Monday 24 April 2017

ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል ( ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) ክፍል ሰባትወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል ( ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) ክፍል ሰባት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ዛሬ የክፍል ሰባት ትምህርታችን ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል የሚል ነው ይሄ የሚሻል ተስፋ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ የሆነበት አዲሱ ኪዳናችን ነው ( ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 12 ፤ ኤርምያስ 31 ፥ 31 _ 34 ) ይመልከቱ ታድያ ይሄ አዲሱ ኪዳናችን ጌታ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ( በዘጸአት 24 ፥ 7 _ 8 ) ከተጻፈልን በሙሴ አማካኝነት ከተሰጠው ኪዳን ይበልጣል የተመሠረተውም በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው ( ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 12 ፤ ዕብራውያን 12 ፥ 24 ፤ ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) በብሉይ ኪዳኑ ኪዳን የተጻፈልን አልደረሳችሁምና የሚል ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ በሆነበት በሐዲሱ ኪዳናችን ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ………… ደርሳችኋል የሚል ተጽፎልናል በመሆኑም ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል ማለታችን ከዚህ እውነት ተነስተን ነው ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ይሄ ኪዳን መብለጡና የተሻለ መባሉ በዚህ የሚያበቃ አይደለም ወደ አምስት የሚደርሱ ነጥቦች አሉ ለዛሬ የተመለከትናቸው ሁለቱን ነጥቦች ሲሆን በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜያችን ከእነዚህ የቀጠሉትን ሦስቱን ነጥቦች እንደሚከተለው በየተራ እንመለከታቸዋለን አምስቱ ነጥቦችም እንዲህ የሚሉ ናቸው 1ኛ ) የእግዚአብሔር ሕግ የልብና የሕሊና መርህ ሆኖ በመምጣቱ 2ኛ ) ሕዝቡ ፈቃዱን በመፈጸሙ ደስ የሚሰኝበት በመሆኑ 3ኛ ) እግዚአብሔርን ያለማወቅ ኃጢአት ለዘላለም ይወገዳል 4ኛ ) በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ጥብቅ ግንኙነት የተደረገ እና ወደፊትም በብዙዎች ሕይወት የሚደረግ በመሆኑ 5ኛ ) የኃጢአት ይቅርታ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር እውነት ሆኖአል የተወደዳችሁ ወገኖች ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ የሆነበት አዲሱ ኪዳናችን በሙሴ አማካኝነት ከተሰጠው ኪዳን ይልቅ መሻሉና መብለጡ ከእነዚህ እውነቶች የተነሳ ነው የትምህርቱ ጠቅላላ ሃሳብ እንግዲህ ይህንን ይመስላል ቪዲዮውን ስሙት ተባረኩበት ለሌሎችም ሰዎች ሼር አድርጉት በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የቀረውን እቀጥላለሁ እስከዚያው ሰላም ሁኑ የምላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment