Monday 15 May 2017

ታቦትን ተሸክሞ ማውጣት የቀረው መቼ ነው ( ቊጥር 2 ) 2ኛ ዜና መዋዕል 35 ፥ 3 — 6 ክፍል አስራ ሦስትታቦትን ተሸክሞ ማውጣት የቀረው መቼ ነው ( ቊጥር 2 ) እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ ፦ ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ሸክም አይሆንባችሁም …………………………… 2ኛ ዜና መዋዕል 35 ፥ 3 — 6 ክፍል አስራ ሦስት የተወደዳችሁ ቅዱሳን በዚህ በክፍል አስራ ሦስት ትምህርት ታቦት የምናወጣበት ምክንያት በፊልጵስዩስ 2 ፥ 10 _ 11 መሠረት በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያለ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ይንበረከካል ምላስም ለእግዚአብሔር አብ ክብርን ይሰጣል ስለሚል ይህ ቃል ደግሞ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ እንደገናም በራዕይ 2 ፥ 17 ላይ ድል ለነሳው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል ይላልና በዚህ መሠረት ቅዱስ ስሙ በተጻፈበት ከነጭ ድንጋይ በተሠራው በጽላቱ ፊት ለቅዱስ ስሙ መስገድ ታላቅ የመንፈስ ጥበብ እንጂ ሞኝነት አይደለም ምንአልባትም ስለታቦት ፣ ስለ ጽላት ባለማወቅ በአጠቃቀሙ በኩል የሚሳሳቱ አባቶችን እናቶችን ወንድሞችንና እህቶችን በተገቢው መንገድ ማስተማር ተገቢ ነው እንላለን በማለት ያስተምራሉ በዚህ ወስጥ ግን እውነተኛውን መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርት ስናይ እንዲህ አይደለም በመጀመርያ ታቦትን ተሸክመን ማውጣት እንደሌለብን በ2ኛ ዜና መዋዕል 35 ፥ 3 — 6 ላይ መጽሐፍቅዱሳችን በሚገባ ተናግሮናል ሲቀጥልም በፊልጵስዩስ 2 ፥ 10 _ 11 ላይ የተጻፈው ቃል በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ብቻ ታቦት አውጥተን ለታቦት መስገድ አለብን ብለን ማሰብ የለብንም እንደገናም በዚሁ በፊልጵስዩስ 2 ፥ 10 _ 11 ላይ የተጻፈው ቃል በታቦቱ ላይ ባይጻፍም ጊዜው የሐዲስ ኪዳን ጊዜ በመሆኑ ጌታ ሕጉን በልቡናቸው ላይ እጽፋለሁ ብሏልና ቃሉ በልባችን ላይ የተጻፈ በመሆኑ በአገኘነው አጋጣሚና በየትኛውም ቦታ ለኢየሱስ እንበረከካለን አምልኮውም ዛሬ በሐዲስ ኪዳን የመንፈስ አምልኮ ስለሆነ እግዚአብሔርን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእውነትና በመንፈስ እናመልከዋለን በራዕይ 2 ፥ 17 ላይ ግን ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአልና በማለት ቃሉ ስለሚናገር ይህንን በማየት ታቦት አውጥተን ለታቦት እንሰግዳለን ማለታቸው ትክክለኛ ትርጓሜ አለመሆኑን በመግለጥ እውነተኛውን ሃሳብ ከእግዚአብሔር ቃል እውነት አውጥቼ አብራርቻለሁ ይህንን እውነት ለማወቅ ቪዲዮውን መከታተል በብዙ ይጠቅማል ሌላው ከጊዜ ማነስ የተነሣ ያላብራራሁላችሁ ታቦት ከቤተ መቅደስ ማውጣትና አለማውጣት መጽሐፍቅዱሳዊ ከመሆኑም በተጨማሪ ቀኖና ቤተክርስቲያን መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል ነገር ግን ታቦት ከቤተመቅደስ መውጣት እንደሌለበት በ2ኛ ዜና መዋዕል 35 ፥ 3 — 6 ላይ የተጻፈልን ቢሆንም ታቦት አለማውጣት ግን መጽሐፍቅዱሳዊ እንጂ ቀኖናዊ አለመሆኑን ከቃሉ መረዳት እንችላለን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቅዱሳን እንግዲህ ጽሑፉንም አንብቡ ቪዲዮውንም ተከታተሉ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment