Tuesday, 19 March 2019
ለመምህር ዘበነና ለመምህር ታሪኩ የተንጋደደ ሃሳብ በመጋቢ ዳዊት በኩል የተሰጠ መጽሐፍቅዱሳዊ መልስ ( ክፍል አንድ )ድርሳነ ዑራኤል ዘየካቲት ገጽ 136 አምስተኛ ተአምር ልመናውና አማላጅነቱ ለዘላለሙ በእውነት ከወዳጁ ………..ጋር ይሁንና የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው :: ከምዕራብ ወይም ከዓረብ አገር የመጣች አንዲት ሴት ነበረች :: ይህ የወራት ግዳጅዋ በየጊዜው እያስጨነቃትና እንደ ጎርፍ እየወረደ ሰውነቷን ያደክማት ነበር :: ቤተክርስቲያን ዘንድ ሄዳ በብዙ ማልቀስ ልትጸልይ ከአጸደ ቤተክርስቲያን ውጪ ቆመች :: ከዚያም ከቤተክርስቲያኑ በስተውጪ ስትጸልይና ስታለቅስ ጊዜ ቆየች :: ይህቺ ሴት ከቤተክርስቲያን ውጪ በሆነ በዐጸዱ ውስጥ ቆማ ብዙ ጊዜ መዘግየቷን ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ባዩ ጊዜ አንቺ ሴትዮ ሥራሽ ምንድነው ? ምንስ ትፈልጊያለሽ ? ሲሉ ጠየቋት :: እርስዋም ልጅ እንደሌላትና ለብዙ ዘመን መካን ሆና ስታዝንና ስትተክዝ የኖረች መሆንዋን ነገረቻቸው :: ያን ጊዜ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ስዕለት ተሳይ እርሱም መልካም ልጅ ይሰጥሻል አሏት :: እርስዋም እሺ እንደ ቃላችሁ አደርጋለሁ አለቻቸው እስከ ዛሬ ዓመት ድረስ ማኅፀኔን ልጅ ለመውለድ የከፈተልኝ እንደሆነ እስከ ዕለተ ሞቴ አገለግለዋለሁ በማለት ተማፅና ወደ ሀገርዋ ተመለሰች :: በመንገድም ስትሔድ የምታውቃት አንዲት ሴት አገኘችና ሰላም አለቻት :: ከጥንት ጀምሮ ስለምታውቃትም ሁለቱም አፍ ለአፍ ገጥመው ተሳሳሙ :: ያን ጊዜ በመንገድ ያገኘቻት ሴትዮ የጸነሰች ስለነበረች በሚሳሳሙበት ጊዜ የጸነሰችው ሴት ምራቅ ባልጸነሰችው ሴት አፍ ገባና ከወንድ ጋር ሳትገናኝ በዚሁ ብቻ ጸነሰች :: በዚህ ጊዜ የወር ግዳጅዋ ቆመና ቅሪት ሆና ወይም ጸንሳ በፍጹም ደስታ ወደ ቤቷ ገባች :: ከሦስት ወር በኋላ ጐረቤቶችዋ ከምክነትሽ እንዴት ዳንሽ ? እንዴት ስለሰማሽ ነው የተወደደ ልጅ የሰጠሽ ? አሏት :: ከሰባት ወር በኋላም ልጅ ወለደችና በክንዷ ታቅፋ እግዚአብሔርን አመሰገነች :: ስለ እምነትዋ የተወደደ ልጅን አገኘች እያለ …………..