Friday 19 January 2018

የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Challenges ) ክፍል ስድስት ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ? ( ቊጥር 3 )የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Challenges ) ክፍል ስድስት ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ? ( ቊጥር 3 ) የቤተክርስቲያን ሥልጣን የክርስቶስ እንጂ የነቢያት ወይም የፓስተሮች አይደለምና በማናለብኝነት የክርስቶስ የሆነችን ቤተክርስቲያን የኔ ሲሉ የራሳቸው እና የቢጤዎቻቸው ሊያደርጉ የሚሯሯጡ የዘመናችን የነቢያቱ ፣ የፓስተሮቹ……. እሩጫና የኲራቱ ጒዞ እስከ መቼ ? ( ቊጥር 3 ) ከአሜሪካ ____________________ ጂንካ ጓዛቸውን ጠቅልለው የገቡና ለወንጌሉ ሥራ ቆርጠው የዘመቱ ደገኛው ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የወንጌል ዘማች ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ለሰሚዎቻቸው ያስተላለፉትን አንኳር የሆነውን አስተማሪ መልዕክት በአጭሩ ቀንጨብ አድርጌ እነሆ ብያለሁ እና ተከታተሉ ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ? በሚለው በክፍል ስድስት ቊጥር ሦስት ትምህርታችን ላይ በጥምረት አያይዘን የምናነሳቸው ዓበይት ጉዳዮች ከዚህ እንደሚከተሉት ናቸው ትምህርታችንን ጠቅለል አድርገን በአጭሩ ስንመለከተው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመኑ ከሐዋርያቱ ይልቅ ፈጥኖ መልስ በመስጠት ለሚታወቀው ለጴጥሮስ የሰጠው መልስ ነበረ በዚህ የክርስቶስ ለቀረበ የማን ትሉኛላችሁ ጥያቄ ጴጥሮስ አንታማ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ሲል አስደናቂ መልስ ሰጠ በዚህን ጊዜ ነው ጌታችን የዮና ልጅ ስምኦን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ የገሃነም ደጆች አይችሉአትም ያለው እናንተ ምዕራፉን አውጥታችሁ የተጻፈበትን ክፍል ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 13 _ 20 የተወደዳችሁ ወገኖች እንግዲህ ይህንን የመጽሐፍቅዱስ ክፍል በማስተዋል ስናነበው ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የራሱ አድርጎ ያያትና የቆጠራትም በመሆኑ ቤተክርስቲያኔ ብሎአታል ስለዚህ ቤተክርስቲያን የእርሱና የእርሱ ብቻ ስለሆነች እርሱም በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ የገሃነም ደጆች አይችሉአትም ስላለ በራሱ ቤተክርስቲያን ላይ ዋናው ሠራተኛ እርሱ ራሱ ነው እኛ ባሮቹ ግን ልዩ ልዩ ዓይነት የአገልግሎት ስም ቢኖረንና ስማችንም በሰዎች ዘንድ ሳይቀር ገዝፎና ከብሮ ቢጠራም ቤተክርስቲያን ግን አንዴ የእርሱና ለእርሱ ብቻ ስለሆለች የእኛ አይደለችም የእኛም ልትሆን አትችልም የእኛ የምንለው ምንአልባትም እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሠራተኛ በከንቱ ይተጋል ይላልና እግዚአብሔር በቸርነቱ የሠራልን ዞረንና አገልግለን ገብተን የምናርፍበት ቤት ሊሆን ይችላል መዝሙር 126 ( 127 ) ፥ 1 ፤ 2ኛ ሳሙኤል 7 ፥ 11 _ 18 ከዚያ ውጪ ግን የእኛ ያልሆነችዋን ቤተክርስቲያን