Monday, 4 February 2019
የመልዕክት ርዕስ ፦ ያልተያዘና ያልተነካካ ነገር ይሰጥሃልና አንተም አትነካካ ( ክፍል አንድ ) የመልዕክት ርዕስ ፦ ያልተያዘና ያልተነካካ ነገር ይሰጥሃልና አንተም አትነካካ ( ክፍል አንድ ) የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ዛሬ ዘፍጥረት ምዕራፍ 24 ን በሙሉ የትምህርታችን ዋና ሃሳብ በማድረግ ተመልክተነዋል :: የርብቃ ቤተሰቦች ርብቃን ሚስት አድርገው ሲሰጡ እንዲህ ነበር ያሉት :: ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል ክፉም በጎም ልንመልስልህ አንችልም ርብቃ እንኋት በፊትህ ናት ይዘሃት ሂድ፥ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ለጌታህም ልጅ ሚስት ትሁን የአብርሃምም ሎሌ ነገራቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእግዚአብሔር ሰገደ ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ ልብስም አወጣ፥ ለርብቃም ሰጣት የከበረ ስጦታንም ለወንድምዋና ለእናትዋ አቀረበ ይለናል ዘፍጥረት ምዕራፍ 24 ፥ 50 - 53 ውድ ወገኖቼ ያልተያዘና ያልተነካካ ሕይወት ከእግዚአብሔር ለመሆኑ የርብቃ ቤተሰቦች የሆኑት ላባና ባቱኤልም ሆኑ ልጃቸው ርብቃ እንዲሁም የአብርሃም ሎሌ ጽኑ ምስክሮች ናቸው :: ስለዚህ ዛሬም በእኛ ዘመን ሥራ ፣ ሕይወት ፣ እጮኝነት ፣ ትዳር አገልግሎትና የመሣሠሉት ሁሉ ከእግዚአብሔር ሲሆኑ ያልተነካኩ የሰውንም ሆነ የእያንዳንዳችንን ነገር ነገር ጣልቃ ያላስገቡ ይሆኑና ከእግዚአብሔር ብቻ ሆነው ለእኛ ይሰጣሉ ታድያ በዚያ ውስጥ በረከት እንጂ ልቅሶም ሆነ ሃዘን የለበትም ለዚህም ነው የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም ያለን መጽሐፈ ምሳሌ 10 ፥ 22 ትምህርቱ ዘፍጥረት ምዕራፍ 24 ን በሙሉ መሠረት አድርጎ የተነሳ ስለሆነ አብርሃምን ፣ የአብርሃምን ሎሌ ፣ ርብቃንና ቤተሰብዋን እንዲሁም የይስሐቅንም ሕይወት ያካተተ ነው ትምህርቱን ለመረዳት የክፍሉን ሃሳብ እንደሚገባ ማጥናትና ማንበብ ያስፈልጋል ለተጨማሪ መረጃ እንዲሆናችሁ ቪዲዮውን መላልሳችሁ ስሙ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የክፍል ሁለት መልዕክት ይቀጥላል ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊ የተሃድሶ አገልግሎት
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment