Thursday, 28 March 2019

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን መጽሐፍቅዱሳችን በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ፥ 41 — 43 ላይ በተጻፈ ሃሳቡ ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር እያለን የተአምረ ማርያሙ ጸሐፊ ግን ማርያምን በእውቀትዋ መተናነስ ሳይኖርባት ከእግዚአብሔር እኩል እንደሆነችና መፍትሔ ሰጭም መሆንዋን በመናገር የዋሸበትን ትልቁን ውሸት ፣ ሕዝባችንንም ያሳሳተበትን ጉዳይ ዛሬ ተመልክተናል ለማስታወስ ያክልም ከዚህ መልስ የዘረዘርኩዋቸውን ሃሳቦች ተመልከቱ በምዕ.  41፥13  “በእግዚአብሔር  አምነው፥  በወለደችውም  በእመቤታችን አምነው  ከቤተ  ክርስቲያን  ወጡ”  ይላል።  ቁ.  25  እምነቱን  በናቱና  በእግዚአብሔር  ላይ  ያደረገ  ሁሉ  አያፍርምና  ይላል።  53፥55  ላይ  እግዚአብሔርን  አመሰገኑ  እመቤታችንንም  አመሰገንዋት  ይላል።  እምነት ክርስቶስ  ሲደመር  ሌላ  ነገር  ሆነ  ማለት ነው! በምዕ. 56  ማርያም  አንዱን መነኩሴ፥ “ከሚያልፈው ዓለም እስክወስድህ  ድረስ  ልጄ  ካንተ  አይለይም”  አለችው። ወሳጇ  እርሷ ስትሆን እስክትወስደው  ከመነኩሴው  የማይለየው  ልጇ  ነው  ልክ  እንደ  አገልጋይ  ማለት  ነው በመጽሐፉ  ማርያም  ብቻ “ከልጇ  ጎን  በፈሰሰው  ደሟ”  አዳኝ  ሆና  ቀርባለች።  ታዲያ  ይህ የሰሚዎችን  ጆሮ  እያደነቆረ  የጠፉቱ  የምሥራቹን  ቃል ለመስማት የተቸገሩበት ሁኔታ ነው ያለው በምዕ.  81  አንድ  መነኩሴን  በአንድ  ሌሊት  ተገልጣ  ወደ  ኢየሩሳሌም  ወስዳ  አዙራ አስጎብኝታ፥  በዮርዳኖስም  አጥምቃ  የሚሞትበትን  ጊዜ  ነገረችው፤ እንደተናገረችው  ጊዜ  ዐረፈ። ታድያ ይህቺ ማርያም ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቃቸው የሌሉ ነገሮችን  ካወቀች  ሁሉን  አዋቂ  ናት  ሁሉን  አዋቂ  ከሆነች ደግሞ አምላክ ናት እያለን ነው ጉዳኛው ተአምረ ማርያም ሌላም ብዙ የብዙ ብዙ ነገሮችን ነቅሰን ከዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማውጣት እንችላለን ወገኖቼ ስለዚህ እንግዲህ ለእምነታችን በቂ የሆነውን መጽሐፍቅዱሳችንን እያነበብን ቃሉ የሚለንን ብቻ እንመን ለቃሉም እንታዘዝ ተባረኩ አባ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday, 20 March 2019

የመልዕክት ርዕስ ፦ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ ታላቅ ጸጥታም ሆነ የማቴዎስ ወንጌል 8 ፥ 23 - 27የመልዕክት ርዕስ ፦ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ ታላቅ ጸጥታም ሆነ የማቴዎስ ወንጌል 8 ፥ 23 - 27 የመነሣትና የእምነትንም ሥራ የመሥራት ጊዜ ለዘመኗ ለቤተክርስቲያን ይሁን አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት ( የማርቆስ ወንጌል  4 : 38 ) ወአንከሩ ሰብእ ወይቤሉ መኑ እንጋ ውእቱ ዝንቱ ዘይትኤዘዙ ሎቱ ባሕርኒ ወነፋሳትኒ ሰዎቹም ነፋሳትና ባሕር ስንኳ የሚታዘዙለት ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው ?እያሉ ተደነቁ ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን በኋላቸው ገሥግስው ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ ( ኦሪት ዘጸአት  14 :10 ) ሙሴንም፦ በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸንን? ከግብፅ ታወጣን ዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? በምድረ በዳ ከምንሞት ብንገዛላቸው ይሻላልና፦ ተወን፥ ለግብፃውያን እንገዛ ብለን በግብፅ ሳለን ያልንህ ቃል ይህ አይደለምን? አሉት ( ኦሪት ዘጸአት  14 : 11 - 12 ) እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና ( የሐዋርያት ሥራ  10 : 38 ) እነዚህ ጥቅሶች የመልዕክቱን ዋናና አንኳር ሃሳቦችን የሚገልጡ ናቸው ተባረኩ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ አባ ዮናስ ጌታነህ

