Thursday, 15 June 2017
ሥዕል በቤተ ክርስቲያን መቼ ተጀመረ ክፍል አራት ሥዕል በቤተ ክርስቲያን መቼ ተጀመረ ክፍል አራት የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል አራት ትምህርታችን ሥዕል በቤተክርስቲያን የተጀመረበትን ጊዜ ትምህርቱ በሰፊው ከተረከልንና ካብራራው በኋላ ከመከራው ጽናት የተነሳ በዚያን ዘመን የነበረው ክርስቲያን በዋሻ ወይም በግበበ ምድር ውስጥ ጌታን ያመልክ ስለነበር የክርስትናን ትምህርት አስፋፍቶ ለመስጠት በቂ መጻሕፍት አልነበሩም ፣ እንደ ልብ ወጥቶ ለመፈለግና ለማዘጋጀትም ነጻነት ስላልነበረቸው በዚያን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍቅዱስ ውስጥ አንዳንድ ምሳሌዎችን በሥዕል እያሰፈሩ ማስተማር ጀመሩ ብለናል አያይዘንም በዚህ ሁኔታ ሥዕል ማስተማርያ ሆኖ የቆየ መሆኑንም ተናግረናል ሥዕሎችም የሚሳሉት በምሳሌነት Symbol ( ሲምቦል )ሲሆን የሚሳሉትም በአመድና በከሰል በዋሻ ዙርያ እንደሆነ ታሪክ ይናገራል ወደ ዋናው ሃሳብ ስመጣ ሥዕሎች መጽሐፍቅዱሱን ተመስርተው በዋሻ ውስጥ በመሳል ትምህርት ሲሰጥባቸው የቆዩ ቢሆንም እስከ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመርያ ድረስ ሥዕል በቤተክርስቲያን እንደተጠበቀ ቆይቶ በዚሁ በሥዕል ምክንያት በሮምና በቢዛንታይን ግዛት በሚኖሩ ምዕመናን መካከል አለመግባባት ተፈጠረ በዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ አንዳንድ ክርስቲያኖች ሥዕልን ከመውደዳቸው የተነሳ ሥዕሎችን አማልክት ናቸው እስከ ማለት መድረሳቸውን ትምህርቱ የሚጠቁመን የትምህርቱ ሃሳብ በይበልጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ያጠነጠነ ነው ትምህርቱን ደረጃ በደረጃ ለማየት ቢያስፈልግ ፦ 1ኛ ) ከእግዚአብሔር በላይ የምንወደው ነገር ሊኖር አይገባም የሚል ማብራርያ የያዘ ነው የሉቃስ ወንጌል 10 : 27 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 10 ; 37 ፣ የማርቆስ ወንጌል 12 : 30 ፣ 33 2ኛ ) ኢያሱ እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን እናንተ ግን የምታመልኩትን ምረጡ ያለ ነበር ኢያሱ 24 ፥ 15 3ኛ ) ኤልያስም ደግሞ እስከመቼ በሁለት ሃሳብ ታነክሳላችሁ ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ በአል ግን አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ አለ ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም 1ኛ ነገሥት 18 ፥ 20 _ 22 4ኛ ) ከእግዚአብሔር ጋር የምንጣበቀው በ2ኛ ነገሥት 18 ፥ 1 _ 8 በተጻፈው ቃል መሠረት እንደ ሕዝቅያስ በኮረብታ ያሉትን መስገጃዎች አስወግደን ፣ ሐውልቶችንም ቀለጣጥመን ፣ የማምለክያ አጸዶችንም ቆራርጠን ብቻ አይደለም የእስራኤልም ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ እንደ ሰራው ዓይነት የናስ እባብ የመሰለን ነገር ሰባብረን ፣ ስሙንም ነሑሽታን ብለን ነው ከእግዚአብሔር ጋር የምንጣበቀው በማለት ይህንን ሃሳብ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 19 ፥ 19 ከተጻፈው ቃል ጋር በማያያዝ ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር በማለት የጌታ ቃል ያሸነፋቸው ሰዎች የወሰዱትን እርምጃና ከእግዚአብሔር ጋር በሐዲስ ኪዳን ሳይቀር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የተጣበቁበትን እውነተኛ የሕይወት ትስስርና ዘላለማዊ የሆነን መጣበቅ ተመልክተናል ቪዲዮውን ደጋግማችሁ ስሙት ትባረኩበታላችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የክፍል አምስት ትምህርት ይቀጥላል ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment