Monday, 4 May 2015

Seeking Guidance የተማርነውን መያዝ Holding on to what we learn ክፍል ሰባት

Seeking Guidance

የተማርነውን መያዝ


Holding on to what we learn


ክፍል ሰባት


እውነትን ግዛት አትሽጣትም ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም

ምሣሌ 23 23

እርሱም እንዲህ አለ፦ ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌ ነው ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው በመንገድ ዳርም ያሉት የሚሰሙ ናቸው፤ ከዚህ በኋላም ዲያብሎስ ይመጣል አምነውም እንዳይድኑ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል በዓለት ላይም ያሉት ሲሰሙ ቃሉን በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ እነርሱም ለጊዜው ብቻ ያምናሉ እንጂ በፈተና ጊዜ የሚክዱ ሥር የሌላቸው ናቸው በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው ይለናል የሉቃስ ወንጌል 8 10 _ 15 ወገኖቼ ቃሉን ሰምቶ መጠበቅ የተማሩትን መያዝ ነው ፍሬ የሚያፈሩ ደግሞ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁ ማለት የተማሩትን የሚይዙ በዚያም ቃል የሚጸኑ ናቸው ስለዚህ ፍሬ ለማፍራት ቃሉን ሰምቶ መጠበቅ ማለት የተማሩትን መያዝና በዚያም ቃል መጽናት ነው ያልተማረ ሰው ቃሉን መያዝም ሆነ መጠበቅ አይችልም ቃሉን ለመያዝና ለመጠበቅ ደግሞ መማር የሁሉም ሰው ተግባር ሊሆን ይገባል ታድያ ብዙ ሰዎች ባንልም ከብዙዎች ጥቂት የሆንን  የመማር ፍላጎቱና መሻቱ ስላለን እንማራለን የተማርነውን ግን  ለመጠበቅና በዚያም ለመጽናት ያለን ጥረት አናሳ በመሆኑ የምናፈራው ፍሬ በጣም ጥቂት ነው የተማሩትን መጠበቅና መያዝ እንዳይኖር ደግሞ ሌላው የሰዎች ባላንጣ የሆነው ሰይጣን ሰዎች አምነው እንዳይድኑ ቃሉን ከልብ ይወስዳል  እንደገናም ሰዎች የተማሩትን ቃል ከመያዝና በመጽናትም ፍሬ ከማፍራት ይልቅ ቃሉን በደስታ በመስማት ብቻ የሚቀመጡ ናቸው ስለዚህ መከራ በመጣ ጊዜ ፈጥነው ይክዳሉ በማለት ቃሉ ይነግረናል በመሆኑም ቃሉ ለደስታችን የመጣ በመስማት ብቻ የሚያስቀምጠን ሳይሆን ይህን የሰማነውንና የተማርነውን ቃል በመያዝ በዚያም ላይ በመጽናት ወደ ፍሬ ማፍራት መምጣት ከእኛ ይጠበቃል ሐዋርያው ጳውሎስ ከዚህ የተነሳ ነው 2 ተሰሎንቄ 2 9 _ 12 እንደገናም ቁጥር 15 ላይ ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ ይለናል ይህ እንግዲህ በእርግጠኝነት ማድረግ ያለብን በመታመን ከእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ጋር መጣበቅ ነውና የተማሩትን መያዝ ማለት እንዲህ ነው ከዚህም ሌላ በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3 15 ላይ ከሕፃንነ ትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል በማለት ጢሞቴዎስን ሲነግረው እንመለከታለን እንግዲህ ሰው ሲማር እንደ ጢሞቴዎስ ያውቃል መማር ከሌለ ግን ማወቅ የለም እንደገናም በቆላስያስ 1 9 _ 10 ላይ ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን ይለናል በመሆኑም ስንማርና የተማርነውንም እየያዝን ስንመጣ ጳውሎስ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትናለመታገ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን ያለው ሃሳብ በእኛም ይፈጸማል ለትምህርቱ ማጠናከርያ እንዲሆኑ እነዚህን ተጨማሪ ጥቅሶች አብረን እናጥናቸው 1 ተሰሎንቄ 5  21  2 ጢሞቴዎስ 3  13 _ 15  ቆላስያስ 1  22 _23  መዝሙር 119  10 _ 16 እግዚአብሔር የምናነበውን ቃል እንድናስተውለው ይርዳን  









ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment