Tuesday 27 June 2017

የሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ሰባትየሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ሰባት በክፍል ሰባት ትምህርታችንም ድንግል ማርያምን መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ይሏታልና ወደ አማርኛው ስተረጉመው ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሚለውን ሃሳብ የሚይዝልን በመሆኑ ከዚህ በመነሳት ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሰዓላ በዕዱ ሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ ወደ አማርኛው ስተረጉመው ከወንጌላውያን አንዱ ሉቃስ በእጁ ለሳላት ለማርያም ሥዕል ምስጋና ይገባል የሚል ሃሳብ ይዘው ብዙዎች የኦርቶዶክሳውያን አማኞች በማርያም ሥዕለ አድኅኖ ፊት ይጸልያሉ ፣ ይሰግዳሉ ፣ አምልኮተ እግዚአብሔርም ያደርጋሉ ታድያ ይህ ትክክለኛ የሆነ መጽሐፍቅዱሳዊ እውነትነት ያለው ነው ወይ ? ወንጌላዊ ሉቃስስ በእርግጠኝነት የማርያምን ሥዕል ስሏል ወይ ? ስንል ለዚህ ያገኘነው መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃ ባለመኖሩ ወንጌላዊ ሉቃስ የማርያምን ሥዕል ስሏል ለማለት አንችልም ድንግል ማርያምም መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ሲተረጎም ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሚል ነውና በመጽሐፍቅዱሳችን ውስጥም ማርያም ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ናት የሚል ቃል ተጽፎ አላገኘንም ይልቁንም የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስተምረን ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ ነው የሚለን የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 27 ስለዚህ ከዚህ ከመጽሐፍቅዱሱ እውነት የተነሳ ማርያም ሰው የሆነች ድንግል መሆንዋን ነው ከቃሉ የምንረዳው ነገር ግን መጽሐፍቅዱሳችን ትክክለኛውን እውነት ነግሮን ሳለ ድንግል ማርያምም ሰው መሆንዋ ተረስቶ ተአምረ ማርያም በሚለው መጽሐፍ ላይ ለሥዕሏ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ ፣ ማርያም ማለት መንግስተ ሰማያት መርታ የምታገባ ማለት ነው የሚሉት እና የመሣሠሉት ሃሳቦች ተሰንዝረዋል ከዚህም ሌላ አሁንም ለድንግል ማርያም መልክአ ሥዕል ተደርሶላት በአምላክነት ወይም በመለኮት ኃይል ልክ እንድትመለክ የሚያደርግ ድርሰትና ምስጋና እስካሁን ድረስ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እየተዘመረ ፣ እየተመሰገነ ፣ እየተጸለየ ይገኛል ይህ ግን መጽሐፍቅዱሳዊ አለመሆኑን ከተአምረ ማርያም መጽሐፍ ጀምሮ ባለው ሃሳብ ተነስቼ እያንዳንዱን የተደረሰ መልክ በመዘርዘርና በመተንተን እንደ እግዚአብሔር ቃል ትክክል አለመሆኑን ገልጬ በዚህ የቪዲዮ ትምህርት አቅርቤዋለሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንግዲህ ትምህርቱ እንዳያመልጣችሁ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተከታተሉ በብዙ ትባረኩበታላችሁ እንደገናም ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ በክፍል ስምንት እስከምንገናኝ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ በማለት የምሰናበታሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment