Thursday 17 January 2019

የአረጋዊው አባት የአቶ ተፈራ የክፍል ሁለት ምስክርነት የአረጋዊው አባት የአቶ ተፈራ የክፍል ሁለት ምስክርነት ስላነበቡትና ስለመረመሩት መጻሕፍት በውስጡም ስላገኙት ጥቅም አጫውተውናል አሁን ላይ ያለ ትውልድም ጭፍን ተቃውሞን አስወግዶ መጻሕፍትን በማንበብ ለዘላለም ሕይወት የሆነውን እውነትና እውቀት እንዲያገኝ በጽኑ መክረዋል በወንጌል ሥራ ያሳለፉአቸውን ጊዜያት ፣ ይህንን ወንጌል ከነማን ጋር እንዳገለገሉ ፣ የት እንዳገለገሉና በአገልግሎታቸውም የመጣውን ለውጥ ም ነግረውናል እኚህ አባት አሁንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በፓልቶክ ፣ ባሉበት አጥቢያ ቤተክርስቲያንም ይሁን በተጋበዙበት ቦታ ሁሉ በማገልገል እና አባታዊ ምክራቸውንም በመስጠት ላይ ይገኛሉ ዕድሜና ዘመን ለአባታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጨመርላቸው እላለሁ ደግሞም እጸልይላቸዋለሁ እናንተም ጸልዩላቸው የተሃድሶን አገልግሎት አስመልክቶ በእርሳቸው በኩል ቤተክርስቲያንዋ መታደስ አለባት ሲሉ የያዙትን አቋምና የአገልግሎቱም ሂደት ሁኔታ ምን መምሰል እንዳለበት ከቆይታቸውና ከልምዳቸው ተነስተው የገባቸውን ያህል አጫውተውናል አባታዊ ምክርም ሰጥተውናል ቤተክርስቲያናችን ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃል እንድትመለስና ኢየሱስን ጌታዋና አዳኝዋ አድርጋ በመቀበል እንድትሠብክ ፍንጭ የሚሰጡ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመጻሕፍቶችዋ ተጽፈውና ሰፍረው ያሉትን ሃሳቦች ነበር በጥቂቱ ያነሳነው ለምሳሌ ነፍስ አባትነትን በተመለከተ ፣ ሊቀካህናትነትንም ሆነ አማላጅነትን በተመለከተ ፣ አዳኙም ነፍስ አባቱም አማላጁም ሆነ ሊቀካህናቱ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን የሚገልጹ ከመጽሐፍቅዱሱ ሌላ በቤተክርስቲያኒቱ ያሉ መጻሕፍትም ስላሉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ወደ መሠረትዋ ተመልሳና ተረቶችዋን ጥላ ብቸኛ አዳኛችንና አማላጃችን የሆነውን ኢየሱስን ብቻ ልትሠብክ ጊዜው አሁን ነው እንላለን ዘመኑ የጥልና የክርክር ሳይሆን የወንጌል ዘመን ስለሆነ ሁላችንም ለመከሩ ሥራ እንነሳ ወንጌሉንም ተነስተን እንስበክ የሚለውን መልዕክት ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ ተባረኩልኝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment