ምዕራፍ ሁለት
ርዕስ
የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ?
Topic
How to understand the bible ?
ክፍል አንድ
1) በትሕትና መንፈስ
እግዚአብሔር እንዲረዳን ለትሕትና መጸለይ አለብን ይህ የመጀመርያው ቃሉን የመረዳት ቁልፍ ሃሳብ ነው ነገር ግን መጽሐፉ እንደሚነግረን ወደዚህ ወደ ትሑት መንፈሱም ወደ ተሰበረ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ ይለናል ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ፥ 2 መንፈሱም ወደተሰበረ ማለት በእንግሊዘኛው Repentant spirit ማለት ነው የንስሐ መንፈስ ያለው ማለትን ያመለክተናል የእግዚአብሔር ቃል መረዳት የአዕምሮ ማስተዋል ችሎታ ፣ የማወቅ ችሎታ ፣ ብልህነት እና የበላይነት ጉዳይ አይደለም understanding God’s word is not a
matter of superior attitude እግዚአብሔር ለእኛ በውሳኔ መረዳትን ለመስጠት ልባችንን አስተሳሰባችንን አስተያየታችንንና አቀራረባችንን ያያል በሐዋርያት ሥራ 10 ፥ 34 እና 35 ላይ
ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ አለ በሉቃስ ወንጌል 10 ፥ 21 እና 22 ላይ ደግሞ በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትሕ እንዲህ ሆኖአልና ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ ይለናል
የእግዚአብሔርን ቃል በመረዳት ዙርያ የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ጥቅም አለው ጥቅሙም ከዚህ እንደሚከተለው ነው በሉቃስ ወንጌል 24 ፥ 44 እና 45 ላይ መጽሐፉ እንዲህ ይለናል እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው ይለናል ይህ ማለት እንግዲህ መጽሐፉን መያዛቸው እና መጨበጣቸው የብልህነትና የአዕምሮ ማስተዋል ችሎታቸው ጉዳይ ሳይሆን እግዚአብሔር አዕምሮአቸውን ከፍቶላቸው ነው
በ1ኛ ቆሮንቶስ 2 ፥ 13 _ 14 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም ይለናል ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቃል የገለጠው እግዚአብሔር ነው የሚጨመርለትና የሚቀነስለት መጽሐፍ ሆኖ ለመረዳትም የሰዎችን ብልህነትና የአዕምሮ ማስተዋል ግምትና ጥረትን አልጠየቀም እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ይጥቀመን ተባረኩልኝ
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment