Tuesday 13 June 2017

የሥዕልን ትርጉም ፣ ሥዕሎች Symbolic ( ሲምቦሊክ ) በመሆናቸው መጽሐፍቅዱሳዊ ይዘታቸውንና ዘይቤያቸውን የምና...የሥዕልን ትርጉም ፣ ሥዕሎች Symbolic ( ሲምቦሊክ ) በመሆናቸው መጽሐፍቅዱሳዊ ይዘታቸውንና ዘይቤያቸውን የምናይበት የክፍል ሦስት ትምህርት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ከርማችኋል ዛሬ በቪዲዮ በለቀኩት ትምህርትና በርዕሱ መሠረት በግዕዙ ዲክሺነሪ ሥዕል ማለት በቁሙ መልክ ፣ የመልክ ጥላ ፣ አምሳል ፣ ንድፍ ፣ በውሃ በመጽሔት ፣ በጥልፍ ፣ በሥፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ ከደብር ፣ ከዕብን ፣ ከዕፅ ፣ ከማዕድን ታንጾ ፣ ተቀርጾ ፣ ተሸልሞ አጊጦ የሚዳሰስ መሆኑን አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋስው ወግሥ መዝገበ ቃላት ባዘጋጁት መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል ሥዕለ ኪሩብ ፣ ሥዕለ ጣኦት ፣ ሥዕላት ወምስላት ፣ አስተረየ በአየረ ሰማይ ሥዕለ መስተጽዕና በአፍራስ እሳት ወደ አማርኛ ስተረጉመው በሰማይ አየር ላይ በእሳት ፈረስ የተጫነ ሥዕል ታየ ማለትን የሚያመለክት ነው በመሆኑም Figurative language በመስጠት እንግዲህ ኤልሳዕም አይቶ አባቴ አባቴ ሆይ የእስራኤል ሰረገላና ፈረሰኞች ብሎ ጮኸ በማለት ይህንን ቃል ነው ጸሐፊው ሊጠቅስልን የፈለገው 2ኛ ነገሥት 2 ፥ 10 _ 12 እነዚህ የእስራኤል ሰረገላና ፈረሰኞች የእስራኤል ደኅንነት ናቸው እስራኤል በደኅንነት ተጠብቀው የሚኖሩት ከእነዚህ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች የተነሳ ነው በዚህም ምክንያት የግያዝ መንፈሳዊ ዓይን የተያዘ በመሆኑ በሥጋዊ ዓይኑ የሶርያ ፈረሶችና ሰረገሎችን አይቶ በጮኸ ጊዜ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥለት ብሎ ጸለየ እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ ይለናል 2ኛ ነገሥት 6 ፥ 1 _ 23 ስለዚህ በምድር ላይ ዛሬም Symbolic ( ሲምቦሊክ ) ሆነው የቀረቡ ብዙ ፈረሶችና ሰረገሎች አሉ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ናቸው ባንላቸውም ሲምቦሊክ ሆነው በመሰራታቸው ሰዎች በእነዚህ ፈረሶችና ሰረገሎች ዛሬም ይጓዛሉ የመጽሐፍቅዱስ ቋንቋ ሃብታምና ዘይቤያዊ አነጋገር ያለው በመሆኑ የመጽሐፍቅዱስ ጸሐፊዎች ማንኛውንም መንፈሳዊ እውነቶችን Symbolized ( ሲምቦላይዝድ ) ሲያደርጉ ቤተሰባዊ ሆነው ነው Symbols ( ሲምቦልስ ) ብዙ ጊዜ ውብና አስደሳች የሆነ Figurative Language አላቸው ይህንን ሃሳብ ለማጠናከር መክብብ 2 ፥ 2 ፣ ኢሳይያስ 10 ፥ 18 _ 19 ፤ ኢሳይያስ 32 ፥ 19 ፤ ዘጸአት 19 ፥ 4 ኢሳይያስ ሁልጊዜ የሚጠቀመው ዛፎችንና ጫካዎችን እንዲሁም ደኖችን ለጥንካሬ ነው ነገር ግን እነዚህ ደኖችና ጫካዎች የሊባኖስም ዝግባ ጭምር እንደሚቆረጡና እንደሚገለጡ ዳዊት በመዝሙሩ ተናግሯል መዝሙር 28 ( 29 ) ፥ 3 _ 9 ጫካው ደኑ ዱሩና በሊባኖስ ዝግባ የተመሠለው ጠንካራው የሰው ልብ ነው ዘላለማዊና ኃይለኛ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ግን ይመነጠራል ይገለጣል ኢያሱንም ተራራማው ሀገር ለአንተ ይሆናል ዱር እንኳ ቢሆን ትመነጥረዋለህ ያለው ለዚህ ነው ኢያሱ 17 ፥ 17 እና 18 የንስር ክንፍንም በተመለከተ በፊደላዊ ትርጉሙ ስንመለከተው እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብጽ ለማውጣት እውነተኛውን ንስር ሕዝቡን በዓየር ለመሸከም አልተጠቀመም ይህ ዓረፍተ ነገር በግልጽነት ሲምቦሊክ ነው እግዚአብሔር አጉልቶና አጋኖ በጣምም አሳስቦ ሊነግረን የወደደው እስራኤልን ነጻ በማውጣት ዙርያ ፍጥነትንና ጥንካሬን ለማሳየት ነው ኢየሱስም ሰዎችን ያስተማረው ሙሉ በሆነ ሲምቦሊዝም ነው ራሱንም ያቀረበው በእረኛ ፣ በሙሽራ ፣ በበር ፣ በማዕዘን ራስ ድንጋይ ፣ በወይን ፣ በብርሃን ፣ በእንጀራና በውሃ ነው ሲምቦል ሁልጊዜ ምልክቶች ብቻ አይደሉም ሲምቦል ትንንሽ ሥዕሎች በኮምፒውተር ውስጥ እንዳለ አይከን ቀለል ያሉ ማብራርያዎችን የሚሰጡን ናቸው ይህንን ሁሉ ያብራራሁበት ምክንያት ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን የራስዋ የሆነ ፊደል ፣ ስነ ጽሑፍ ፣ ዜማ ፣ ኪነ ሕንጻና የመሣሠሉት እንዳሏት ሁሉ የራሱ የሆነ የስነ ሥዕል ጥበብም ያላት ስንዱ እመቤት እንደሆነች ለመጠቆም ነው ከዚህ የተነሳ በትውፊታዊ መልክ የተቀበለችውን ሥዕሎችዋን በአብያተ ክርስቲያናት ግድግዳ ፣ በሸራ ፣ በብራና በወረቀትና በመስቀሎች ላይ በቀለም ወይም በጭረት ባለ ሁለት ጎን ሆነው የሚሰሩ የተደራሲውን ማንነት የሚገልጥ መንፈሳዊ ጥበቦች ናቸው ይሁን እንጂ በሥዕሉ ላይ የሚታዩትን መንፈሳዊ ጥበቦችን ብናደንቅም ስግደትንና አምልኮትን ግን በፍጹም አንሰጠውም በሥዕሉም ፊት በመጸለይና በመስገድ ከሥዕሉ ባለቤት መንፈሳዊ በረከቶችን እናገኛለን ብለን አናምንም ሥዕልን በትክክለኛው መንገድ እንደ መጽሐፍቅዱሱ ቃል ተስሎ ካገኘነው ለማስተማርያነት ልንጠቀምበት እንችላለን ከዚያ ያለፈ ትርጉም ግን አንሰጠውም በክፍል አራት ትምህርት እስክንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ የምላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment