Monday 1 May 2017

4ኛ ) በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ጥብቅ ግንኙነት ይደረጋል ( ክፍል ዘጠኝ )4ኛ ) በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ጥብቅ ግንኙነት ይደረጋል ክፍል ዘጠኝ የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በክፍል ዘጠኝ ትምህርታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ በሆነበት ሐዲሱ ኪዳን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን ከዳንነው ከእኛ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያደረገበት እና እኛም የእግዚአብሔር ልጆች በመሆን ከእግዚአብሔር ጋር ቤተሰብነትን የመሠረትንበት ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የእኛ የሆነበትን እውነት ነው የተማማርነው ዕብራውያን 8 ፥ 10 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 9 _ 10 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 8 ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5 ፥ 5 ፤ ቆላስያስ 1 ፥ 11-12 ሙሴ መካከለኛ በሆነው በብሉይ ኪዳኑ ሕግና የኪዳኑ ሥርዓት ግን የሄ ሁሉ የለም የነበረውም የግንኙነቱ መስመር በጣም የተራራቀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከዚያም መልስ እጅግ አስፈሪ ነበር በመሆኑም ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ አውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምጽም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና ያንን ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትዕዛዝ ሊታገሡ አልቻሉም ሙሴም እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበረ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር በእሳት ስለወረደበት የሲና ተራራ ይጤስ ነበረ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁ ተንቀጠቀጡ ይለናል ዕብራውያን 12 ፥ 18 _ 21 ፤ ዘጸአት 3 ፥ 6 ፤ ዘጸአት 19 ፥ 16 _ 25 ፤ ዘጸአት 20 ፥ 18 _ 21 በዚህም ምክንያት ነው እንግዲህ ነጐድጓዱንና መብረቁን የቀንደ መለከቱን ድምጽ ተራራውንም ሲጤስ ያዩ ሕዝቦች ተርበደበዱ ርቀውም ቆሙ ሙሴንም አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን እንዳንሞት እግዚአብሔር አይናገረን ነበረ ያሉት ታድያ በዚህ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የሆነ ጥብቅ ግንኙነት ነበረ ፤ አለም ብሎ ማሰብና መገመትም አይቻልም እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ያለው ነገር ከቃሉ እንደሰማነው ሌላ ቃል እንዳይጨመር መለመን ፤ መፍራትና መርበድበድ ርቆም መቆምና የመሣሠሉት ነገሮች ነው ያሉት በሐዲሱ ኪዳን የግንኙነት ሥርዓት ግን እግዚአብሔር ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ ያልሰጠን በመሆኑ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ተወግደዋል ሮሜ 8 ፥ 14 _ 17 ከእግዚአብሔር ጋር ያለንም ግንኙነታችን በክርስቶስ ፍጹም ሆኗል ወገኖች ተባረኩ ይህንንም ቪዲዮ ሼር አድርጉ በክፍል አስር ትምህርት እስክንገኛኝ ሰላም ሁኑ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment