በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት
Actively
Read and Study the Bible
ክፍል አንድ
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2 ፥ 15 እንደገናም በኤፌሶን 1 ፥ 13 ላይ እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ ይለናል በመሆኑም መጽሐፍቅዱሳችንን በንቃት ከምንጊዜውም በተለየ ሁኔታ የምናጠናበት ምክንያት ቃሉ የእውነት ቃልና የመዳን ቃል ስለሆነ ነው ታድያ ይህ የእውነት ቃልም ሆነ የመዳን ቃል አምነን ስንከተለው እንድንሆንለት የሚፈልገው ነገርና የሚያደርገንም ነገር አለ እንድንሆንለት የሚፈልገው ነገር ቃሉን በቅንነት የምንናገርና የማናሳፍር ሠራተኛ ሆነን የተፈተነውን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ልናቀርብ መትጋት የሚያደርገን ነገር ደግሞ ይህንን የእውነትን ቃልና የመዳንን ወንጌል ሰምቶ መቅረት ብቻ ሳይሆን ሰምቶ በክርስቶስ በማመን በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ መታተም ነው ታድያ ይህ
ሊሆን የሚችለው ግን በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት ስንችል ነው ከዚህም ሌላ ይሄ የእውነት ቃል ለፍጥረቱ የበኲራት ዓይነት እንድንሆን መንፈሳዊ ልደትን የሚሰጠን ነው ለዚህም ነው በያዕቆብ 1 ፥ 18 ላይ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን የሚለን በመሆኑም በቆላስያስ 1 ፥ 15 ላይ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል ስለዚህ ይሄ ጌታ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ የወለደን ብቻ ሳይሆን በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል ስለሚለን ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል ስለሆነም መጽሐፍቅዱሳችንን በንቃት ስናነብና ስናጠና እንግዲህ ይህ የእውነት ቃል የሥነፍጥረት ፈጣሪና መገኛ መሆኑን ፣ የበኲራት ዓይነት የሆንበትን መንፈሳዊ ልደት አስገኚ መሆኑንም ጭምር እናይበታለን ለዚህም ነው ጊዜያችንን በእቅድና በመደበኛነት አስተካክለን በንቃት መጽሐፍቅዱሳችንን ለማንበብና ለማጥናት የተዘጋጀን እንድንሆን የሚያስፈልገን እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ ሲል ሐዋርያው የጻፈልን ኤፌሶን 5 ፥ 15 _ 17 በጊዜና በእቅድ ውስጥ ሆኖ በመደበኛነት መጽሐፍቅዱሱን በንቃት ለማንበብና ለማጥናት የሚተጋ ሰው ጥበበኛና እንዴት እንዲመላለስ የተጠበቀ የቀኖችን ክፋት የሚያውቅ የጌታን ፈቃድ ያስተዋለ ነው ይህ ሰው እንዲህ ሲሆን ታድያ ዘመኑን ሳይቀር እየዋጀ በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ጭምር የሚመላለስ ነው ቆላስያስ 4 ፥ 5 መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም በኤፌሶን 5 ፥ 10 ላይ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ እያለን በተደጋጋሚ የሚናገረን ለዚህ ነው ጌታ በምናነበው ቃል ይባርከን ተባረኩልኝ
ለተጨማሪ እነዚህን ሃሳቦች በእንግሊዝኛም ጭምር በጥቂቱ
አብራራቸዋለሁ እና ተከታተሉ
1-
Actively
Read and study the Bible
2- Plan time for regular study
It`s easy to
let everyday concerns interfere so schedule study time and try to maintain it. Over
time you will look forward to this daily experience.
Servant of
Lord Priest and Preacher Yonas Getaneh
No comments:
Post a Comment