Wednesday, 31 January 2018

በስድብና በቅንዓት ዙርያ የተዘጋጀ ተከታታይ ፣ ወቅታዊና ትምህርት አዘል የክፍል አንድ ውይይት ከተወደደው ወንድማች...በስድብና በቅንዓት ዙርያ የተዘጋጀ ተከታታይ ፣ ወቅታዊና ትምህርት አዘል የክፍል አንድ ውይይት ከተወደደው ወንድማችን ቢንያም ጋር የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው ትምህርታችን ያጠነጠነው በስድብ ዙርያ ላይ ሲሆን በክፍል ሁለት ትምህርታችን ደግሞ የቅንዓትን አላስፈላጊነት ይዘን እንቀርባለን እነዚህ ትምህርቶች ወቅታዊና ከሕዝባችን አመለካከት እንዲሁም አስተሳሰብ ጋር በተጓዳኝነት ተያይዘው የቀረቡ በመሆናችው ሕዝባችንን ከዚህ ዓይነቱ የጨለማ አሠራር ለመታደግና ለማዳን ሲባል የተዘጋጁ ትምህርቶች ናቸው ሕዝባችን በተገቢው መንገድ የእግዚአብሔርን ቃል ካለማጥናቱና ካለመማሩም የተነሳ ለሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም ያገለገለ እየመሰለው ለወንጌል እውነት ቆርጠው የተነሱ አባቶችንና ወጣት አገልጋዮችንም ጭምር ሃይማኖት አፍራሽ ፣ ጡት ነካሽ ፣ ሐራ ጥቃ ፣ ተሐድሶና የመሣሠሉትን ናችሁ እያለ ፣ ስምም እያጠፋ አጋጣሚዎችን ሲያገኝ ደግሞ መንገድ ጠብቆ ልብሳችንን አውልቁ ፣ አስረክቡን እያለ እያስፈራራና እየደበደበ ከዚህም ሌላ የቃሉን መመርያ ተከትሎ ወንጌል በገባቸው አባቶች የተጻፉ መጻሕፍቶችንም እያቃጠለ በተጨማሪም በየፌስቡክ ሚዲያውና በየዩቲዩቡም ሳይቀር ተመሣሣይ የሆኑ ስድቦችንና ማስፈራራቶችን እያካሄደ ስላለ እኛ የዚህ ዘመን የቃሉ አገልጋዮች ትውልዱ ለምን ይህን አደረገ ፣ ለምንስ ተሳደበ ፣ ተቆጣና ስማችንንም አጠፋ ስንል ለመብታችን ተቆርቁረን ፣ ራሳችንንም ለመከላከልና መልስ ለመስጠት ብለን ወይንም ማስፈራራቱም ሆነ ዱላው አስደንግጦን ስጋት ላይም ጥሎን እንዲህ ያልን ሳይሆን ትውልዱ ለሃይማኖት ከመቅናት አኳያ እየሄደበት ያለው የስድብና የማሳደድ መንገድ ውሎ አድሮ የሚያስከፍለውን ዋጋ መጽሐፍቅዱሳችን ግልጥ አድርጎ ስለነገረን ትውልዱም ይህንን የእውነት ቃል አውቆና ተረድቶ ከዚህ ዓይነቱ የዓመጻ መንገድ ራሱን እንዲለይ ለመርዳት ብለን ነው እኛን የቃሉ አገልጋዮችን በተመለከተ ግን ይሄ ጉዳይ ሰው እንደመሆናችን መጠን የሚያሳስበን እንኳ ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ በማለት ቃሉ የነገረን በመሆኑ የመጣውን ነገር ሁሉ በምስጋና ለመቀበል እየተዘጋጀን ነፍሳችንን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ሰጥተናል 1ኛ ጴጥሮስ 4 ፥ 19 ከዚህ የተነሳ ጌታ ባበዛልን ጸጋ መጠን ሐዋርያው እንደነገረን ሲሰድቡን እንመርቃለን ሲያሳድዱን እንታገሣለን ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን 1ኛ ቆሮንቶስ 4 ፥ 11 _ 13 የወንጌል ባሕርዩ ይሄ ስለሆነ ይህንኑ ልናደርግ ራሳችንን በማማጠን ላይ እንገኛለን 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 3 _ 13 ቅዱሳን ወገኖች ዛሬ የለቀቅነው ትምህርትም ሆነ የሚቀጥለው ዓርብ ይዘን የምንቀርበው ትምህርት ወሳኝና ሕይወታችንንም በብዙ የሚለውጥ ትምህርት በመሆኑ አያምልጣች ስል ላበረታታችሁ እወዳለሁ ዛሬ የተለቀቀውን ቪዲዮም ሆነ ዓርብ ዕለት የሚለቀቀውን ሼር ማድረግ አትርሱ አባ ዮናስ ጌታነህ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

No comments:

Post a Comment