የትምህርት ርዕስ
በአብ በወልድና በመ
የዛሬው የሐዲስ ኪዳኑ ታቦታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅጽ ይትሜሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ
ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውጪ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት አካላዊ ቃልን ይመስልልናል
( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት )
ወኮነ አራቄ ለሐዲስ ኪዳን በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሆሙ ለመሐይምናን ወለሕዝብ ንጹሐን
የሐዲስ ኪዳን አስታራቂያችን ሆነ በከበረው ደሙ ፈሳሽነት አማኞችንና ሕዝብን አነፃ
( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት )
የሐዲስ ኪዳን አስታራቂያችን ሆነ በከበረው ደሙ ፈሳሽነት አማኞችንና ሕዝብን አነፃ
( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት )
በአብ በወልድና በመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ስም አሜን
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ጌታ እግዚአብሄር ረድቶን
በእናንተም በወገኖች ጸሎትና እገዛ ሰሞኑን ለተከታታይ ወራትና ሳምንታት እንማማርበት
የነበረውን የቃልኪዳኑ ታቦት በሚል አርዕስት ያቀረብኩትን ዛሬ በጥሩ ሁኔታ አጠናቀን
ጭርሰናል አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር
ምስጋና ይድረሰው አሜን ከዚህ በመቀጠልም የተማማርንባቸውን ንኡሳን አርዕስቶች
እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁና ጊዜ ስታገኙ በአርእስቱ መሠረት እየገባችሁና
የተለቀቁትን ቪዲዮዎች እየከፈታችሁ እንድትሠሙ ከዚህ እንደሚከተለው በዝርዝር
ተዘጋጅቶ ቀርቦላችኋል
1ኛ የታቦቱ ምሥጢር ፣ ታቦት ምንድነው ? ( ክፍል አንድ )
2ኛ ) ታቦት ከምን እንደተሠራ ፣ አጀማመሩና ምሳሌነቱ ( ክፍል ሁለት )
3ኛ ) የታቦቱ አገልግሎት ( ክፍል ሦስት )
4ኛ ) በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንትዋ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት
ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ክፍል አራት )
ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ክፍል አራት )
5ኛ ) የእሥራኤልና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1ኛ ) በክህነቱ ነው ( ክፍል
አምስት )
አምስት )
6ኛ ) የእሥራኤልና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 2ኛ ) በሕጉ ነው ( ክፍል
ስድስት )
ስድስት )
7ኛ ) ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቷል ( ክፍል ሰባት )
8ኛ ) እግዚአብሔርን ያለማወቅ ወራት ለዘላለም ይወገዳል ( ክፍል ስምንት )
9ኛ ) በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ጥብቅ ግነኙነት ይደረጋል ( ክፍል ዘጠኝ )
10ኛ ) የኃጢአት ይቅርታ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር እውነት ሆኗል ( ክፍል አስር )
11ኛ ) የሙሴን ሕግ ያልተከተለ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ያለ የታቦትና የጽላት
አሠራር ( ክፍል አስራ አንድ )
አሠራር ( ክፍል አስራ አንድ )
12ኛ ) ታቦትን ተሸክሞ ማውጣት ማውጣት የቀረው መቼ ነው ? ( ክፍል አስራ ሁለት _
ሀ )
ሀ )
13ኛ ) ታቦትን ተሸክሞ ማውጣት ማውጣት የቀረው መቼ ነው ? ( ክፍል አስራ ሦስት _ ለ )
14ኛ ) ዛሬ የቃልኪዳኑ ታቦት አለ ወይ ? ( ክፍል አስራ አራት )
15ኛ ) የቃልኪዳኑ ታቦት ዛሬ አለ ወይ ? ስለ ቃልኪዳኑ ታቦት የአዋልድ መጻሕፍት ምን
ይሉናል ? ድርሳነ ዑራኤልስ ? ( ክፍል አስራ አምስት )
ይሉናል ? ድርሳነ ዑራኤልስ ? ( ክፍል አስራ አምስት )
16ኛ ) የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል አንድ ትረካ ( ክፍል
አስራ ስድስት )
አስራ ስድስት )
17ኛ ) የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል ሁለት ትረካ ( ክፍል
አስራ ሰባት )
አስራ ሰባት )
ወድ የትምህርቱ ተከታታዮች ወገኖቼ !! የትምህርቱ ቅደም ተከተልና ንዑሳን አርዕስቶቹ
እነዚህ ናቸው በፌስቡክ ላይቭ ተላልፈው በዩቲዩብ የተለቀቁ ስለሆኑ ትባረኩበታላችሁ
ከዚህም ሌላ ሌሎችንም ልታስተምሩበት ስለምትችሉ በትምህርቱ ተጠቀሙ ስል
ላበረታታችሁ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ
እነዚህ ናቸው በፌስቡክ ላይቭ ተላልፈው በዩቲዩብ የተለቀቁ ስለሆኑ ትባረኩበታላችሁ
ከዚህም ሌላ ሌሎችንም ልታስተምሩበት ስለምትችሉ በትምህርቱ ተጠቀሙ ስል
ላበረታታችሁ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ
ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
yonasasfaw8@gmail.com
No comments:
Post a Comment