Tuesday, 19 March 2019

ለመምህር ዘበነና ለመምህር ታሪኩ የተንጋደደ ሃሳብ በመጋቢ ዳዊት በኩል የተሰጠ መጽሐፍቅዱሳዊ መልስ ( ክፍል አንድ )ድርሳነ ዑራኤል ዘየካቲት ገጽ 136 አምስተኛ ተአምር ልመናውና አማላጅነቱ ለዘላለሙ በእውነት ከወዳጁ ………..ጋር ይሁንና የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው :: ከምዕራብ ወይም ከዓረብ አገር የመጣች አንዲት ሴት ነበረች :: ይህ የወራት ግዳጅዋ በየጊዜው እያስጨነቃትና እንደ ጎርፍ እየወረደ ሰውነቷን ያደክማት ነበር :: ቤተክርስቲያን ዘንድ ሄዳ በብዙ ማልቀስ ልትጸልይ ከአጸደ ቤተክርስቲያን ውጪ ቆመች :: ከዚያም ከቤተክርስቲያኑ በስተውጪ ስትጸልይና ስታለቅስ ጊዜ ቆየች :: ይህቺ ሴት ከቤተክርስቲያን ውጪ በሆነ በዐጸዱ ውስጥ ቆማ ብዙ ጊዜ መዘግየቷን ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ባዩ ጊዜ አንቺ ሴትዮ ሥራሽ ምንድነው ? ምንስ ትፈልጊያለሽ ? ሲሉ ጠየቋት :: እርስዋም ልጅ እንደሌላትና ለብዙ ዘመን መካን ሆና ስታዝንና ስትተክዝ የኖረች መሆንዋን ነገረቻቸው :: ያን ጊዜ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ስዕለት ተሳይ እርሱም መልካም ልጅ ይሰጥሻል አሏት :: እርስዋም እሺ እንደ ቃላችሁ አደርጋለሁ አለቻቸው እስከ ዛሬ ዓመት ድረስ ማኅፀኔን ልጅ ለመውለድ የከፈተልኝ እንደሆነ እስከ ዕለተ ሞቴ አገለግለዋለሁ በማለት ተማፅና ወደ ሀገርዋ ተመለሰች :: በመንገድም ስትሔድ የምታውቃት አንዲት ሴት አገኘችና ሰላም አለቻት :: ከጥንት ጀምሮ ስለምታውቃትም ሁለቱም አፍ ለአፍ ገጥመው ተሳሳሙ :: ያን ጊዜ በመንገድ ያገኘቻት ሴትዮ የጸነሰች ስለነበረች በሚሳሳሙበት ጊዜ የጸነሰችው ሴት ምራቅ ባልጸነሰችው ሴት አፍ ገባና ከወንድ ጋር ሳትገናኝ በዚሁ ብቻ ጸነሰች :: በዚህ ጊዜ የወር ግዳጅዋ ቆመና ቅሪት ሆና ወይም ጸንሳ በፍጹም ደስታ ወደ ቤቷ ገባች :: ከሦስት ወር በኋላ ጐረቤቶችዋ ከምክነትሽ እንዴት ዳንሽ ? እንዴት ስለሰማሽ ነው የተወደደ ልጅ የሰጠሽ ? አሏት :: ከሰባት ወር በኋላም ልጅ ወለደችና በክንዷ ታቅፋ እግዚአብሔርን አመሰገነች :: ስለ እምነትዋ የተወደደ ልጅን አገኘች እያለ …………..