Sunday, 3 February 2019
Aba WoldeTensae Ayalenahe የሃዲስ ኪዳን ታቦት አሁን አድን የታቦቱ ምስጢር በቆራጡ የወንጌሉ ሐዋርያና አርበኛ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ በዛሬው ስማቸው የሁላችን አባት በሆኑት በአቡነ በርናባስ ሲገለጥ እኚህ አባት በዚህ አስደናቂ መልዕክታቸው ስደትንና መገፋትን ከመጥላት የተነሣ እውነትን ይዞ ፣ ፈርቶና ተደብቆ ያለውን መምህር ልዑለ ቃል አካሉን ከተደበቀበት መቅደስ ውስጥ በስሙ በመጥራትና ወደ መድረኩም በማውጣት ፣ የእሁድ ውዳሴ ማርያም የሚለውን ቃል አንስተው በግዕዝ በማንበብ ፣ እርሱ ደግሞ አማርኛውን እንዲተረጉም አድርገውታል :: መምህር ልዑለ ቃልም በሕዝብ ፊት መጠራቱ ምንም እንኩዋ ያስደሰተው ባይመስልም የግድ እየተናነቀውም ቢሆን እውነቱን ይፋ አውጥቶና ዝርግፍ አድርጎ ተርጉሞታል :: ሃሳቡንም ፈራ ተባ እያለም ቢሆን እንዲህ ሲል ገልጾታል :: በወርቅ የተለበጠው ታቦት በአካላዊ ቃል ይመሰልልናል :: እኛን ለማዳን ሰው የሆነ በጎላ በተረዳ ሰው ከሆነ በኋላ እውነተኛ የባሕርይ አምላክ ነው :: ድንግል በድንግልና ጸንታ ሳለች እመቤታችን ወለደችው በማለት እውነቱን አፍረጥርጦ ተናገረ :: ታድያ ከዚህ እውነት አንጻር መምህር ልዑለ ቃል ከዚህ ከተገለጠለት የወንጌል እውነት ራሱን ማሸሹም ሆነ መደበቁ ምን የሚሉት ሞኝነት ነው እንላለን :: ይህ ብቻ አይደለም ራሱን ወንጌል ያልተገለጠለትና ያልበራለት በማስመሰል ፣ የወንጌሉንም እውነት ሽምጥጥ አድርጎ በማካድ ፣ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክተኞችና የወንጌሉ አገልጋዮች የሆነውን እኛን ደግሞ አሁን ላይ ተነስቶ በብዙ ማሳደዱ በእጅጉ አስገርሞኛል :: ይሄ ብቻ አይደለም መምህር ልዑለ ቃል ተአምረ ማርያምን የጣልያን ባንዳ የጻፈው ነው ሲል የተቸበት የቪዲዮ ማስረጃ በእጃችን አለ :: ስለ መምህር ልዑለቃል ከተፈለገ በእውነት ላይ እንዲቆም ከምንፈልግ ውጪ ልንወነጅለው አንፈልግም እንጂ በወንጌል እውነት ላይ የቆመበትን ሌላ ብዙ የብዙ ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ እንችላለን :: ለማንኛውም ግን ለዚህ እውነት ያነሳሱትንና ያበረታቱትን አቡነ በርናባስን ፣ እግዚአብሔር ይባርክዎት ፣ ዕድሜና ዘመንም ይጨመርልዎት ለማለት እወዳለሁ :: ከዚያ መልስ ብፁዕ አባታችን አቡነ በርናባስ ርቱዕ በሆነና በመንፈስቅዱስም በተቃኘው አንደበታቸው የጌትነቱንና የአዳኝነቱን ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኛ ማዕከላችን የብሉይ ኪዳኑ ታቦት ሳይሆን ኢየሱስ መሆኑን ፣ ወደ አብ መንግሥት የሚወስደን በራችንም ሆነ መንገዳችን አሁንም ይኸው ኢየሱስ መሆኑን ትርትር አድርገው በሚገባ አስተምረዋል :: ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን መስማቱ አማራጭ የለውምና ቪዲዮውን ሰምታችሁ ተባረኩበት :: ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment