Monday 29 May 2017

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: የትምህርት ርዕስ የቃልኪዳኑ ታቦት              ...የትምህርት ርዕስ የቃልኪዳኑ ታቦት

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: የትምህርት ርዕስ 





የቃልኪዳኑ ታቦት 








             ...
: የትምህርት ርዕስ  የቃልኪዳኑ ታቦት                                                      በአብ በወልድና በመ ...
የትምህርት ርዕስ 






የቃልኪዳኑ ታቦት 

Image result for ታቦት




Image result for ark of covenant



Image result for arrow
                                             

     
በአብ በወልድና በመ







የዛሬው የሐዲስ ኪዳኑ ታቦታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው 

ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅጽ ይትሜሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ 


ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውጪ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት አካላዊ ቃልን ይመስልልናል
( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት )












 


































Image result for arrow
Image result for jesus christ





ወኮነ አራቄ ለሐዲስ ኪዳን በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሆሙ ለመሐይምናን ወለሕዝብ ንጹሐን 


የሐዲስ ኪዳን አስታራቂያችን ሆነ በከበረው ደሙ ፈሳሽነት አማኞችንና ሕዝብን አነፃ


( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት )











በአብ በወልድና በመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ስም አሜን


የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ጌታ እግዚአብሄር ረድቶን 

በእናንተም በወገኖች ጸሎትና እገዛ ሰሞኑን ለተከታታይ ወራትና ሳምንታት እንማማርበት 

የነበረውን የቃልኪዳኑ ታቦት በሚል አርዕስት ያቀረብኩትን ዛሬ በጥሩ ሁኔታ አጠናቀን 

ጭርሰናል አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር 

ምስጋና ይድረሰው አሜን ከዚህ በመቀጠልም የተማማርንባቸውን ንኡሳን አርዕስቶች 

እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁና  ጊዜ ስታገኙ በአርእስቱ መሠረት እየገባችሁና 

የተለቀቁትን ቪዲዮዎች እየከፈታችሁ እንድትሠሙ ከዚህ እንደሚከተለው በዝርዝር 

ተዘጋጅቶ ቀርቦላችኋል  



1ኛ የታቦቱ ምሥጢር ታቦት ምንድነው ? ( ክፍል አንድ )

2ኛ ) ታቦት ከምን እንደተሠራ አጀማመሩና ምሳሌነቱ ( ክፍል ሁለት )

3ኛ ) የታቦቱ አገልግሎት ( ክፍል ሦስት )

4ኛ ) በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንትዋ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት 

ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው  ማስረጃዎች ( ክፍል አራት )

5ኛ ) የእሥራኤልና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1 ) በክህነቱ  ነው ( ክፍል 

አምስት

6ኛ ) የእሥራኤልና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 2 ) በሕጉ ነው ( ክፍል 

ስድስት )

7ኛ ) ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቷል ( ክፍል ሰባት

8ኛ ) እግዚአብሔርን ያለማወቅ ወራት ለዘላለም ይወገዳል ( ክፍል ስምንት )

9ኛ ) በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ጥብቅ ግነኙነት ይደረጋል ( ክፍል ዘጠኝ

10ኛ ) የኃጢአት ይቅርታ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር እውነት ሆኗል ( ክፍል አስር

11ኛ ) የሙሴን ሕግ ያልተከተለ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ያለ የታቦትና የጽላት 

አሠራር ( ክፍል አስራ አንድ

12ኛ ) ታቦትን ተሸክሞ ማውጣት ማውጣት የቀረው መቼ ነው ? ( ክፍል አስራ ሁለት

)

13ኛ ) ታቦትን ተሸክሞ ማውጣት ማውጣት የቀረው መቼ ነው ? ( ክፍል አስራ ሦስት _ )

