Sunday 15 March 2020

የመልዕክት ርዕስ ፦ እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ ( የሉቃስ ወንጌል 4 ፥ 16 - 30 ) ክፍል አንድለወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የተላለፈ መልዕክት የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ከዚህ በመቀጠል ጌታ በልቤ ላይ ባስቀመጠው ቃል ዛሬ ወደ እናንተ ብቅ ብያለሁ :: ምንም እንኩዋ የቤተክርስቲያኖቻችሁ አባላት ባንሆንም ለአካሉ ሥራ ግን እናንተን ብቻ ሳይሆን ሳይለየን እኛንም ጭምር የጠራን በመሆኑ የአካሉ ሥራ ግድ ይለናልና ይህንን መልዕክት በመስማት ከስሕተቶቻችሁ እንድትመለሱ መልእክቴን ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ :: መልዕክቱ በሁለት ተከታታይነት ባለው የቪዲዮ ዝግጅት የቀረበ ነው :: ጊዜ ሰጥታችሁ ብትሰሙት ብዙ ትጠቀማላችሁ :: ባትሰሙት ደግሞ የሚሰሙት ልጆች ጌታ ስላሉት መልዕክቱን በሰሙት ሰዎች ጌታ ይጠቀማል:: መልዕክቱ የሚመለከተው በእግዚአብሔር ሥራ ላይ እንቅፋት ለሚያኖሩ ፣ እነርሱ ካልሰሩ በስተቀር የእግዚአብሔር ሥራ የተሠራ ለማይመስላቸው ፣ ሰውን በመጽሐፉ ቃል ሳይሆን በራሳቸው ማለትም በፖዚሺናቸውና በዕድሜ ቆይታቸው ሊመዝኑ ለሚፈልጉ ፣ እየወጡና እያደጉ ያሉትን አገልጋዮች ለሚያናንቁና ለሚያንኩዋስሱ ፣ ልባቸውንም ለመስበር የሚፈልጉትን ትምክህተኛ ፓስተሮችንና የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ነው :: ወደ መልዕክቱ እንለፍ ጌታ ዘመናችንን ይባርከው አባ ዮናስ ጌታነህ ሐዋርያዊ አገልጋይ

Sunday 8 March 2020

ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የድንግል ማርያም ሥዕል



Image result for ስንክሳር
ኢዮብ በፈሳሽ ውሃ ታጥቦ ከደወአው ተፈወሰ



ስንክሳር * Sinksar - (Lives of Saints)
የዚህች ቅድስት ሐናን ክብርዋን መናገር የሚችል የለም


Image result for ስንክሳር

የስንክሳር አስማት ጥንተ አብሶ የአዳም በደል መተላለፍ የቀረው በማህጸነ ሐና ውስጥ ነውና ለዚህ አንክሮ ይገባል



Image result for ስንክሳር

መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁማርያም አምላክ ናት ፣ ገብርኤል አምላክ ነው ሲሉ ለተናገሩት መታረምን ጠልተው የተዛለ...

የአህያዋና የተኩላው ክርክር (ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

የአህያዋና የተኩላው ክርክር
(ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ እና አህያ የሳር ቀለም እንዲህ ነው
እንዲያ ነው
በሚል ክርክር ውስጥ ገቡ።

አህያ ፡- “ የሳር ቀለም ቢጫማ ነው ” አለ።
ተኩላ ፡- “ በፍፁም ! አረንጓዴ ነው ” አለ።

ክርክራቸው እየጦፈ መጣ። ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ላይ
መድረስ
አልቻሉም።
በመጫረሻም የጫካ ንጉስ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው
መሸማገል
እንዳለባቸው ወሰኑ።

ሽምግልናው ተጀመረ።

ሁለቱም የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቀረቡ። አንበሳም
የሁለቱን የመከራከያ
ነጥብ በጥሞና አዳመጠ። የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል
የታደሙት እንስሳቶች
በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን ጣል አደረጉ።
አንበሳው ታዳሚውንም
ሆነ ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ።
ተኩላው በአንድ ወር
እስራት እንዲቀጣ ሲወሰንበት አህያው ደግሞ በነፃ ተሰናበተ።

በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በሚል ስሞታ
አቀረበ ፡-

“ ክቡር አንበሳ ሆይ ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን ? ”
አንበሳም “ አዎ በርግጥ አረንጓዴ ነው ” በማለት መለሰ።

ተኩላውም “ ታዲያ በየትኛው ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያክል
ዘብጥያ
እንድወርድ የወሰንክብኝ ” በማለት ጠየቀ።

አንበሳውም “ ትክክል ነህ ፤ በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት
አላስተዋልኩም።
ጥፋትህ ይህን መሰል በሆነ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር
ውስጥ መግባትህ
ነው። ነገሮችን በጥልቀት መረዳትና መገንዘብ ከማይችል
አካል ጋር መከራከር
ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዘን አንደሚችል ትምህርት ትቀስም
ዘንድ ብየ ነው
የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ ” አለው።

እንዲህ ቢሆንስ ?






ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤



ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሃይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡” ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
ታግሶ ለኖረ ጊዜ መልስ ይሰጣል


Saturday 7 March 2020

አስማት ያለበት ድርሳነ ሚካኤል ( የቅዱስ ሚካኤል ድርሳን )



Image result for አስማት ያለበት ድርሳነ ዑራኤል

ድርሳነ ሚካኤል አስማትና መተት
እየሱስ በሚካኤል ክንፍ ላይ የአስማት ስሞችን ፃፈ!
ይህን ድርሳን የፃፈው የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባደማቲዎስ ነው በመፅሐፉም ውስጥ በመላኩ ገብርኤል ስም ጥንቆላና አስማት ተፅፏል ፃፈው የተባለው ደግሞ ኢየሱስ ነው ትርጉማቸው ምን እንደሆነ የማይታወቁ ቃላቶች የከበሩ እያለ ይጠራቸዋል ግማሾችን ደግሞ የእግዚአብሔር ኀቡዕ ስሞች ሲሆኑ ከገብርኤል እጅ የተገኙ ናቸው ይላቸዋል
ለነብያት ያልተገለፁ ስሞች ለአባ ደማቲዎሥ ተገልፀው ይሆን?
ድርሳነ ሚካኤል ዘኀዳር
ገፅ 39 እና 44
92 በትሕትና ቃልም እነዚህን የከበሩ ቃላትን ተናገር " አካዕ አሜዕ ሌክ ቦኤ ኤንካ ካዚን አርያኪን ኤርናኬ ኬም ካዮን ፔጉ ጌሎ አስኤሌቅ አስሎ አስከማ አላሶሙ ኤቅሬው ያበስትክ ፒስኪር ጋርጎ አቢት ከቢስ ፌይኦ ፌኤ አንልካ ኢዊስ አብሶላ ኪፍ ካዕዊኑ አርህሉ አዋፅ አዊካ እሎ አሴሎ ዮብጎ ኤል አክዕዊ አስ ከመዕ ወዲናኬጓ ።
112 አካ ክስብኤል ቤቃ ጼቃ ሴቃ አልፍ ወዖ ቤጣ የውጣ ዮድ አኸያ ሸራኽያ አልመክኑ እነዚህ አስማቶች #እየሱስ #ክርስቶስ #በቅዱስ #ሚካኤል #በክንፎቹ #ላይ #የጻፈለት #ናቸው
Image result for አስማት ያለበት ድርሳነ ዑራኤል
113 #በነዚህ #አስማቶች ዲያብሎስ ከነሰራዊቱ በጨለማ መጋረጃ ተጠቅልሎ እንደወደቀ የኔንም ጠላቶቸንና ባላጋራዎችን ለዘላለሙ ጣልልኝ
እነዚህ ትርጉም የለላቸው ቃላቶች ምንድን ናቸው የገባው ያስረዳን እየሱስስ እውነት አስማትን ይሰራ ነበር?




ሔኖክ ዘአዶናይ – ድርሳነ ዑራኤል (ዘጥቅምት ምዕራፍ ሁለት ..አስማት ያለበት ድርሳነ ዑራኤል


ድርሳነ ዑራኤል (ዘጥቅምት ምዕራፍ ሁለት)
"አመድ በዘነመ በአምሳ ሰባት ዓመት የአረማውያን ጠላታቸው የሆነ ይነግሣል።አመድ ከዘነመ በኃላ የአረማውያን ነገሥታት አምላካችን የሰጣቸው ሰብዓ ሰባት ዘመን ካለቅ በኃላ ኃይልና ግዛት የላቸውም።ዳግመኛም መጋቢት ፱ ቀን ጥቂትች የከዋክብት ምልክቶች ይታያሉ።አመዳይ ወይም ውርጭ በዘነመ በሰብዓ ዓመት በኀዳር ፯ ቀን በእራሱ ላይ ሦስት የመስቀል ምልክት ያለው አንድ ኮከብ ይታያል።ከዚህ በኃላ የአረማውያን ዘመን ያልቅና የስሙ ምልክት #ና ተብሎ ከተመለከተው ንጉሥ የተወለዱ የኢትዮጵያ ነገሥታት ያሸንፏቸዋል።...."
#ሔኖክ #ሄ
No photo description available.