Thursday 25 May 2017

የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል አንድ ትረካና የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ክፍል አስራ ስድስትየቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል አንድ ትረካና የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ክፍል አስራ ስድስት ይህ የቃልኪዳኑ ታቦት በቀዳማዊ ምኒሊክ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ተሰርቆ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ይገኛል ይባላል ይህንንም ታሪክ ተጽፎ የምናገኘው 1ኛ ) በክብረ ነገሥት መጽሐፍ 2ኛ ) በገድለ ተክለሐይማኖት መጽሐፍ 3ኛ ) በድርሳነ ዑራኤል መጽሐፍ ነው ( ምንጭ ካነበብኳቸው እና ካጠናኋቸው መጻሕፍት እንዲሁም ከአባ ሰላማ ብሎግ Wednesday, February 16, 2011 የተወሰደ ) በአዋልድ መጻሕፍት ወይንም አፖክሪፋ በተባለው መጽሐፍ ግን ይህ የቃልኪዳኑ ታቦት ከሌሎች የመቅደሱ ዕቃዎች ጋራ ወደ ባቢሎን እንደተወሰደ ወይንም እንደተማረከ ራሱ አፖክሪፋው መጽሐፍ መረጃ በመስጠት ይናገረናል ይህንንም ከዚህ በፊት በነበረው ትምህርታችን ያየነው ጉዳይ ስለሆነ ወደዚያ ተመልሼ አልገባም ይሁን እንጂ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ በክብረ ነገሥት መጽሐፍ የተተረከለት ታቦት ከሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኋላ ብዙም ዘመን ሳይቆይ በ16ኛው የይሁዳ ንጉሥ በተሰኘው በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት እዚያው ኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ መታየቱ የክብረ ነገሥትን ትረካ ውድቅ ያደርገዋል ሰሎሞን ለእስራኤል 3ኛው ንጉሥ ሲሆን ሴዴቅያስ ግን 21ኛው ንጉሥ ነው ስለዚህ በሰሎሞን ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ተሰርቆ የመጣው ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ተሰርቆ ከመሄዱ የተነሳ በኢየሩሳሌም የለምና በሴዴቅያስ ጊዜ እንዴት ወደ ባቢሎን ተማርኮ ሊሄድ ቻለ ?እንደገናስ ወደ ኢትዮጵያ ተሰርቆ ነው የሄደው ካልን በባቢሎናውያን ተማርኮ የሄደው ከኢትዮጵያ ነው ? ወይስ ከኢየሩሳሌም ? የሚለውን ያልተመለሰና ሊመለስም የማይችል ጥያቄ አስነስቷል ከዚህም ሌላ የታሪክ መፋለስን ያስከተለና የመጽሐፍቅዱሱንም እውነት ያልጠበቀ በመሆኑ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በቀዳማዊ ምኒሊክ ታቦቱ የመጣ ነው ለማለት አንችልም ታቦቱም ወደ ኢትዮጵያ የመጣ አይደለም ታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶአል የሚለውም ታሪክ አፈ ታሪክና የቅብብሎሽ ወሬ ከሚሆን ውጪ ፍጹም ስሕተት ነው እንደገናም ይህ የክብረ ነገሥት ደራሲ ይህን ልብ ወለድ ታሪክ ለምን መጻፍ እንዳስፈለገው ስናጠና ደግሞ የታሪክ ሽሚያና የቅርስ ባለቤትነትንም የመሆን ፍላጐትን የሚያሳየን ሆኖ አግኝተነዋል ከዚህም ሌላ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትን ለማስፋፋት የታለመ ፖለቲካዊ ሂደት መሆኑንም ያመላክተናል ይሁን እንጂ በቀዳማዊ ሚኒሊክ ምክንያት ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትን ተቀዳጅተናል ብለን ብናስብ እንኳ ይኸው ሰሎሞናዊ ክብረ መንግሥት ወደ ኢየሱስ እስካልመራንና ኢየሱስንም የሕይወታችን ባለቤት እንድናደርገው እስካልረዳን ድረስ በራሱ ክብረ መንግሥታችን ሰለሞናዊ ነው ማስባሉ ትምክህት ከሚሆንብን በስተቀር የሚያስገኝልን ጥቅም የለውም ይህ የብሉይ ኪዳኑ ታቦት እንኳን ለእኛ ለእስራኤላውያኑም አስፈላጊያቸው እንዳልሆነ ኤርምያስ በትንቢቱ ተናግሮአል ትንቢተ ኤርምያስ 3 ፥ 16 ይህንንም የተናገረበት ምክንያት በባቢሎን የምርኮ ዘመን የነበረው ነቢዩ ኤርምያስ ከንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ የባቢሎን ምርኮ እስከመጣበት እስከ ንጉሥ ሴዴቅያስ ዘመን ድረስ የነበረ ነቢይ በመሆኑ ነው ኤርምያስ 1 ፥ 15 ፤ 2ኛ ዜና 36 ፥ 11 _ 23 ፤ ኤርምያስ 1 ፥ 1 _ 3 ን ልንመለከት እንችላለን ከዚህ የተነሣ ዘሩባቤል ባሰራው በሁለተኛው ቤተመቅደስ ውስጥ ታቦቱ አልነበረም መጽሐፈ ዕዝራ ከምዕራፍ 3 _ ምዕራፍ 6 ይመልከቱ ከዚህም ሌላ የቃልኪዳኑ ታቦት የእስራኤል ታሪክ ሆኖ ሳለ እኛ ግን በድፍኑ የእኛው የራሳችን ነው ስንል በሌላ ሕዝብ ታሪክ መታበዩ ደግሞ ራሱን የቻለ ትልቅ ስሕተት ሲሆን እንደገናም እኛኑ ራሳችንን ትዝብት ላይ ከሚጥለን በቀር የሚፈይድልን ነገር የለም በኢዮስያስ ዘመን በትከሻችሁ ላይ መሸከም አይሆንባችሁም የተባለበትን ምክንያት ደግሞ እንደሚከተለው አቀርባለሁ ኢዮስያስ ለሰሎሞን 16ኛው ንጉሥ ነበር ከኢዮስያስ በፊት ነግሦ የነበረው ምናሴ የቤተመቅደሱን ዕቃ አውጥቶ በውስጡ ጣኦት አስቀምጦ ነበረና 2ኛ ዜና 33 ፥ 8 በዚህም ምክንያት ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው በየቤታቸው ይዞሩ ነበር ታድያ ከምናሴ ቀጥሎ የተሾመው ኢዮስያስ ምናሴ የተከለውን የጣኦት ምስል ያፈራረሰና ታቦቱንም ወደ ቤተመቅደሱ እንዲመለስ ያደረገ ንጉሥ በመሆኑ በ2ኛ ዜና 35 ፥ 3 መሠረት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን አገልግሉ …… የሚል ቃል ተነገረ ከዚህ ቃል በኋላ ነው እንግዲህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ታቦትን ተሸክሞ ማውጣት የቀረው እንደገናም ዘሩባቤል ባሰራው ቤተመቅደስ ውስጥም ታቦት የሚባል ነገር የለም ፣ በታቦቱም ላይ የተደረገ አምልኮት አልነበረም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የክፍል አስራ ስድስት ትምህርታችን እንግዲህ ይህን ይመስል ነበር በክፍል አስራ ሰባት የመጨረሻና የታቦት የማጠቃለያ ትምህርት እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ወይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment