Thursday, 11 January 2018
የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Challenges ) ክፍል ስድስት ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ?የተሃድሶ ተግዳሮቶች ( Challenges ) ክፍል ስድስት ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው ? ነቢይ ማለት ከእግዚአብሔር የተላከ ማለት ሲሆን መልዕክተኛ እንደመሆኑ መጠን ከዚሁ ከእግዚአብሔር ቃልን ተቀብሎ ለሕዝብ የሚናገር ማለት ነው ( ዘጸአት 7 ፥ 1 እና 2 ፣ ሆሴዕ 12 ፥ 14 ) በነቢይነትም ሆነ በልዩ ልዩ የአገልግሎት ጥሪ ውስጥ ገብተው ማገልገል ለሚፈልጉ የወንጌላውያን አማኞችም ሆነ ለኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን የተላለፈ ትምህርት ( ቊጥር 1 ) የተወደዳችሁ ወገኖች እንግዲህ በቀጥታ ወደ ትምህርቱ ፍሬ ሃሳብ ስንሄድ በዚሁ ቃል መሠረት ትምህርቱ በነቢያቱ ላይ የሚያጠነጥን ይምሰል እንጂ መላክን በተመለከተ የተላኩም ሆኑ ወደፊትም የሚላኩ ነቢያቱ ብቻ ሳይሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል ወደሰዎች የሚያመጡ የቃሉ አገልጋዮችም ልዑካን ናቸው ( ሮሜ 10 ፥ 14 _ 17 ) ይሁን እንጂ ታድያ አሁን ላይ በነቢያቱም ሆነ በቃሉ አገልጋዮች በኩል እየተሰጠ ያለ አገልግሎት ቃሉን የተከተለና መልኩን የጠበቀ ካለመሆኑ የተነሳ በእግዚአብሔር ስም እየተተነበየ ያለው ትንቢቱም ሆነ ስብከቱ መታነጽያ መሆኑ ቀርቶ የመድረክ ላይ መደባደብያና ማደባደብያ ፣ ትዳርን ሳይቀር መፍቻና ማፋቻ በአጠቃላይ ቤተሰብን መበተኛና ጓደኛንም ከጓደኛ መለያያ ማለያያም እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሮአል ከዚህ የተነሳ ሕዝባችንም ሚዛኑን የጠበቀና መጽሐፍቅዱስን ያማከለ ትንቢትም ሆነ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ካለማግኘቱ የተነሳ የመጡትን ትንቢቶችም ሆነ መልዕክቶች ሰምቶ ተጠቃሚ ከሚሆን ይልቅ ለሌላው የሰማና የሚሰማ ሆኖ በመቅረብ ስማልኝማ ፣ ስሚልኝማ ልክ ልኩን ፣ ልክ ልኳን ነገረልኝ እኮ ሴትም ከሆነች አገልጋይዋ ነገረችልኝ እኮ በማለት አብዛኛው ምዕመናችንም ሆነ የቃሉ አገልጋዮችና ነቢያቱም ጭምር በአገልግሎትና በመልዕክተኝነት ስም መስሎ በታየን ፣ ይሆናል ብለን ባመንበትም ነገር ሁሉ ላይ ቊጭታችንን ልንወጣ የልባችንንም ምኞት ልንፈጽም እየተውተረተርን ያለንና እንቅልፋችንን አጥተን የምናድርም ብዙዎች ነን የእግዚአብሔር አገልግሎት ግን መደባደብያና ሌላውንም ማጥቂያ ፣ የግል ጉዳዮቻችንንም ማስፈጸምያ እና ማሟያ አይደለም ውድ ወገኖቼ ሆይ ለዚሁ ሃሳቤ ድጋፍ የሚሆነኝን በነህምያ 6 ፥ 10 _ 14 ላይ ነህምያን፣ ለነህምያም ትንቢት እንዲያመጣ በሰንባላጥና በጦቢያ ተገዝቶ ትንቢት የተናገረውን የሐሰተኛውን ነቢይ የሸማያን ትንቢትም ሆነ ነህምያ የሰጠውን ምላሽ ፣ የወሰደውንም የሕይወት አቋም ከክፍሉ በሰፊው ተመልክተናል ታድያ ይህንን አስመልክቶ የዛሬዎቹ አገልጋዮቻችን ምን ሊሆኑ እንደሚገባ ፣ ለሕዝባችንም የሚሰጡት ትምህርት ምንና እንዴት መሆን እንዳለበት ትምህርቱ ይጠቁማል ቅዱሳን እንግዲህ ጊዜ ወስዳችሁ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተከታተሉ እኔም እርግጠኛ በመሆን በዚህ ትምህርት ብዙዎቻችን ተጠቃሚዎች እንደምንሆን አምናለሁ ትምህርቱ ይቀጥላል ተባረኩልኝ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment