Tuesday, 9 August 2016

ማገልገል Serving

ማገልገል   Serving






እያንዳንዱ ክርስቲያን የአገልግሎትን ሁኔታ ይጠብቃል እግዚአብሔር በስጦታና በችሎታ በጥበብና በብልሃት በመንፈሳዊ ስጦታም እያንዳንዱን ሰው ማዘጋጀት ይፈልጋል እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ዓይነት ስጦታን እንድንጠቀም አጥብቆ ይፈልጋል እንድናገለግለውም ስጦታውን ሰጥቶናል ስናገለግልም የኢየሱስን ዱካ እየተከተልን ልናገለግል ይገባል እንደገናም በቤተክርስቲያን ስናገለግል ለሕይወታችን ቅድሚያ ሰጥተን  በእግዚአብሔር ደስታ ውስጥ መግባትና በመንፈሳዊ ብስለት ማደግ አለብን ስለ አገልግሎት መጽሐፍቅዱስ ምን እንደሚል ለማየት ወደ መጽሐፍቅዱስ ሃሳብ እንመለስ 



በኤፌሶን 2 10 መሠረት በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርነው ምን ለማድረግ ነው ?




በኤፌሶን 4 11 _ 13 በዚህ ምንባብ መሠረት ኢየሱስ ሕዝቡን ለመርዳትና ለማዘጋጀት ሲል የሰጠው ምን ነበር ?




ለአገልግሎት ሥራስ የተዘጋጀው እና የታጠቀው ማን ነው ?



የእግዚአብሔር ሕዝብ ለአገልግሎቱ ሥራ የተዘጋጀ ሲሆን ውጤቱ ምንድነው ?





ሮሜ 12 6 _ 8 1 ጴጥሮስ 4 7 _ 11 ይነበብ 






በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት ሁሉም ክርስቲያን አንድ ዓይነት ስጦታ አላቸውን ?




እግዚአብሔር በሰጠን ስጦታ ምን ማድረግ ያስፈልገናል ?




ስለ አገልግሎት ኢየሱስ ምን እንደተናገረ በመቀጠል እንመልከት 


የዮሐንስ ወንጌል 13 1 _ 17 እንመልከት 






ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ተግባራዊ እያደረገ ነበር ወይንስ መንፈሳዊ ትምህርትን ለማስተማር እየሞከረ ነበር ?




አንዱ የአንዱን እግር ሊያጥብ ያስፈልገዋል ሲል ኢየሱስ ምን ለማለት የፈለገ ነው ?




በቊጥር 17 መሠረት በረከትን ስለሚያመጣው ነገር ኢየሱስ ምን አለ ?




የዮሐንስ ወንጌል 12 26 ይነበብ




ኢየሱስ የትኛውን ምሣሌ በእርግጠኝነት መከተል እንዳለብን ተናገረ ?




አባቱን ስለማክበር ኢየሱስ ምን አለ ?




የማርቆስ ወንጌል 10 42 _ 45 ይነበብ




በእግዚአብሔር ዓይን ትልቅ የመሆን አንዱ ጉዳይ እንዴት ነው ?




ኢየሱስ ምሳሌያችን ነው ታድያ ኢየሱስ ለማገልገል የመጣ ነው ወይንስ እንዲያገለግሉት ?




ኤፌሶን 6 7 _ 8 ይነበብ 



በሙሉ ፈቃድና ልብ እንድናገለግል የነገረን ማን ነው በእውነተኝነትስ  ያገለገለ ማን ነው ?




የሉቃስ ወንጌል 10 38  _ 42  ይነበብ




ማርታ እያገለገለች ሳለች ስሕተት ነበረች ?




ማርያም በኢየሱስ የታዘዘችው ስለምን ነበር  ?




ከዚህ ምንባብ ምን ዓይነት ጠቃሚ ትምህርት ልንማር ችለናል ?







ስንደመድመው በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እርሱ የሰጠንን ችሎታና ስጦታ በመጠቀም እርሱን ለማገልገል ጊዜን ማዘጋጀት አለብን እርሱን በሕይወታችን መጀመርያ እንድናደርግ እግዚአብሔር አጥብቆ ይፈልጋል ይህ ማለት ለማገልገል ጊዜን መውሰድ ማለት ነው ጠቃሚ በሆነው የሕይወታችን ክፍል ሌሎችን ስናገለግል እና የኢየሱስን ዱካ ስንከተል በመንፈሳዊ ሕይወታችን እናድጋለን በአገልግሎት ሌሎችን ስንባርክ እግዚአብሔር ደግሞ እኛን ይባርከናል 

No comments:

Post a Comment