14ኛ ) ዛሬ የቃልኪዳኑ ታቦት አለ ወይ ? ( ክፍል አስራ አራት

15ኛ ) የቃልኪዳኑ ታቦት ዛሬ አለ ወይ ? ስለ ቃልኪዳኑ ታቦት የአዋልድ መጻሕፍት ምን 

ይሉናል ? ድርሳነ ዑራኤልስ ? ( ክፍል አስራ አምስት

16ኛ ) የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል አንድ ትረካ ( ክፍል 

አስራ ስድስት

17ኛ ) የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል ሁለት ትረካ ( ክፍል 

አስራ ሰባት

ወድ የትምህርቱ ተከታታዮች ወገኖቼ !! የትምህርቱ ቅደም ተከተልና ንዑሳን አርዕስቶቹ 

እነዚህ ናቸው  በፌስቡክ ላይቭ ተላልፈው በዩቲዩብ የተለቀቁ ስለሆኑ ትባረኩበታላችሁ 

ከዚህም ሌላ ሌሎችንም ልታስተምሩበት ስለምትችሉ በትምህርቱ ተጠቀሙ ስል 

ላበረታታችሁ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ









Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ




yonasasfaw8@gmail.com



የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል ሁለት ትረካና የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ( ክፍል አስራ ሰ...የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል ሁለት ትረካና የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ክፍል አስራ ሰባት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ይህ የቃልኪዳኑ ታቦት ትምህርት የመጨረሻውና የማጠቃለያው ትምህርት ነው በዚህ ትምህርት ውስጥ የምንመለከተው ከክብረ ነገሥት ጋር በተያያዘ መልኩ ከጥቂት ዓመታት በፊት ፕሮፌሰር ግራንት ጄፈሪ የተሰኙ ካናዳዊ የመጽሐፍቅዱስ ምሁር "Armageddon :- Appointment of Destiny " በተሰኘው መጽሐፋቸውና እንደዚሁም " The Ark of the Covenant and the red Heifer " በሚል ባስቀረጹት ትምህርታዊ ቪዲዮአቸው የቃልኪዳኑ ታቦት ስለሚገኝበት ሥፍራ ወደፊትም ስለሚኖረው መለኮታዊ ሚና ሰፊ የሆነ ታሪካዊ ትንታኔና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፕሮፌሰሩ ይህንን ታሪክ በትንታኔ ሲያቀርቡ አቀራረባቸው በክብረ ነገሥት ከተጻፈው ሃሳብ ጋር የተገናኘ ይመስላል ያቀረቡትም በዚህ መልኩ ነበር ወጣቱ ምኒሊክ አባቱን ጎብኝቶና በእሥራኤል የነበረውን ቆይታውን አጠናቆ ሲመለስ ሳለ አባቱ ንጉሥ ሰሎሞን ልጁ ምኒሊክ ከእናቱ ሀገር ከኢትዮጵያ እየመጣ በአይሁዳውያኑ ቤተመቅደስ ውስጥ ለማምለክ ስለሚቸግረውና መንገዱም ሩቅ ስለሆነ ለአምልኮት ሥርዓት ይዞት የሚሄደውን ታቦት ቅጂ ወይንም ት መሣሣዩን አሰርቶለት ነበር ይሁን እንጂ ምኒሊክ የአባቱን ከእግዚአብሔር መንገድ ሕግና ሥርዓት መራቅ ስለተመለከተና ልቡም በአሕዛባውያን ሴቶች ጣኦቶቻቸው ፍቅር በመነደፉ እጅጉን አዝኖ ትክክለኛውን ታቦት ከአይሁዳውያኑ ቤተመቅደስ ሰርቆ ወደ አክሱም ይዞ እንደመጣ ፕሮፌሰሩ አብራርተዋል ታድያ ታሪኩን በታሪክ ደረጃ ብንቀበለውም ከዚህ በፊት እንደተማርነው ታቦቱ በኢዮስያስ ዘመን በቤተመቅደስ ውስጥ ስለነበር በሰሎሞን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጣ ለማለት አንደፍርም 2ኛዜና መዋዕል 35 ፥ 3 እንደገናም በሴዴቅያስ ዘመን ወደ ባቢሎን ተማረከ ብንል እንኳ በሰሎሞን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ሄዶአል ብለናልና የተማረከው ከኢትዮጵያ ነው ? ወይንስ ከኢየሩሳሌም ? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳብናልና የታሪክ መፋለስን ስለሚያስከትል ልክ አይሆንም 2ኛዜና መዋዕል 36 : 11— 23 እንደገናም ከእንግዲህ የእሥራኤል የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይጠሩትም አያስቡትም ተብሎ በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረ ትንቢት ስላለ ትንቢተ ኤርምያስ 3 ፥ 16 ዘሩባቤል ባሰራው ቤተመቅደስ ታቦቱ አልነበረምና ለእሥራኤል ያልሆነ ታቦት ለእኛም አይሆንም ከዚህም ሌላ በሐዲስ ኪዳን ሕጉን በልቡናቸው አኖራለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ በማለት የተናገረ ነውና ዛሬ ሕጉ የተጻፈው በእኛ በልቡናችን ሰሌዳ ላይ እንጂ በግራሩ እንጨት ላይ አይደለም ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 13 ሌላው የሰው ወርቅ አያደምቅ እንደተባለው ታቦት የተሰጠው ለእሥራኤል ሕዝብ በመሆኑ የሌላ ሕዝብ ታሪክ ለራሱ ለዛው ሕዝብ እንጂ ለእኛ የሚጠቅመን ነገር አይደለም መጽሐፍቅዱሳዊው ምሁር ፕሮፌሰር ግራንት ጄፈሪ እንዳሉትም ታቦቱ ከእሥራኤል ኮፒ ሆኖ ወይንም ቅጂ ሆኖ ተመሣሣዩ መጣ ቢባል እንኳ አለበለዚያም ደግሞ ሰሎሞን በአሕዛብ ሴቶች ፍቅር በመነደፉ ምክንያት ልጁ ሚኒሊክ ቅር ተሰኝቶ ዋናውንና ኦርጂናሉን ታቦት ያመጣው ነው ብንልም ለእኛ በአሁኑ ሰዓት ወደ አዲሱ ኪዳናችን ወደ ኢየሱስ የተሸጋገርን በመሆናችን የሚጠቅመን ነገር የለም አዲሱ ኪዳናችን ኢየሱስ ወደ እኛ ወደ እያንዳንዳችን ሲመጣ ቅጂ ሆኖ ወይንም ኮፒ ሆኖ ከዚህም ሌላ ተሠርቆም የመጣ አይደለም መጽሐፍቅዱሳችን አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው ለሚጠሩትም ባለጠጋ ነው ስላለን የሁላችን ጌታ ሊሆን ወደ እያንዳንዳችን መጣ ስለዚህ ይሄ ጌታ የአይሁዳዊውም የግሪኩም የአሕዛቡም ሆነ የጨዋውና የባርያውም ጌታ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ለሚጠሩትም ባለጠጋ ነው በመሆኑም ይሄ ጌታ እንደ ብሉይ ኪዳኑ የቃል ኪዳን ታቦት ለእሥራኤል ብቻ የሆነ አይደለም ሮሜ 10 ፥ 8 _ 13 ከዚህ የተነሳ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስተሠርይ የእግዚአብሔር በግ እነሆ ተባለ ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 29 ከዚህ ባሻገርም በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ባለ መለያየት ምክንያት ስለ አሕዛብ ሊናገረን ወዶ ልባቸውን በእምነት ሲያነጻ በእኛ እና በእነርሱ መካከል አንዳች አለየም ተባለ ሌላው ቀርቶ አብርሃም ሳይገረዝ በነበረ እምነቱና ከተገረዘም በኋላ ለሁሉም አባት የተባለ ነበረ ሮሜ 4 ፥ 11 እና 12 ን ይመልከቱ ትምህርታችን እንግዲህ በጥቅሉ ይህንን ይመስላል በሰላም ጀምረን እንድናጠናቅቅ የረዳንን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

