Thursday 20 April 2017

በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ...በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ክፍል አራት ) 1ኛ ) ቤተክርስቲያኒቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን የነገሠ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ለመሆኑ ማስረጃ ስትሰጥ ቀዳሚሁ ቃል እንዲል ስተረጉመው በመጀመርያ ቃል ነበረ ይለናልና ከአብ ጋር በቅድምና በቃልነት ይመሰገን የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ለብሶ ፣ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኖ የመጣ ቢሆንም እነዚያ ስሞች ከስመ ሥጋዌው ማለትም ከሥጋዌ ስሙ የሚቀድሙ ስሞች በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ለመሆኑ ዋነኛ ማስረጃዎቻችንና ጠቋሚዎቻችን ናቸው ይለናል ትምህርቱ ስሞቹም ሆኑ የትዕዛዛቱ ምስጢራት በቪዲዮ ላይ የተብራሩ ስለሆኑ ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን መስማቱ ይበልጥ ይጠቅማል 2ኛ ) የውጣ ጥንታዊ የግሪክ ቋንቋና አስረኛ ቁጥር ስለሆነች እዝል ፣ ቅጽል የሌላት እንደ ጭራ የቀጠነች በአጻጻፍም ትንሽና ቀጭን በመሆንዋ የአብ ባሕርያዊ ቃል የሆነው ኢየሱስ በአጽባዕተ መንፈስቅዱስ ማለትም በመንፈስቅዱስ ጣቶች ፣ በመንፈስቅዱስ አሠራር በድንግል ማኅጸን እንዲቀረጽ አሰርቱ ቃላትን በጽላቱ ጽፎ በማኖር ነገረን በማለት ከዚያም መልስ ከመወለዱ ጀምሮ ባለ አስተዳደጉ ሁሉ በዮሴፍ ቤት ኢየሱስ ለአባትና ለእናቱ እየታዘዛቸው ያደገ በመሆኑ ድንግል ማርያም ኢየሱስን በመንፈስቅዱስ ምክር ቀርጻ ያሳደገችው መሆኑን ትምህርቱ ይጠቁመናል 3ኛ ) ጽላቱ ከተሰበረ በኋላም እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ፊተኞቹ አድርገህ እነዚህን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጥረብ በማለት በሰበርሃቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ ሲል መናገሩ ምሳሌነቱ ቃሉ የጌታ ምሳሌ በድንጋይ ጽላቶች ላይ የሚጻፉ ቃሎች ከእግዚአብሔር አፍ የወጡ እንደመሆናቸው ሁሉ ጌታችን ኢየሱስም በግብረ አምላካዊና በመንፈስቅዱስ የተገኘ የተጸነሰና የተወለደ መሆኑን እንደገናም ይሄ ጌታ በመንፈስቅዱስ አማካኝነት የተወለደ በመሆኑ በወንድና በሴት የግንኙነት ፈቃድ የተገኘ ወይም የተወለደ ባለመሆኑ እንበለ ዘር የተገኘ ነው ስትል ቤተክርስቲያኒቱ ርቱዕ በሆነው ትምህርቷ ታመሰጥራለች ትናገራለች 4ኛ ) ወኮነ አራቄ ለሐዲስ ኪዳን በማለትም የሰንበት ውዳሴ ማርያምን ለአብነት ጠቅሳ ደሙን በማፍሰስ እና በደሙም በማንጻት የእርሱ የሆኑትን አማኞች ለእግዚአብሔር መንግሥትና ለመንግስተ ሰማያት ያበቃ ወደፊትም የሚያበቃ እውነተኛው የሐዲስ ኪዳን አስታራቂያችን ኢየሱስ መሆኑንም በደስታ ታበስረናለች እነዚህን ማብራርያዎች የጻፍኩት በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት በመስማት የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራችሁና እንድትወዱትም ጭምር ለመርዳት ያዘጋጀሁት ነውና አንብቡት ቪዲዮውንም ስሙት ፣ ተባረኩበት ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

No comments:

Post a Comment