ይናገራል :: የተወደዳችሁ ወገኖች ይህን ጽሑፍ ከድርሣነ ዑራኤል አውጥቼ በማስረጃነት እንድታነቡት ለእናንተ ያቀረብኩበት ምክንያት ከመጋቢ ዳዊት ጋር በነበረን የትምህርት ቆይታ ግብረ ሰዶማዊነትን ማለትም ጌይና ሌዝቢያንን አንስተን ስለነበረ የራስዋ ሽንኩርት አሮባት የሰው ድስት ታማስላለች እንዲሉ የኛዎቹ መምህራን ነን ባዮች ዶክተር ዘበነ ለማና መምህር ታሪኩ በዓይናቸው ያለውን ምሰሶ ሳያወጡ ሰው ቤት ሄደው ከሰዉ ዓይን ጉድፍ ላውጣልህ ፍቀድልኝ ሲሉ መጮሃቸው ደንቆኝ ነው :: ስለዚህ ሰው የሆነ ሰው ስለ ሌሎች ከማውራቱ በፊት እኔስ ጋር ምንድነው ያለው ? ሲል ቅድሚያውን ወስዶ ራሱን ነው ማየት ያለበት :: የድርሳነ ዑራኤል ተአምር እኮ ከሳውዘርን ባብቲስት ቤተክርስቲያን ባልተናነሰ ሁኔታ ግብረ ሰዶማዊነትን ወይንም ጌይንና ሌዝቢያንን እንድናቀነቅን እንዲህ ሲል መክሮናል :: ከሴት ጋር ተሳስማ የጸነሰችዋን ሴት ትክክለኛ መጽነስን ነው የጸነሰችው ሊለን ከእምነት ጋር አያይዞ ከሰባት ወር በኋላም ልጅ ወለደችና በክንዷ ታቅፋ እግዚአብሔርን አመሰገነች ስለ እምነትዋ የተወደደ ልጅን አገኘች በማለት ነገረን :: ታድያ እንዲህ ማለቱ ምን ለማለት ፈልጎ ይመስላችኋል ? እናንተም ነገ ጠዋት በጾታዊ ገደብ ሳትያዙ ሴት ለሴት ወይንም ወንድ ለወንድ ጋብቻን ብትፈቅዱና አጋብታችሁም ሆነ ተጋብታችሁ ብትሳሳሙ ለዚህች ሴት የሆነው መጽነስና ልጅንም መውለድ ለእናንተም ይሆናል እያለን እኮ ነው :: መልአኩ ዑራኤልም የዚህ ነገር ተባባሪና ስዕለትንም ፈጻሚ እንደሆነ አያይዞ ይናገራል :: ድርሣኑ የዋዛ ድርሳን አይደለምና አያይዞም እንዲህ ይላል :: የዚህችን ልጅ የወለደችዋን ሴት ስዕለት ቀሳውስቱ ሳይቀር በደስታ መቀበላቸውን ይዘረዝራል :: ስለዚህ እኛ እዛ ጋር በርቀት ያሉትን ሳውዘርን ባብቲስት ቸርችንና የመሳሰሉትን እንወቅሳለን እንጂ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችንን ድርሳነ ዑራኤል የኔን ድርሳን ተቀብላ በማመኗ የለየላት ሌዝቢያኒስት የባሰሰባትም ሳውዘርን ባብቲስት ናት እያለን ነው :: በመሆኑም በእጅ አዙር በመጣ የድርሳነ ዑራኤል መልዕክት እኛው ራሳችን ሳውዘርን ባብቲስትና የመሳሰሉትን ሆነን ከተገኘን ስለሌሎች ቤተክርስቲያኖች ወይንም ስለ ሳውዘርን ባብቲስት ቸርች ሰዶማዊነት ማውራቱ በእኔ በኩል በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ከሚሆንብን በቀር ጥቅሙ አይታየኝም :: ስለዚህ ሌላው ጋር ተሻግረን ጣት ከመቀሰራችን በፊት በቅድሚያ የኛኑ የራሳችንን ችግር እኛው እናውጣው ፣ እናስተካክለው :: በዚሁ የተረታተረት መጽሐፍም ለመልአኩ ዑራኤል የሌለ ስም አይሰጠው ፣ ስሙም አይጥፋ :: ድርሳነ ዑራኤልም የተሳሳተና ሰውንም እያሳሳተ ያለ ድርሳን ስለሆነ ይታረም ፣ እኛም እንታረም ፣ ራሳችንንም እናርም የሚል መልዕክት አለኝ :: ተባረኩ:: አባ ዮናስ ጌታነህ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ

