Sunday 15 March 2020

የመልዕክት ርዕስ ፦ እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ ( የሉቃስ ወንጌል 4 ፥ 16 - 30 ) ክፍል አንድለወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የተላለፈ መልዕክት የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ከዚህ በመቀጠል ጌታ በልቤ ላይ ባስቀመጠው ቃል ዛሬ ወደ እናንተ ብቅ ብያለሁ :: ምንም እንኩዋ የቤተክርስቲያኖቻችሁ አባላት ባንሆንም ለአካሉ ሥራ ግን እናንተን ብቻ ሳይሆን ሳይለየን እኛንም ጭምር የጠራን በመሆኑ የአካሉ ሥራ ግድ ይለናልና ይህንን መልዕክት በመስማት ከስሕተቶቻችሁ እንድትመለሱ መልእክቴን ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ :: መልዕክቱ በሁለት ተከታታይነት ባለው የቪዲዮ ዝግጅት የቀረበ ነው :: ጊዜ ሰጥታችሁ ብትሰሙት ብዙ ትጠቀማላችሁ :: ባትሰሙት ደግሞ የሚሰሙት ልጆች ጌታ ስላሉት መልዕክቱን በሰሙት ሰዎች ጌታ ይጠቀማል:: መልዕክቱ የሚመለከተው በእግዚአብሔር ሥራ ላይ እንቅፋት ለሚያኖሩ ፣ እነርሱ ካልሰሩ በስተቀር የእግዚአብሔር ሥራ የተሠራ ለማይመስላቸው ፣ ሰውን በመጽሐፉ ቃል ሳይሆን በራሳቸው ማለትም በፖዚሺናቸውና በዕድሜ ቆይታቸው ሊመዝኑ ለሚፈልጉ ፣ እየወጡና እያደጉ ያሉትን አገልጋዮች ለሚያናንቁና ለሚያንኩዋስሱ ፣ ልባቸውንም ለመስበር የሚፈልጉትን ትምክህተኛ ፓስተሮችንና የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ነው :: ወደ መልዕክቱ እንለፍ ጌታ ዘመናችንን ይባርከው አባ ዮናስ ጌታነህ ሐዋርያዊ አገልጋይ

No comments:

Post a Comment