ይናገራል :: የተወደዳችሁ ወገኖች ይህን ጽሑፍ ከድርሣነ ዑራኤል አውጥቼ በማስረጃነት እንድታነቡት ለእናንተ ያቀረብኩበት ምክንያት ከመጋቢ ዳዊት ጋር በነበረን የትምህርት ቆይታ ግብረ ሰዶማዊነትን ማለትም ጌይና ሌዝቢያንን አንስተን ስለነበረ የራስዋ ሽንኩርት አሮባት የሰው ድስት ታማስላለች እንዲሉ የኛዎቹ መምህራን ነን ባዮች ዶክተር ዘበነ ለማና መምህር ታሪኩ በዓይናቸው ያለውን ምሰሶ ሳያወጡ ሰው ቤት ሄደው ከሰዉ ዓይን ጉድፍ ላውጣልህ ፍቀድልኝ ሲሉ መጮሃቸው ደንቆኝ ነው :: ስለዚህ ሰው የሆነ ሰው ስለ ሌሎች ከማውራቱ በፊት እኔስ ጋር ምንድነው ያለው ? ሲል ቅድሚያውን ወስዶ ራሱን ነው ማየት ያለበት :: የድርሳነ ዑራኤል ተአምር እኮ ከሳውዘርን ባብቲስት ቤተክርስቲያን ባልተናነሰ ሁኔታ ግብረ ሰዶማዊነትን ወይንም ጌይንና ሌዝቢያንን እንድናቀነቅን እንዲህ ሲል መክሮናል :: ከሴት ጋር ተሳስማ የጸነሰችዋን ሴት ትክክለኛ መጽነስን ነው የጸነሰችው ሊለን ከእምነት ጋር አያይዞ ከሰባት ወር በኋላም ልጅ ወለደችና በክንዷ ታቅፋ እግዚአብሔርን አመሰገነች ስለ እምነትዋ የተወደደ ልጅን አገኘች በማለት ነገረን :: ታድያ እንዲህ ማለቱ ምን ለማለት ፈልጎ ይመስላችኋል ? እናንተም ነገ ጠዋት በጾታዊ ገደብ ሳትያዙ ሴት ለሴት ወይንም ወንድ ለወንድ ጋብቻን ብትፈቅዱና አጋብታችሁም ሆነ ተጋብታችሁ ብትሳሳሙ ለዚህች ሴት የሆነው መጽነስና ልጅንም መውለድ ለእናንተም ይሆናል እያለን እኮ ነው :: መልአኩ ዑራኤልም የዚህ ነገር ተባባሪና ስዕለትንም ፈጻሚ እንደሆነ አያይዞ ይናገራል :: ድርሣኑ የዋዛ ድርሳን አይደለምና አያይዞም እንዲህ ይላል :: የዚህችን ልጅ የወለደችዋን ሴት ስዕለት ቀሳውስቱ ሳይቀር በደስታ መቀበላቸውን ይዘረዝራል :: ስለዚህ እኛ እዛ ጋር በርቀት ያሉትን ሳውዘርን ባብቲስት ቸርችንና የመሳሰሉትን እንወቅሳለን እንጂ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችንን ድርሳነ ዑራኤል የኔን ድርሳን ተቀብላ በማመኗ የለየላት ሌዝቢያኒስት የባሰሰባትም ሳውዘርን ባብቲስት ናት እያለን ነው :: በመሆኑም በእጅ አዙር በመጣ የድርሳነ ዑራኤል መልዕክት እኛው ራሳችን ሳውዘርን ባብቲስትና የመሳሰሉትን ሆነን ከተገኘን ስለሌሎች ቤተክርስቲያኖች ወይንም ስለ ሳውዘርን ባብቲስት ቸርች ሰዶማዊነት ማውራቱ በእኔ በኩል በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ከሚሆንብን በቀር ጥቅሙ አይታየኝም :: ስለዚህ ሌላው ጋር ተሻግረን ጣት ከመቀሰራችን በፊት በቅድሚያ የኛኑ የራሳችንን ችግር እኛው እናውጣው ፣ እናስተካክለው :: በዚሁ የተረታተረት መጽሐፍም ለመልአኩ ዑራኤል የሌለ ስም አይሰጠው ፣ ስሙም አይጥፋ :: ድርሳነ ዑራኤልም የተሳሳተና ሰውንም እያሳሳተ ያለ ድርሳን ስለሆነ ይታረም ፣ እኛም እንታረም ፣ ራሳችንንም እናርም የሚል መልዕክት አለኝ :: ተባረኩ:: አባ ዮናስ ጌታነህ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment