Thursday, 18 January 2018

የእንጨቱ መስቀል ከአምላክ ጋር በእኩል ዓይን ታይቶ የተፈለገበትና የተመለከበት አሳፋሪ ታሪክ እና የደብረ ታቦር የ...የእንጨቱ መስቀል ከአምላክ ጋር በእኩል ዓይን ታይቶ የተፈለገበትና የተመለከበት አሳፋሪ ታሪክ እና የደብረ ታቦር የበዓል ትረካ አኮ ከመ ይትረዓይ አላ ከመ ይትሐለይ ውእቱ ዝንቱ መስቀል የሚታሰብ እንጂ የሚታይ መስቀል ለእኛ የለንም ( ምንጭ ትምህርተ ኅቡዓት መጽሐፍ ) እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐተ ስግደተ …………. እሰግድ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ስብሐት ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ አምላክን ለወለደች ለድንግል ማርያም እሰግዳለሁ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እሰግዳለሁ ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስቅዱስ ምስጋና ይገባል አምላክን ለወለደች ለድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባል ለእነዚህ ሁሉ በቅደም ተከተል ለተቀመጡት ምስጋናና ስግደቶች የዘወትር ጸሎት የተባለው መጽሐፍ ፦ ይደልዎሙ ለአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ ይደልዋ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ይደልዎ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲል ሕዝባዊ መልስ ይሰጣል ሕዝቡ ለዚሁ ስግደትና ምስጋና እንዲሁ ሲል መልስ ሰጥቶአልና ወደ አማርኛ ስተረጉመው ይደልዎሙ ፣ ይደልዋ ፣ ይደልዎ የሚሉት የግዕዙ ቃላት ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ ፣ ለወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የተቀጸሉ ናቸውና ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ ስግደትም ሆነ ምስጋና ይገባቸዋል አምላክን ለወለደች ለድንግል ማርያም ይገባታል ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ይገባዋል እያለን ነው ያለው ( ምንጭ የቤተክርስቲያኒቱ መጽሐፍ ጸሎት ዘዘወትርን ይመልከቱ ) ታድያ የጸሎት መጽሐፉ ይህን ካለ እኛስ ይደልዎሙ፦ ይገባቸዋል ፤ ይደልዎ ፦ ይገባዋል ፤ ይደልዋ ፦ ይገባታል ስንል ማንን አምላክና ጌታ ብለን እርሱን እናምልክ ? ለማንስ እንስገድ ? ደግሞስ የሚታሰብ እንጂ የሚታይ መስቀል ከሌለን ከሥላሴ እኩል ቦታ ተሰጥቶአቸውና ሊመለኩ ተወስነው የቀረቡ እነዚሁ ግዙፋን መስቀሎች እንዴት ወደ መታየት መጥተው ሊመለኩ ጊዜ ሆነላቸው ? እንዴትስ ተፈቀደላቸው ? መልሱን ለእናንተ ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው የሉቃስ ወንጌል 4 : 8 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትአይሁኑልህ…………….. ኦሪት ዘጸአት 20 : 3 - 6 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትአይሁኑልህ……………… ኦሪት ዘዳግም 5 : 7 - 10 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም ( ትንቢተ ኢሳይያስ 42 : 8 ) ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ ስሜ ተነቅፎአልና፤ ክብሬንም ለሌላ አልሰጥም ( ትንቢተ ኢሳይያስ 42 : 11 )

No comments:

Post a Comment