Thursday, 14 March 2019

የሙሴን እጆች አለመደገፍ አማሌቅነት ነው ኦሪት ዘጸአት 17 Aba Yonas Getaneh Asfaw

የሙሴን እጆች አለመደገፍ አማሌቅነት ነው ኦሪት ዘጸአት 17 Aba Yonas Getaneh Asfawየሙሴን እጆች አለመደገፍ አማሌቅነት ነው ( ኦሪት ዘጸአት 17 ፥ 8 -17 ) ዛሬ የሚኖረን የጸሎት ጊዜ ነው ቤተሰባቸውን በአውሮፕላን አደጋ ላጡና ለተጎዱ ሰዎች እንጸልያለን በዚያው መጠን ለሀገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግሮችና ቀውሶች እንድትወጣ እንጸልያለን ጥቂት የእግዚአብሔርንም ቃል እንከፋፈላለን ተባረኩ

ዳንኤል በአምላኩ ፊት ሲጸልይና ሲለምን አገኙት ( ክፍል ሁለት ) ዳንኤል በአምላኩ ፊት ሲጸልይና ሲለምን አገኙት ( ክፍል ሁለት ) እነዚያም ሰዎች ተሰብስበው ዳንኤል በአምላኩ ፊት ሲጸልይና ሲለምን አገኙት ትንቢተ ዳንኤል 6 ፥ 11 ዳንኤል ሲጸልይ ሲለምን ተገኘ እኛንስ ሰዎች ምን ስናደርግ ያገኙን ይሆን ? በተለይ ጌታ ምን ስናደርግ ያገኘን ይሆን ? መልሱን ለእናንተ

Saturday, 9 March 2019

ዶክተር ዘበነ ለማ ሰማንያ አንዱን መጽሐፍቅዱስ ከስልሳ ስድስቱ እንዳይለይ አድርጎ ያወሳሰበውን በእግዚአብሔር ቃ...

ዶክተር ዘበነ ለማ ሰማንያ አንዱን መጽሐፍቅዱስ ከስልሳ ስድስቱ እንዳይለይ አድርጎ ያወሳሰበውን በእግዚአብሔር ቃ...

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት ከእግዚአብሔር እንዲሆን የተካሄደ ጸሎት ነው የሀገር ጉዳይ ነውና የሚመለከታ...

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት ከእግዚአብሔር እንዲሆን የተካሄደ ጸሎት ነው የሀገር ጉዳይ ነውና የሚመለከታ...

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት ከእግዚአብሔር እንዲሆን የተካሄደ ጸሎት ነው የሀገር ጉዳይ ነውና የሚመለከታ...

Sunday, 3 March 2019

በሚገርም መረዳትና በሚገርም መገለጥ ስለ መሪነት በአገልጋይ ፒተር ማርዲግ የተነገረ በማስተዋል ሆናችሁ መልዕክቱን ተከታተሉ ጌታ ይባርካችሁ ከተናገራቸውም ዋና ዋና የሆኑትን ነጥቦች በጽሑፌ ላይ ለማስፈር ሞክሬያለሁ :: መሪነት ቀዳሚነት እንጂ የበላይነት አይደለም ይለናል:: ሊደርሺፕ እንደ ሥርወ መንግሥት ለልጅ ልጆቻችን የምናስተላልፈው አይደለም በማለት ይጀምርና አገልጋይ ፒተር የጊዝ ሊደር ሺፕን ያነሳል :: በመቀጠልም እኛ ልጆች ሆነን ይለናል ፒተር በላይ ሲበሩ የምናያቸው ዳክዬዎች ሲበሩ ሁልጊዜ ቪ ሆነው ነው የሚበሩት በማለት በቀዳሚነት ዓየሩን እየሰነጠቀች የምትሄደዋ ዳክዬ ሲደክማት ፈቃደኛ ሆና ያለትግል እንዴት ሌላውን እንደምትተካና በሌላውም እንደምትተካ ያጫውተናል :: እከስት አፉየ በምሳሌ እንዲል የግዕዙ ቃል ወደ አማርኛው ስተረጉመው አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነውና የሚገርም ምሳሌ የሚደንቅም የማስተዋል ንግግር ነው የተናገረው እግዚአብሔር አምላክ ዘመኑን ይባርከው :: አያይዞም ስለዚህ ሊደርሺፕ የእኔነትና በእኔነት ብቻ የተቃኘ ጉዞ ሳይሆን ብዙ መሠሎችን በማፍራት ለአንድ ዓላማ ፍጻሜያችን ላይ ለመድረስ የምናደርገው መተጋገዝ ነው ይለናል ይኸው ወዳጃችንና አገልጋያችን የሆነው ፒተር :: በመቀጠልም ሟች እንደሆንን ብናስብ ምንም ቢሆን እኛ ብቻችንን መሆን አንችልም:: አንድ ወጥነት ያለውና አራት ሳይዝ ያለው ወረቀት አምስት ቦታ ብንበጣጥሰው የአንድ ወረቀት ውጤት ነው አምስቱ ታድያ ኢየሱስም ወደ ላይ ባረገ ጊዜ አንድ ሙሉ የሆነ ብቃቱን በአንድ ሰው ውስጥ አልከተተም አምስት ቦታ ነው የተበተነው :: ኢየሱስ ሐዋርያ አስተማሪ ነቢይ ወንጌል ሰባኪና እረኛ ነው የሆነው :: ስለዚህ ለአንዱ አንዱን ለአንዱ አንዱን ሰጠ :: ታድያ እነዚህ አምስት አገልግሎቶች በባሕርይ በአመለካከትና እኔነት በሌለበት መንፈስ ውስጥ ሆነን ብንታረቅ ኢየሱስ ቸርች ውስጥ ተገለጠ ማለት ነው :: ቲም ሊደር ሺፕን የሚያህል የተባረከ ሲስተም የለም ይለናል አሁንም የተባረከው የእግዚአብሔር ሰው ፒተር ማርዲግ :: ኢየሱስ መሐላቸው እያገለገለ አይታወቅም ካልተሳመ ምንድነው ለእኔ ይሄ የሚያሳየኝ ኢየሱስ የተለየ ወንበር የለውም ሶፋ የለውም የተለየ ቦታ የለውም የተለየ ልብስ የለውም ጉዋደኛ ነው ወንድም ነው ወዳጅ ነው :: ታድያ ምንአለበት ይህ የሊደር ሺፕ አሠራር ቸርች ውስጥ ቢመለስ ? ምንለበት ጓደኛማቾች ብንሆን ? ምንአለበት ከሕዝቡ ሁሉ ጋራ አገልጋዩ ሁሉ አብሮ መኖር ቢጀምር :: ተለያይተን አንቀጥልም ተዋደን ነው አብረን መቀጠል ያለብን :: ኢየሱስ ወድቀውበት እንኩዋ እንዲፈወሱ አድርጎአል :: ኢየሱስ የሩቅ መሪ አይደለም :: ሊደር ሺፕ ተጽእኖ ፈጣሪነት እንጂ ፖዚሺን አይደለም :: እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ሊደርሺፕ ሰርቫንት ሊደርሺፕ አገልጋይ መሪነት ወደምድራችን ቢመጣ ደስ ይለኛል :: ከደከመን የሚበልጡንን ሰዎች ካፈራን ምንአለ ቢተኩን ? ቢያስቀጥሉን ? በመበለጥ ደስ የሚለው አባት ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት አለበት እኛም እንዲበልጡን መሥራት አለብን ሪቫይቫል የሀገር ወሬ የትውልድ ወሬ በመሆኑ ንስሐና መቀራረብን የሚጠይቅ ነው :: ይህንን ደግሞ የሚያመጣው እግዚአብሔር ነው :: ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 6 ን በመጥቀስ ቤተ መንግሥት የሆነው ነገር ሲቀየር ቤተክህነት ውስጥም የሚሆነው ይቀየራል :: የኦዝያን ነገር ሲቀየር የነቢዩም ነገር እንዴት እንደተቀየረና ነቢዩም ለእግዚአብሔር ተልእኮ በእሳቱ ተነክቶ እንደተዘጋጀ ይነግረናል ::አያይዞም ስለዚህ በሚመጡት ዘመናት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወደ ተልዕኮዋ ትመለሳለች :: ኦሪጂናል የሆነ ሪቫይቫል ፕራዮሪቲዋ ወንጌል የሆነ ማንን እልካለሁ ? የሚለውን ሰምታ እኔ እሄዳለሁ የምትል አንደበትዋ የተፈወሰ እሳትን የተላበሰች ክብርን አይታ በሪቫይቫል አቅም የምትገለጥ ቸርች ትወጣለች :: ከአሁን በኋላ ለኢትዮጵያ ያለኝ መልዕክት ይሄ ነው ቢቻል ይህንን እያሰብን ብንጸልይ ይለናል ወንድማችን ፒተር :: እኔም አሜን ወ አሜን ለይኩን ለይኩን ብያለሁ :: ሪቫይቫል እንዲመጣም የሰጠውን የመፍትሔ ሃሳብ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል :: ጨው በጨው ገበያ ከጨው ጋር ተቀምጦ ስኳር በስኳር ገበያ ከስኳዋር ጋር ተቀምጦ ማንንም እንደማያጣፍጥ እርሾም በእርሾ ገበያ ከእርሾ ጋር ተቀምጦ ማንንም እንደማያቦካ የመንግሥት ልጆችም እንደዚሁ በቸርች አዳራሽ ውስጥ የሚያመጡት ለውጥ የለም ከመዘመር ከማጨብጨብና ዕልል ከማለት ውጪ በማለት ቸርች በኅብረተሰብ ውስጥ በመግባትና ራስዋንም በማሰማራት ለውጥ አምጪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ልትሆን ይገባታል ሲል እንደ አንድ ታማኝ ባለ አደራና የእግዚአብሔር አገልጋይ መክሮናል ልባዊ መልዕክቱን አስተላልፎልናል :: ጌታ ዘመኑን ይባርከው የቃሉ አገልጋይ አባ ዮናስ ጌታነህ

የመልዕክት ርዕስ ፦ ዮሴፍም ይህንን ሲሉት አለቀሰ ( ዘፍጥረት 50 : 15 - 21 ) part 2