የእኛ ልናደርግ በገዛ አዕምሮአችን ሰንፈን ከሰዎች ጋር በተጋጨንበት ፣ ከሌሎች አገልጋይ ባሮችም ጋር በተማታንበት ፣ ልንበላ ፣ ልንጠጣ ልንሰክርም በጀመርንበት ነገር ሁሉ አሁኑኑ ፈጥነን ንስሐ ልንገባ የበደልናቸውንም ሰዎች እግራቸው ላይ ወድቀን ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል እላለሁኝ አለበለዚያ ግን በፍጻሜው ከአምላካችን ዘንድ የሚመጣብን ቅጣት የከፋ ይሆናል የሉቃስ ወንጌል 12 ፥ 41 _ 48 ነገር ግን ከዚህ ይልቅ እምቢ አሻፈረኝ ስንል ቤተክርስቲያንን የራሳችን ልናደርጋት ብንሞክር ስንላላጥ እንኖራታለን እንጂ በምንም መልኩ ቤተክርስቲያን የእኛ ልትሆን አትችልም ደግሞም ሊቆይ ይችል ይሆናል እንጂ በጊዜ ውስጥ እግዚአብሔር ከእጃችን ወስዶ ሃላፊነታቸውን ለተገነዘቡና የቤተክርስቲያንን ማንነትም ሆነ የራሳቸውን ማንነት በውል አውቀው የማልጠቅም ባርያ ነኝ ሲሉ በትሕትና ለሚያገለግሉ ባሮች በባላደራነት ይሰጣል የሉቃስ ወንጌል 17 ፥ 10 ቤተክርስቲያን ግን ለሁልጊዜም እስከ ዘላለም የክርስቶስ ነች ኤፌሶን 1 ፥ 22 እና 23 ፣ ራዕይ 11 ፥ 15 ውድ ወገኖቼ ሆይ እንግዲህ ይህንን የቃሉን እውነት እንድናገር ግድ ያለኝ ከለቀኩት ቪዲዮ ተነስቼ ነው ትምህርቱም እንዲህ በማለት የሚናገር ነው በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ነቢያት የቤተክርስቲያን መሪዎች ነበሩ ይህ ማለት የሐዲስ ኪዳን ነቢያት በአዲሱ የኪዳን ሥርዓት መካከል የቤተክርስቲያን ጒበኞችና አቅጣጫንም ጠቋሚዎች ስለሆኑ የተለዩ መሪዎች ናቸው ኤፌሶን 4 ፥ 11 እንደገናም መጽሐፍቅዱሳችን በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል ብሎናልና ቤተክርስቲያን የተገነባችው በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ነው ኤፌሶን 2 ፥ 20 ይህ ማለት ግን መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ቤተክርስቲያን በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታነጸች አለን እንጂ ሐዋርያትና ነቢያት በቤተክርስቲያን ላይ ተመሠረቱ አላለንም ከዚህ የተነሣ ቤተክርስቲያን ለጥቂት ሕዝቦች ፍላጎትና ስኬት ሲባል ለሐዋርያትና ለነቢያት ፣ ለፓስተሮች ሥልጣን የበላይነት የተሰጠች አይደለችም እንደገናም ቤተክርስቲያን የነቢያቱም ሆነ የሐዋርያቱ እንዲሁም የመጋቢዎች ስልጣን አይደለችም ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሥልጣን ናት ባለ ሥልጣኗና አዛዥዋ አስተዳዳሪዋም ክርስቶስ ነው ቤተክርስቲያን ግን ራስ ከሆናት ከክርስቶስ ሥልጣን የተነሳ ለእነዚህ አገልጋዮች እውቅና እየሰጠች እንዲያገለግሉ ታደርጋለች ይህንን እውነታ ባለማወቅና አውቆም የሕይወትን ለውጥ ባለማግኘት ነው እንግዲህ ዛሬ ላይ የምናየውን ትርምስ እስካሁን የምናየው የተወደዳችሁ ወገኖች ፦ ከአሜሪካ ____________________ ጂንካ በማለት የብፁዕ አባታችን አቡነ ፊልጶስን ምስክርነት በወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ካሉ ነቢያትና ፓስተሮች ጋር አያይዤ ማቅረብ የፈለኩት እንግዲህ ከዚህ የተነሳ ነው ከአሜሪካ ____________________ ጂንካ መልዕክታቸው በዩቲዩብ ስለተለቀቀ አቡነ ፊልጶስ ብላችሁ በመጻፍ ዩቲዩብ ውስጥ ገብታችሁ ምስክርነታቸውን ማዳመጥ ትችላላችሁ ታድያ እኚህ አባት በጠያቂያቸው በሊቀ ማዕምራን ዓባይ አማካኝነት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ወደ ጵጵስና ማዕረግ ከመምጣታቸው በፊት በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ብዙ ጊዜያቸውን ተቀምጠው በትምህርት ዓለም ያሳለፉ በመሆናቸው የሊቀ ጵጵስናቸውን ማዕረግ እንደተቀበሉ ለአገልግሎት የተመደቡት ጅንካ ነበርና ይህንን የሥራ ዝውውር በአሜንታ ነበር ተቀብለው ጉዞአቸውን ወደ ጂንካ ያደረጉት ታድያ ጠያቂው ሊቀ ማዕምራን ከአሜሪካ ወደ ጂንካ ሄደው ሊያገለግሉ የወሰኑበትን ጉዳይ ሊያውቅ ብሎ የጠየቀውን ጥያቄ ብፁዕነታቸው ሲመልሱ መልሳቸው ትሕትናንና መንፈሳዊነትን አዋቂነትንም ጭምር የተላበሰ በመሆኑ እጅግ ማራኪ ነበር ብፁዕነታቸው እንዲ ሲሉ ዛሬ ላይ በፓስተሮችና ነቢያቶቻችን ጭምር እግራችን እስኪነቃ ድረስ ብንፈልግ የማናገኘውን ነገር ፍንትው አድርጎ በመግለጽ መልሳቸውን አዥጎደጎዱት ከዚህም ሌላ ማን ያርዳ የነበር ማን ይናገር የቀበር እንደሚባለው እኚህ አባት አሁን ላይ እየኖሩ ያሉትን የጂንካን ሕይወት ከአሜሪካውና ከአውሮፓው ሕይወት ጋር ጎን ለጎን በማስተያየት በውስጣቸው አላባራ ብሎ እየነደደ ያለውን እውነታ ከተጻፈልን ቃል ጋር እያያያዙ አቀጣጠሉት እኔም ደገኛው ሐዋርያ እንዲህ ነው ይበል ብዬ ማስታወሻ ደብተሬንና ብዕሬን ይዤ ቀረብኩ እርሳቸውም ነገራቸውን በመቀጠል ወደ ተረሱት ወደተጣሉት መድኃኒተ ዓለም ክርስቶስ መጥቷል እኔም እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በእርሱ ሳይገባኝ እንዲገባኝ አድርጎ በአባቶች ወንበር ላይ እንድቀመጥ ካደረገበት ጀምሮ መንገዴን ወደ ደቡብ ኦሞ አድርጌያለሁ ብዙ ስለ ሀገሩ የተነገረኝ ነገር ነበረ እንዴት ይኖሩ ይሆን ?ተብዬም በስልክ ሳይቀር ብዙ ተወርቶልኛል ተነግሮኛልም እንግዲህ ስላልገባንና ስላላወቅን ነው እንጂ መቼም ደቡብ ኦሞ ሀገራችን ነው አንድ ዓይነት ጫካ ፣ አንድ ዓይነት ሕዝብ ነው ያለን ደግሞም ያሳደገን ጫካ ፣ ያሳደገን ወንዝ ፣ ያሳደገን ውሃ ፣ ያሳደገን አፈር ላይ ነው ተመልሰን የገባነው የማናውቀው ቋንቋ ላይ ፣ የማናውቀው ሀገር ላይ ፣ የማናውቀው አየር ላይ እኮ መጥተን ለምደን እየኖርን አይደለም እንዴ የነበርነው በምዕራቡ ዓለም ? የሚገርመው እኮ ያ ነው የምናውቀው ሀገራችንማ እንዴት ? የምናውቀው ሕዝባችን ያሳደገን እኮ ነው እንጨት እኮ ሰብረንበት የኖርነው ነው ይሄ አያስገርመኝም ( ይበል አሜን ብያለው ከጸሐፊው ) ቀጥለውም እንዲህ አሉ እንደውም እኔ ሕሊናዬ ያረፈው እዚያ ተመድቤ ስኖር ነው ምቾትም ቢሆን እኮ ከዚያ የበለጠ ምቾት አይኖርም ምክንያቱም የጠፋ ሰው ተመልሶ የእግዚአብሔር ልጅ ሲሆን ማየት በእውነት ትልቅ ነገር ነው ይህን ከማየት በላይ ለእኔ ምንም ደስታ የለም ብለዋል ይህ እንግዲህ ሐዋርያዊ የነ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ጉዞና ቀጣይነትም ኖሮት ለወንጌል ሥራ ወደፊት የተራመደ በ14ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ተነስቶ ያለ የነ አባ እስጢፋኖስ ንቅናቄ ብዬዋለሁ በዚህ አጋጣሚ ለብፁዕ አባት አቡነ ፊልጶስ እድሜና ጤናን እመኝላቸዋለሁ መልዕክቴን አልጨረስኩም የሚቀጥለውን የብፁዕነታቸውን ሃሳብ በክፍል ሁለት ትምህርቴ ላይ አቀርበዋለሁ አስተውላችሁ አንብቡት ቪዲዮውንም ስሙት ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን

No comments:

Post a Comment