ይጫወትብናል አዛውንት አባቶቻችንም በምሳሌያቸው ሊያስረዱን አወኩሽ ናኩሽ ያሉን ለዚህ ነው በመሆኑም ከነዚህና ከመሳሰሉት መጽሐፍቅዱሳዊ ምክሮች በመነሳት ጌታ እግዚአብሔር መናናቃችንን አስወግዶ ፣ ዘለቄታዊ ያለው የመቀባበል ፈውስ ለኦርቶዶክሳዊቷ ብቻ ሳይሆን በዘመናችን ላለች ለየትኛዋም ቤተክርስቲያን ያምጣልን እላለሁኝ ተባረኩልኝ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment