Sunday, 3 March 2019

በሚገርም መረዳትና በሚገርም መገለጥ ስለ መሪነት በአገልጋይ ፒተር ማርዲግ የተነገረ በማስተዋል ሆናችሁ መልዕክቱን ተከታተሉ ጌታ ይባርካችሁ ከተናገራቸውም ዋና ዋና የሆኑትን ነጥቦች በጽሑፌ ላይ ለማስፈር ሞክሬያለሁ :: መሪነት ቀዳሚነት እንጂ የበላይነት አይደለም ይለናል:: ሊደርሺፕ እንደ ሥርወ መንግሥት ለልጅ ልጆቻችን የምናስተላልፈው አይደለም በማለት ይጀምርና አገልጋይ ፒተር የጊዝ ሊደር ሺፕን ያነሳል :: በመቀጠልም እኛ ልጆች ሆነን ይለናል ፒተር በላይ ሲበሩ የምናያቸው ዳክዬዎች ሲበሩ ሁልጊዜ ቪ ሆነው ነው የሚበሩት በማለት በቀዳሚነት ዓየሩን እየሰነጠቀች የምትሄደዋ ዳክዬ ሲደክማት ፈቃደኛ ሆና ያለትግል እንዴት ሌላውን እንደምትተካና በሌላውም እንደምትተካ ያጫውተናል :: እከስት አፉየ በምሳሌ እንዲል የግዕዙ ቃል ወደ አማርኛው ስተረጉመው አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነውና የሚገርም ምሳሌ የሚደንቅም የማስተዋል ንግግር ነው የተናገረው እግዚአብሔር አምላክ ዘመኑን ይባርከው :: አያይዞም ስለዚህ ሊደርሺፕ የእኔነትና በእኔነት ብቻ የተቃኘ ጉዞ ሳይሆን ብዙ መሠሎችን በማፍራት ለአንድ ዓላማ ፍጻሜያችን ላይ ለመድረስ የምናደርገው መተጋገዝ ነው ይለናል ይኸው ወዳጃችንና አገልጋያችን የሆነው ፒተር :: በመቀጠልም ሟች እንደሆንን ብናስብ ምንም ቢሆን እኛ ብቻችንን መሆን አንችልም:: አንድ ወጥነት ያለውና አራት ሳይዝ ያለው ወረቀት አምስት ቦታ ብንበጣጥሰው የአንድ ወረቀት ውጤት ነው አምስቱ ታድያ ኢየሱስም ወደ ላይ ባረገ ጊዜ አንድ ሙሉ የሆነ ብቃቱን በአንድ ሰው ውስጥ አልከተተም አምስት ቦታ ነው የተበተነው :: ኢየሱስ ሐዋርያ አስተማሪ ነቢይ ወንጌል ሰባኪና እረኛ ነው የሆነው :: ስለዚህ ለአንዱ አንዱን ለአንዱ አንዱን ሰጠ :: ታድያ እነዚህ አምስት አገልግሎቶች በባሕርይ በአመለካከትና እኔነት በሌለበት መንፈስ ውስጥ ሆነን ብንታረቅ ኢየሱስ ቸርች ውስጥ ተገለጠ ማለት ነው :: ቲም ሊደር ሺፕን የሚያህል የተባረከ ሲስተም የለም ይለናል አሁንም የተባረከው የእግዚአብሔር ሰው ፒተር ማርዲግ :: ኢየሱስ መሐላቸው እያገለገለ አይታወቅም ካልተሳመ ምንድነው ለእኔ ይሄ የሚያሳየኝ ኢየሱስ የተለየ ወንበር የለውም ሶፋ የለውም የተለየ ቦታ የለውም የተለየ ልብስ የለውም ጉዋደኛ ነው ወንድም ነው ወዳጅ ነው :: ታድያ ምንአለበት ይህ የሊደር ሺፕ አሠራር ቸርች ውስጥ ቢመለስ ? ምንለበት ጓደኛማቾች ብንሆን ? ምንአለበት ከሕዝቡ ሁሉ ጋራ አገልጋዩ ሁሉ አብሮ መኖር ቢጀምር :: ተለያይተን አንቀጥልም ተዋደን ነው አብረን መቀጠል ያለብን :: ኢየሱስ ወድቀውበት እንኩዋ እንዲፈወሱ አድርጎአል :: ኢየሱስ የሩቅ መሪ አይደለም :: ሊደር ሺፕ ተጽእኖ ፈጣሪነት እንጂ ፖዚሺን አይደለም :: እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ሊደርሺፕ ሰርቫንት ሊደርሺፕ አገልጋይ መሪነት ወደምድራችን ቢመጣ ደስ ይለኛል :: ከደከመን የሚበልጡንን ሰዎች ካፈራን ምንአለ ቢተኩን ? ቢያስቀጥሉን ? በመበለጥ ደስ የሚለው አባት ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት አለበት እኛም እንዲበልጡን መሥራት አለብን ሪቫይቫል የሀገር ወሬ የትውልድ ወሬ በመሆኑ ንስሐና መቀራረብን የሚጠይቅ ነው :: ይህንን ደግሞ የሚያመጣው እግዚአብሔር ነው :: ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 6 ን በመጥቀስ ቤተ መንግሥት የሆነው ነገር ሲቀየር ቤተክህነት ውስጥም የሚሆነው ይቀየራል :: የኦዝያን ነገር ሲቀየር የነቢዩም ነገር እንዴት እንደተቀየረና ነቢዩም ለእግዚአብሔር ተልእኮ በእሳቱ ተነክቶ እንደተዘጋጀ ይነግረናል ::አያይዞም ስለዚህ በሚመጡት ዘመናት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወደ ተልዕኮዋ ትመለሳለች :: ኦሪጂናል የሆነ ሪቫይቫል ፕራዮሪቲዋ ወንጌል የሆነ ማንን እልካለሁ ? የሚለውን ሰምታ እኔ እሄዳለሁ የምትል አንደበትዋ የተፈወሰ እሳትን የተላበሰች ክብርን አይታ በሪቫይቫል አቅም የምትገለጥ ቸርች ትወጣለች :: ከአሁን በኋላ ለኢትዮጵያ ያለኝ መልዕክት ይሄ ነው ቢቻል ይህንን እያሰብን ብንጸልይ ይለናል ወንድማችን ፒተር :: እኔም አሜን ወ አሜን ለይኩን ለይኩን ብያለሁ :: ሪቫይቫል እንዲመጣም የሰጠውን የመፍትሔ ሃሳብ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል :: ጨው በጨው ገበያ ከጨው ጋር ተቀምጦ ስኳር በስኳር ገበያ ከስኳዋር ጋር ተቀምጦ ማንንም እንደማያጣፍጥ እርሾም በእርሾ ገበያ ከእርሾ ጋር ተቀምጦ ማንንም እንደማያቦካ የመንግሥት ልጆችም እንደዚሁ በቸርች አዳራሽ ውስጥ የሚያመጡት ለውጥ የለም ከመዘመር ከማጨብጨብና ዕልል ከማለት ውጪ በማለት ቸርች በኅብረተሰብ ውስጥ በመግባትና ራስዋንም በማሰማራት ለውጥ አምጪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ልትሆን ይገባታል ሲል እንደ አንድ ታማኝ ባለ አደራና የእግዚአብሔር አገልጋይ መክሮናል ልባዊ መልዕክቱን አስተላልፎልናል :: ጌታ ዘመኑን ይባርከው የቃሉ አገልጋይ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment