Sunday 7 August 2016

መጽሐፍቅዱስን ማንበብ


መጽሐፍቅዱስን ማንበብ 





መጽሐፍቅዱስ ሲጻፍልን ለእኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው እንደገናም ትምህርት ሰጪ እና ለእኛም የመመርያ  መጽሐፋችን ነው መጽሐፉ ሲገለጥልንም እንዴት ለእግዚአብሔር መኖር እንዳለብን ያስተምረናል እግዚአብሔር ለእኛ በበለጠ በጋራ የተናገረን በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ ነው መጽሐፍቅዱስ የሚለውን ማወቅ ስሕተት እንዳይኖር ለመከላከልና እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ለመረዳት ነው 


የማቴዎስ ወንጌል 4 4  ይነበብ 







ሰው በምን እንዲኖር ኢየሱስ ተናገረ ?



በተፈጥሮ ምግብና በመንፈሳዊ ምግብ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው ?




ነፍሳችንን ምን እንመግባታለን ?



አካላዊና ውጪያዊ ሰውነታችንን ሁልጊዜ የምንመግብ ከሆነ እንዴት ሁልጊዜ ዘላለማዊ ነፍሳችንን ልንመግባት አያስፈልገን ?




የሉቃስ ወንጌል 8 4 _ 15 ስለ ዘሪው ታሪክ ይናገራል 




በሉቃስ ወንጌል 8 12 በመንገድ ዳር  ለብቻው የወደቀው ዘር ምን ሆነ ? 



ሰይጣን ከልባቸው ቃሉን እንዴት ወሰደ ?




በቊጥር 13 መሠረት  በዓለቱ ላይ የወደቀው ቃሉ ምን ሆነ ? 




በቊጥር 14 መሠረት በእሾህ መካከል የወደቀው ዘር ምን ሆነ ? 




በቊጥር 15 መሠረት በመልካም መሬት የወደቀውን ዘር ጨምሮ ከእነዚህ ከሦስቱ የትኛው ነው እውነተኛው 




የማርቆስ ወንጌል 7 6 _ 8 ይነበብ 





ኢየሱስ በተናገረው መሠረት የትኛው ተሸካሚ የበለጠ ሥልጣን አለው የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ወይስ የሰው ባሕል ልምድና ወግ ?



የሉቃስ ወንጌል 11 27 _ 28 ይነበብ




በእነዚህ ቊጥሮች ውስጥ ኢየሱስ ተናግሮ ያመጣው በረከት ምንድነው ? 



የዮሐንስ ወንጌል 8 51 ይነበብ 



ቃሉን ለታዘዙ ለእነዚያ ኢየሱስ የሰጣቸው ተስፋ ምን ነበር ?




የዮሐንስ ወንጌል 12 47 _ 50 




በፍጻሜው ሰዓት በሕዝቦች ላይ ሲፈርድ ኢየሱስ ምን አለ ?





ስንደመድመው በጸሎትና መጽሐፍቅዱስን በማንበብ በየቀኑ ከእርሱ ጋር ጊዜ ስታጠፋ እግዚአብሔር በብዙ ይባርክሃል የሁልጊዜ መሰጠት ለአንተ ለራሱ ከፈጠረህ ከእግዚአብሔር ጋር በግንኙነት የምትሄድበትና የበለጠውን የቀንህን የደስታ ክፍል የሚያመጣልህ ነው

No comments:

Post a Comment