Saturday 27 May 2017




የጾምና የጸሎት ጥሪ



ጽራህ ኀቤየ ወአወስአከ ወእነግር አቢያተ ወኃይላተ ዘኢተአምሩ 


ወደ እኔ ጩኽ እኔ እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ 

ነገርን አሳይሃለሁ
        
                                           ትንቢተ ኤርምያስ 33 : 3







በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ስም አሜን







የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን ሰንብታችኋል 

እግዚአብሔር ረድቶን የቃልኪዳኑ ታቦት በሚል አርዕስት የቃልኪዳኑ ታቦት ምስጢር ምን 

እንደሆነና ዛሬ ላይ በሐዲስኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ መሆኑን በስፋት ተማምረናል 

ይህንንም ትምህርት በእግዚአብሔር ጸጋ እንድናጠናቅቅና ከተሰጠውም ትምህርት 

ተገቢ የሆነውን መንፈሳዊ እውቀት እንድንገበይ የረዳንን እግዚአብሔርን ከልብ 

እናመሰግነዋለን  በቀጣዩ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ 

ቤተክርስቲያን እንዴት ይታያል ? ሥዕል በቤተክርስቲያን እንዴት ተጀመረ ? የሚሉትንና 

ሌሎችንም በሥዕል ዙርያ የተነገሩ ሃሳቦችን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት እያየን 

እንማማራለን  በመቀጠል ግን ከዚህ በፊት በተማማርንባቸውም ይሁን ወደፊት 

በምንማማራቸው መጽሐፍቅዱሳዊ እውነቶች ዙርያ እነዚህን የመሣሠሉ እውነተኛና 

መጽሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶች ሰርጸው በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት 

የቤተክርስቲያኒቱን ሕይወትና ማንነት የሚለውጡበት ጊዜ እንዲሆን ጥንታዊትና 

ሐዋርያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችንም በእነዚህ ቃሎች  ተለውጣና በዚሁ 

በእውነተኛው መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ወደ ጥንተ መሠረቷ ተመልሳ 

ወንጌልን ብቻ እንድትሰብክ በብርቱ ወደ እግዚአብሔር የምንጮህበትና የምንማልድበት 

ጊዜ ይሆናል ይህ ጊዜ የሚሆነው በመደበኛው የትምህርት ፕሮግራማችን ሐሙስ ጁን 2  

10 ሰዓት ላይ  ነው መቅረት አይፈቀድም መጸለይ የምትፈልጉ ሁሉ በዚህ ፕሮግራም ላይ 

ተገኝታችሁ መጸለይ ምትችሉ መሆናችሁንም ከወዲሁ እናስታውቃለን ከዚህም ሌላ 

ጸሎት የሚያስፈልጋቸውና መጸለይም የሚፈልጉ ሁሉ የዚሁ ፕሮግራም እድምተኞች 

እንዲሆኑ በመጋበዝ እንድትተባበሩን ከትልቅ አክብሮት ጋር እንጠይቃለን ጌታ 

ዘመናችሁን ይባርክ 


ጸ                                                                 


                                                                                                                                                 



                                                               
                                                                                                                                






ት                                                                ት






Image result for ጸሎት




                                                 
                                                               
Image result for bible


                 
Image result for arrow














አቤቱ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ 

       ሰቆቃወ ኤርምያስ 5 ፥ 21
Image result for ethiopian orthodox church

                                                 
                                                                       


ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን 


 Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry



ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ


http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39



yonasasfaw8@gmail.com