Thursday, 8 June 2017
እግዚአብሔር ሙሴን ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ማለቱ ክፍል ሁለትእግዚአብሔር ሙሴን ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ማለቱ ክፍል ሁለት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የክፍል ሁለት ትምህርታችንን ጀምረናል ጌታ እግዚአብሔር ሦስት ታላላቅ መመርያዎችን ለሙሴ ነግሮት ነበር 1ኛ ) ከግራር እንጨት ታቦትን ይሥሩ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን …………………..ዘጸአት 25 ፥ 10 _ 17 2ኛ ) ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ በሥርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ ……………….. ዘጸአት 25 ፥ 18 እና 19 3ኛ ) በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ እኔ እንደማሳይህ ሁሉ እንደ ማደርያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ እንዲሁ ሥሩት አለ ዘጸአት 25 ፥ 8 እና 9 ተመልከቱ ውድ ወገኖቼ ሆይ ታድያ ጌታ እግዚአብሔር ለምን ይሆን ? ታቦት ሥሩልኝ ፤ ኪሩብ ሥሩልኝና መቅደስ ስሩልኝ ሲል መናገሩ ? እኛም እነዚህ ሦስት ዓበይት ሃሳቦች በቃሉ ላይ ስለተጻፉ ዛሬም ሆነ ከዚህ በኋላ በቀረው ዘመናችን ታቦትን ፤ ኪሩብንም ሆነ መቅደስን መስራት እንዳለብን ከእኛ ይጠበቃል ? ለዚህ መልሱ አንድና አንድ ነው እርሱም ጌታ እግዚአብሔር ታቦት ሥሩልኝ ፤ ኪሩብ ሥሩልኝና መቅደስ ስሩልኝ ሲል የተናገረውና መመርያንም የሰጠው ለእነ ሙሴ ነው እኛን አይደለም ስለዚህ ታቦትንም ሆነ መቅደስንና ኪሩብን እንድንሰራ ለእኛ የተፈቀደ ነገር አይደለም እኛም እንድንሰራ አልታዘዝንም ሌላው ደግሞ እግዚአብሔር ታቦትን ፤ መቅደስን ፤ ኪሩብን ሥሩልኝ ማለቱ እስከ ዛሬ ድረስም ሆነ ከዛሬ በኋላ ባለው ለወደፊቱም ይህንኑ ታቦት ፤ መቅደስና ኪሩብ እየሠራችሁ በነዚህ ነገሮች አምልኩኝ ፤ ስገዱልኝ ፤ አክብሩኝ ለማለት አይደለም እንደውም በዚህ ነገር ውስጥ ኖረው የሚያመልኩት ሰዎች አምልኮአቸው አስጸያፊና የጣኦት አምልኮ እንደሆነ ነው ቃሉ የሚነግረን ትንቢተ ሕዝቅኤል 8 ፥ 7 _ 13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር መቅደስን ፤ ታቦትንና ኪሩብን ሥሩልኝ ሲል መናገሩ በዘጸአት 25 ፥ 21 እና 22 ፤ በዘኁልቁ 7 ፥ 89 መሠረት ታቦቱ ላይ ካለው ከሥርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል አምላካችን የሆነው እግዚአብሔር ድምጹን ለማሰማት ነው በአጠቃላይ ለግንኙነትና ለኅብረት ነው ስለዚህ እነዚህ ሦሰት ዋና ዋና ነገሮች ማለትም ታቦቱ ኪሩቡና መቅደሱ የተፈለጉት ለእግዚአብሔር የግንኙነቱ መስመር መንገድ እንዲሆኑ ነው ዛሬ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ የግንኙነት መንገዱም ሆነ መስመሩ ክርስቶስ ሲሆን እግዚአብሔርም በዚህ ጌታ አማካኝነት ከእኛ ጋር ሆኖአል ክብር ለስሙ ይሁንለት ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 14 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 23 ፣ ራዕይ 21 ፥ 3 እና 4 ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 16 እና 17 ፣ የሐዋርያት ሥራ 7 ፥ 47 _ 50 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህንን የተቋረጠውን ግንኙነት መቀጠል የፈለገው የመጀመርያው ሰው አዳም በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ካበላሸበት ጊዜ ጀምሮ ነበር ታድያ አዳም ሆይ ወዴት ነህ ? ሲል በገነት ውስጥ መፈለጉ እግዚአብሔር የነፍስን ጥፋት አይወድምና ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ ማሰቡን የሚያመለክተን በመሆኑ አምላካችንን በብዙ እንድናመሰግነው እንሆናለን በሐዲስ ኪዳንም ኢየሱስን የላከልን ከጠፋንበት ፈልጎ ሊያገኘንና ከራሱ ጋር ኅብረት እንድናደርግ ሊያደርገን ነው የሉቃስ ወንጌል 15 ፥ 4 _ 9 ፣ የሉቃስ ወንጌል 19 ፥ 1 _ 10 እንመልከት ስለዚህ የእግዚአብሔር መሠረታዊ ሃሳቡ ተዘጋጅተው የቀረቡለት ሥዕልና ታቦት እንዲሁም ቤተመቅደስ ሳይሆን በእነዚህ በተፈለጉትና ይሠሩልኝ በተባሉት ነገሮች በኩል ከሰዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ ነው በሐዲስ ኪዳን ይህ ግንኙነት ተጠናክሮ በኢየሱስ በኩል ዘለዓለማዊ ሆኖአል በመሆኑም ስለ ኅብረት ስናስብ ብዙ የሆኑ አዳማዊና አሮጌ የሆነ አስተሳሰባችንን እንድንለውጥ ትምህርቱ ይጠቁማል ጌታ የጠራን ለኅብረት ነውና ታድያ ውድ ወገኖቼ ሆይ ጌታ ለኅብረት ሲጠራን በማርቆስ ወንጌል 3 ፥ 14 መሠረት ከእርሱ ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው ስለሚል ………………….. ከአገልግሎታችንና ከስሞቻችን በፊት በቅድሚያ ከእርሱ ጋር መኖርን መውደዳችንን እንድናስቀደም ነው እንደገናም የተጠራነው ለአገልግሎት ሳይሆን በመጀመርያ ለኅብረት ስለሆነ ከእርሱ ጋር የሚኖረን ኅብረት ትክክለኛ የሚሆነው በአገልግሎት ጉዞ ውስጥ ሳይሆን ከእርሱ ጋር በመኖር ውስጥ ነው ስለሆነም ከእርሱ ጋር በመኖራቸው ምክንያት ደቀመዛሙርት የትላንት አሮጌ አስተሳሰባቸውን ማለትም ከመካከላችን ማነው ታላቅና አንዳችን በግራ አንዳችን በቀኝ መቀመጥን ስጠን የሚሉትን ፣ ሌሎችንም ምድራዊ አስተሳሰባቸውን ጥለው ጌታን አይተነዋል ለማለት የበቁት ቅድሚያውን ይዘውና የኃላፊነቱንም ቦታ ተረክበው ስላገለገሉ ሳይሆን ከሕይወት ጅማሬያቸው አንስተው ከጌታ ጋር መኖርን ስላስቀደሙ ነው አያይዘውና ቀጥለውም በዓይኖቻቸን ያየነውን የተመለከትነውን እጆቻችንም የዳሰሱትን ይህንን ጌታ እናወራላችኋለን ሕይወት ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን አሉን 1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 1 ፥ 1 _ 4 ለእኛም እንዲህ ይሁንልን የክፍል ሦስት የሥዕል ትምህርት ይቀጥላል ተባረኩ ሰላም ሁኑ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment