Thursday, 22 June 2017

የሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስድስትየሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስድስት የክፍል ስድስት ትምህርት ከክፍል አምስት ትምህርት ጋር በተያያዥነት የቀረበ ነው የቅድስት ሥላሴን ሥዕል በተመለከተ በቀረበው ሥዕላዊ ማብራርያ መሠረት ሥላሴ እንዲህ ስለሆኑ አምልኮ ይገባቸዋል ስንል ሥዕልን ስለንና ሥዕላዊ ማብራርያ ሰጥተን ማምለክ አንችልም ምክንያቱም የእግዚአብሔር ነገር ጥልቅና ሊመረመር የማይቻል ሲሆን የእግዚአብሔር ምስጢር ግን ክርስቶስ ስለሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ምስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ በእርሱ ነውና በማለት የእግዚአብሔር የሦስትነትና የአንድነት ምስጢር እንዴት እንደተገለጠ ትምህርቱ በሰፊው ያብራራልናል አያይዞም የድንግል ማርያምን የአለባበስ ሁኔታ በሰፊው ከዘረዘረ በኋላ የልብስዋ ቀለም አቀባብም ከላይ ሰማያዊ ከውስጥ ደግሞ ቀይ ሆኖ ይሣላል ቀይ ከውስጥ መሆኑ እሳተ መለኮትን በማኅጸንዋ መሸከምዋን ለማስረዳት ነው ሰማያዊት ናትና ከላይ ያለው ሰማያዊ ቀለም ይደረጋል አንድም ከላይ ሰማያዊ ከውስጥ ቀይ መሆኑ ክብሯ ሰማያዊ ያውም መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፈጣሪ በታች እንደሆነች ተደርጎ ይነገራል የሚል ትረካ ሰምተናል ይሁን እንጂ ሥዕሉም ሆነ የሥዕሉ የታሪክ ገጽታ ትክክል ያልሆነና ኢመጽሐፍቅዱሳዊም በመሆኑ ፍጹም አንቀበለውም ለበለጠ መረጃ ቀይና ሰማያዊ የለበሰችበትን ሥዕሏን ከዚህ ትምህርት መልስ እለቀዋለሁና ተከታተሉ መጽሐፍቅዱሳችንን ስናጠና ድንግል ማርያም ኢየሱስን የወለደችው በሥጋ ነው ለምን ስንል ኢየሱስ በሥጋ የተወለደ መሆኑን ለማመልከት የእግዚአብሔር ቃል በዕብራውያን 2 ፥ 16 ላይ የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላዕክትን አይደለም ይለናል የቤተክርስቲያን መጽሐፍም ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርዓ ብዕሲ ወአድሃነነ አለን ወደ አማርኛው ስተረጉመው ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንግል ተወለደ ተወልዶም አዳነን " በሥጋ አለ በመለኮት አትወልደውምና " አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትስብዕቱ እንዲል ( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ትርጓሜ ) ከዚህ የተነሳ ድንግል ማርያም ኢየሱስን በሥጋ የወለደችው በመሆኑ ወላዲተ ኢየሱስ ትባላለች እንጂ ወላዲተ አምላክ ብለን እንድንጠራት መጽሐፍ አያስተምረንም እንደገናም ወላዲተ አምላክ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ አለማመን ስለሆነ ትልቅ ስሕተትና የኑፋቄ ትምህርት ነው 1ኛ ዮሐንስ 4 ፥ 1 _ 6 ፤ ሮሜ 9 ፥ 4 እና 5 የኃጢአት ሥርየት ያገኘነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል ስለተወለደ ነው እንደገናም ወንድሞቼ ሊለን ያላፈረብንና በነገር ሁሉ እንደኛ የተፈተነ ፣ የሚፈተኑትንም የሚረዳ ፣ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህን የሆነው ፣ ኃጢአትን ስለመተውም በእግዚአብሔር ችሎት ፊት ጽድቁን ያሳይ ዘንድ የኃጢአት ማስተሥረያ ሆኖ የቆመልን ፍጹም አምላክ ብቻ ሳይሆን ፣ በሥጋ የመጣ ፍጹም ሰውም ስለሆነ ነው ዕብራውያን 2 ፥ 13 _ 18 ፤ ሮሜ 3 ፥ 21 _ 26 ከዚህም ሌላ ኢየሱስ የሰው ልጅ በመሆኑ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ ለአይሁድ በውል ሳይገባቸው ኢየሱስን እንደጎሰሙትና ፊቱንም ሸፍነው ኢየሱስ ሆይ ማነው የመታህ ? ትንቢት ተናገር ያሉት ፣ ኢየሱስ በሥጋ የመጣበትን ምስጢር በውል ስላልተረዱና ስላልተገነዘቡ እንደሆነ ሁሉ ለእኛም ለኦርቶዶክሳውያን አማኞች ያለው ነገር ይኸው ነው ታድያ ኢየሱስ የሰው ልጅ ሆኖና በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ የማይቀር ፣ ተመልሶም በደመና በብዙ ክብር እንደሚመጣ እየነገረን ኢየሱስ በአብ ቀኝ ከተቀመጠ በኋላ ፈራጅ ነው እንጂ የሚያማልድ አይደለም ማለታችን ኢየሱስን በሥጋ እንደመጣ አለማመንንን የሚያሳይ ነውና መረዳታችንን በእግዚአብሔር ቃል እውቀት ከፍ ልናደርግ ልናስተካክልም ይገባል እላለሁኝ ማቴዎስ 26 ፥ 63 _ 68 ፤ ሉቃስ 22 ፥ 66 _ 71 ሌላው ድንግል ማርያምን ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ማለት ሰው የሆነችበትን እውነት መካድ ስለሚሆንብን ፍጹም ስሕተት ነው ለምን ስንል መጽሐፍቅዱሳችን ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ ይለናል የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 26 _ 38 የተወደዳችሁ ወገኖች የትምህርቱ ሃሳብ እንግዲህ በአጭሩ ይህንን ይመስል ነበረ ቪዲዮውን ተከታተሉ ሰምታችሁም ለሌሎች ሼር አድርጉ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ተባረኩ የክፍል ሰባት ትምህርት ይቀጥላል ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment