Sunday 8 March 2020

የአህያዋና የተኩላው ክርክር (ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

የአህያዋና የተኩላው ክርክር
(ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ እና አህያ የሳር ቀለም እንዲህ ነው
እንዲያ ነው
በሚል ክርክር ውስጥ ገቡ።

አህያ ፡- “ የሳር ቀለም ቢጫማ ነው ” አለ።
ተኩላ ፡- “ በፍፁም ! አረንጓዴ ነው ” አለ።

ክርክራቸው እየጦፈ መጣ። ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ላይ
መድረስ
አልቻሉም።
በመጫረሻም የጫካ ንጉስ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው
መሸማገል
እንዳለባቸው ወሰኑ።

ሽምግልናው ተጀመረ።

ሁለቱም የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቀረቡ። አንበሳም
የሁለቱን የመከራከያ
ነጥብ በጥሞና አዳመጠ። የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል
የታደሙት እንስሳቶች
በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን ጣል አደረጉ።
አንበሳው ታዳሚውንም
ሆነ ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ።
ተኩላው በአንድ ወር
እስራት እንዲቀጣ ሲወሰንበት አህያው ደግሞ በነፃ ተሰናበተ።

በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በሚል ስሞታ
አቀረበ ፡-

“ ክቡር አንበሳ ሆይ ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን ? ”
አንበሳም “ አዎ በርግጥ አረንጓዴ ነው ” በማለት መለሰ።

ተኩላውም “ ታዲያ በየትኛው ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያክል
ዘብጥያ
እንድወርድ የወሰንክብኝ ” በማለት ጠየቀ።

አንበሳውም “ ትክክል ነህ ፤ በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት
አላስተዋልኩም።
ጥፋትህ ይህን መሰል በሆነ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር
ውስጥ መግባትህ
ነው። ነገሮችን በጥልቀት መረዳትና መገንዘብ ከማይችል
አካል ጋር መከራከር
ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዘን አንደሚችል ትምህርት ትቀስም
ዘንድ ብየ ነው
የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ ” አለው።

No comments:

Post a Comment