የሰላማችን ምልክት
ትዕምርተ ሰላምነ
የሰላምህ ምልክት መስቀልና የመስቀል ደመራ ፣ ከመስቀል ደመራም መልስ ሰላምን አገኛለሁ ስትል የምትቀባው አመድ አይደለም :: እሬቻም ስትል የምታከብረው በዓል ፣ ከዛፉም ስር ወስደህ ግንባርህ ላይ የምትቀባውና የምትለቀለቀው ቅቤ አይደለም :: የሰላምህ ምልክት በእርሱ የምትታመንበትና የምትደገፍበት የመዳኛህ ግንብ የሆነው የሕይወት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ክርስቶስ ነው ::
የመጀመርያይቱ ያልተከለሰችዋና የልተበረዘችዋ ፣ ንጹሑን ወንጌል የሰበከችዋ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን
ትዕምርተ ሰላምነ ዘኪያሁ ንትአመን ዓረፍተ መድኃኒትነ በዘቦቱ ናሰምክ ዕብነ ሕይወት ርዕሰ ማዕዘንት ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስትል አስተምራናለች ::
ትርጉም ፦ በእርሱ የምንታመንበት የሰላማችን ምልክት ፣ በእርሱ የምንደገፍበት የመዳናችን ግንብ የሕይወት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው { መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) ገጽ 121 }
ኤፌሶን 1 : 11 - 22 ፣ ቆላስያስ 1 : 19 - 20 ፣ 1ኛ ጴጥሮስ 3 : 18 - 22
የሰላማችን ምልክት ኢየሱስና ኢየሱስ ብቻ ነው
አባ ዮናስ ጌታነህ