Tuesday, 30 January 2018

የተሃድሶና የከፍታ ዘመን ለኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የተሃድሶና የከፍታ ዘመን ለኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ…. ትንቢተ ኤርምያስ  15 : 19 የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንደምን ሰንብታችኋል ትምህርቶቻችን በጸጋው ጉልበት ተደግፈው ወደፊት እየሄዱ ስለሆነ የእግዚአብሔር ስም ይባረክ የተሐድሶ ተግዳሮቶች( Challenges ) የሚለውን ትምህርት አጠናቅቄ ወደ አዲስ ትምህርት የምገባበት ጊዜ ነው ሐሙስ February 2 / 2018 10 AM በኦታዋ ከተማ የሰዓት አቆጣጠር የምንጀምረው አዲሱን ትምህርት ይሆናል የትምህርቱ ርዕስ «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አመሠራረት» የሚል ሲሆን በዚህ ርዕስ ላይ ተመሥርቼ ቤተክርስቲያኒቱ መቼ እንደተመሠረተችና መሠረቷም እንደ እግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚመስል ? መቼ እንደተበላሸች ? ወደ ተረትና የስሕተት ትምህርቶች ደግሞ መቼ እንደገባች ? በአሁኑ ሰዓትም ከዚህ ስሕተቷና ተረትዋ እንድትመለስ ከዚህ በፊት የነበሩት አባቶች የቱን ያህል ዋጋ እንደከፈሉ ? ዛሬም ይህቺው ቤተክርስቲያን ታድሳና ተለወጣ ፣ ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃልም ተመልሳ ፣ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ሳይቀር በረከት መሆንዋን የሚያውቁ ሰዎች ዛሬም ድረስ ዋጋ እየከፈሉላት ያሉ መሆናቸውን የሚጠቁም ትምህርት ነው የሚተላለፈው ስለዚህ ወገኖች ትምህርቱ እንዳያመልጣችሁ በሰዓታችሁ በመገኘት የትምህርቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ ስል መልዕክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ በዛሬው ዕለት በዚሁ በዕለተ ሰኞ የለቀኩት ቪዲዮ ግን ሐሙስ ለምንጀምረው ለዚህ ትምህርት እንደመግቢያ የሚሆን ትምህርት ነው ተሃድሶ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ እውነተኛ ተሃድሶም የሚመጣው በምን መንገድ እንደሆነ ፣ እውነተኛው የሕይወት ተሃድሶ እንዲመጣ ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ሕይወት መጋበዝ እንደሚያስፈልግ መልዕክቱ ይጠቁማል ይህንንም ለማግኘት ኢየሱስ በዚች ቤተክርስቲያን ውስጥ በግልጽነት ሊሰበክ እንደሚያስፈልገው ፣ ይሄ ጌታ ሲሰበክ ደግሞ በስሙ ንስሐና የኃጢአት ሥርየት እንደሚገኝ እንደገናም ሰው ሁሉ ይህንን ንስሐና የኃጢአቱን ሥርየት ለማግኘት ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ወደ ነፍስ አባቱና ለንስሐ ወደሚጠመቅበት ወደ ቄደሩ እንዲሁም ወደ ውሃ መረጨቱ መሄድ ሳይሆን ለኃጢአት ይቅርታ ባፈሰሰው ደሙ ወደሚረጨን ወደ ኢየሱስ በመምጣት ኃጢአትንም ተናዞና ሽክምን አውርዶ በዚህ ጌታ በደሙ በመታጠብ ፍጹም የሆነ ሥርየትና የእግዚአብሔርን ይቅርታ እንደሚያገኝ ፣ የዘላለም ሕይወት ባለቤትም እንደሚሆን ትምህርቱ ይጠቁማል ወገኖች በጣም አከብራችኋለሁ ወዳችኋለሁ ሐሙስ ለሚጀምረው አዲሱ ትምህርት ተዘጋጅታችሁ ኑ በማለት መልዕክቴን በድጋሜ ለማሳሰብ እወዳለሁ ሰዎችን መጋበዝ አትርሱ በቀጠሮአችንንና በሰዓታችን እስክንገናኝ ተባረኩ የምላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

No comments:

Post a Comment