ጠቃሚ ምክር
( ክፍል አራት )
ከሰማኋቸውና ካነበብኳቸው
የዕለት እንጐቻ
« ፎከስድ የሆነ ውሃ እኮ ድንጋይ ይሰብራል »
ከኢንጂነር ዘማሪ ግዛቸው የተወሰደ የክፍል ሁለት የምስክርነት ቃል
ሙሉውን ሃሳብ ለማግኘት ከዚህ በታች ሊንኩን ስለማስቀምጠው ገብታችሁ መስማት ትችላላችሁ https://youtu.be/2Or8Ruv5x9U
ውድ ወገኖቼ ሆይ የጌታ ሰላም ይብዛላች በማለት መልዕክቴን እቀጥላለሁ :: ይሄ የድሮ ዘማሪ ይህንን ሃሳብ ያነሳው ፎከስድ የሆነ አገልግሎት የሚያስገኘውን ውጤታማነት ለመግለጽ ነው :: ከዚህም የተነሳ ይሄ የተወደደ ዘማሪ ከአምስት ዓመት በፊት ፎከስድ ወይንም ዳይሬክትድ ሆኖ ለማገልገል ምኞቱን ለጌታ በጸሎት እንዺህ ሲል ገለጸ :: «ጌታ ሆይ በጌታ ውጪ እንዳለ እንደሰበቀ ጦር ፎከስድ ሆኜ እንዳገለግልህ እርዳኝ » :: ወገኖቼ ምን ዓይነት ድንቅ ጸሎት ነው :: ይሄ ሃሳብ ነው እንግዲህ እኔንም ውስጤን ቀስቅሶ ከወንድሜ ኢንጂነር ዘማሪ ግዛቸው ጋር የተያያዘውን መልዕክቴን እንዲህ ስል ለእናንተ ለማቅረብ የወደድኩት ::
የልብ ንጽሕናንና ለውጥን የሚፈልጉ ሰዎች በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ቃል ወደሚያገለግል ወደ አንድ አገልጋይ ሄደው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት ይባላል :: የልብ ንጽሕናና ለውጥን ማግኘት እንፈልጋለን ስለዚህ ለዚህ ጉዳያችን ምን ማድረግ እንዳለብን ብትመክረን አሉት :: አገልጋዩም ሲመልስ የወሃ ጠባይ ለስላሳ ነው ፣ የድንጋይ ጠባይ ጠጣር ነው ነገር ግን ውሃ በጠርሙስ ተደርጎ ከድንጋዩ በላይ ከተያዘና ውሃ የሚያንጠባጥብ ከሆነ ቀስ በቀስ ድንጋዩ መሰባበሩ አይቀርም ፣ ቃለ እግዚአብሔርም ለስላሳ ነው ፣ ልቡናችን ደግሞ ጠጣር ነው ነገር ግን ሰው የእግዚአብሔርን ቃል አዘውትሮ የሚሰማ ከሆነ ልቡናው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለፈሪሃ እግዚአብሔር ማለትም እግዚአብሔርን ለመፍራት ቦታ መስጠቱ አይቀሬ ነው አላቸው ይባላል :: ከዚህ ጋር ተያይዞ ፦————————————————
የዘማሪ መጋቢ ዳንኤል አምደ ሚካኤልን የመዝሙር ሊንክ አስቀምጫለሁ በመስማት ተባረኩ https://youtu.be/alU0JgcK2hc
https://youtu.be/b1yufNRFMs0
አባ ዮናስ ጌታነህ