Thursday, 28 March 2019
በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን መጽሐፍቅዱሳችን በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ፥ 41 — 43 ላይ በተጻፈ ሃሳቡ ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር እያለን የተአምረ ማርያሙ ጸሐፊ ግን ማርያምን በእውቀትዋ መተናነስ ሳይኖርባት ከእግዚአብሔር እኩል እንደሆነችና መፍትሔ ሰጭም መሆንዋን በመናገር የዋሸበትን ትልቁን ውሸት ፣ ሕዝባችንንም ያሳሳተበትን ጉዳይ ዛሬ ተመልክተናል ለማስታወስ ያክልም ከዚህ መልስ የዘረዘርኩዋቸውን ሃሳቦች ተመልከቱ በምዕ. 41፥13 “በእግዚአብሔር አምነው፥ በወለደችውም በእመቤታችን አምነው ከቤተ ክርስቲያን ወጡ” ይላል። ቁ. 25 እምነቱን በናቱና በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሁሉ አያፍርምና ይላል። 53፥55 ላይ እግዚአብሔርን አመሰገኑ እመቤታችንንም አመሰገንዋት ይላል። እምነት ክርስቶስ ሲደመር ሌላ ነገር ሆነ ማለት ነው! በምዕ. 56 ማርያም አንዱን መነኩሴ፥ “ከሚያልፈው ዓለም እስክወስድህ ድረስ ልጄ ካንተ አይለይም” አለችው። ወሳጇ እርሷ ስትሆን እስክትወስደው ከመነኩሴው የማይለየው ልጇ ነው ልክ እንደ አገልጋይ ማለት ነው በመጽሐፉ ማርያም ብቻ “ከልጇ ጎን በፈሰሰው ደሟ” አዳኝ ሆና ቀርባለች። ታዲያ ይህ የሰሚዎችን ጆሮ እያደነቆረ የጠፉቱ የምሥራቹን ቃል ለመስማት የተቸገሩበት ሁኔታ ነው ያለው በምዕ. 81 አንድ መነኩሴን በአንድ ሌሊት ተገልጣ ወደ ኢየሩሳሌም ወስዳ አዙራ አስጎብኝታ፥ በዮርዳኖስም አጥምቃ የሚሞትበትን ጊዜ ነገረችው፤ እንደተናገረችው ጊዜ ዐረፈ። ታድያ ይህቺ ማርያም ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቃቸው የሌሉ ነገሮችን ካወቀች ሁሉን አዋቂ ናት ሁሉን አዋቂ ከሆነች ደግሞ አምላክ ናት እያለን ነው ጉዳኛው ተአምረ ማርያም ሌላም ብዙ የብዙ ብዙ ነገሮችን ነቅሰን ከዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማውጣት እንችላለን ወገኖቼ ስለዚህ እንግዲህ ለእምነታችን በቂ የሆነውን መጽሐፍቅዱሳችንን እያነበብን ቃሉ የሚለንን ብቻ እንመን ለቃሉም እንታዘዝ ተባረኩ አባ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment