Saturday 15 April 2017

የታቦቱ አገልግሎት ( ክፍል ሦስት ) የታቦቱ አገልግሎት ክፍል ሦስት በክፍል ሦስት ትምህርት የታቦቱ አገልግሎት በሚል ንዑስ አርዕስት የተነሳሁ ሲሆን በዚህ ትምህርት ውስጥ ፦ 1ኛ ) ታቦቱን በተመለከተ አሰርቱ ቃላት የተጻፈባቸው የሁለቱ ጽላቶች ማኖርያ መሆኑ 2ኛ ) ከእስራኤል መሪዎች ጋር የእግዚአብሔር መገናኛ ነበር 3ኛ ) በዚህም ምክንያት ታቦቱ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር 4ኛ ) ሙሴም ታቦቱን አሰርቶ ሲያበቃ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አኖረው የእስራኤልም ሕዝብ ይዘውት ይጓዙ ነበር ይለናል 5ኛ ) ታቦቱ ወኪል የሆነና ሲንቦሊዝም የሆነ በመሆኑ የእስራኤል ጦረኞች በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ የያህዌ መገኘትና ምልክት ነበር 6ኛ ) አሁንም ታቦቱ ምስክርነቱን የሚያሳይና የተሰየመም በመሆኑ በመሠረታዊው ዓላማ ምክንያት ሀ ) የያህዌ ታቦት መሆኑን ለ ) የቃል ኪዳን ታቦት መሆኑን ሐ ) የጥንካሬው ታቦት መሆኑን የሚያሳይ ነው እነዚህን ሃሳቦች ይዘን ወደ ሐዲሱ ኪዳን የኪዳን አገልግሎት ስንመጣ ከቊጥር 1 እስከ 6 በጠቀስኩት ሃሳብ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ እና ደሙ የኪዳናችን መሠረት በመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኛችን ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የመኖሩ ምልክታችን ፣ ይዘነው የምንጓዘው ታቦታችን ፣ የእግዚአብሔር ጉብኝቱ እና መገኘቱ የታየበት ምልክታችን ፣ እግዚአብሔር የተናገረበት ድምጻችንና የቃልኪዳን ታቦታችን እንዲሁም የጥንካሬ ኃይል የተገለጠበት በመሆኑም የጥንካሬው ኃይላችንና ታቦታችን ነው ትምህርቱ በአጭሩ እነዚህን ሃሳቦች በሙሉ ይጠቀልላል በትምህርቱ እንዲባረኩ ቪዲዮውን አዳምጡ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

No comments:

Post a Comment