Tuesday 29 January 2019

የመልዕክት ርዕስ : - ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አበጀ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18 : 30 - 46የመልዕክት ርዕስ : - ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አበጀ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 18 : 30 - 46 የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ተባረኩ መልዕክቱ በቪዲዮ ተለቆአል ተከታተሉ በዚህ መልዕክት ውስጥ ግን አስተውለን እንድንረዳው የምፈልገው ጥያቄያችን ፈርሶ የነበረውን መሠዊያ ማበጀት ከሆነ ጊዜ ሊቆይ ይችል ይሆናል እንጂ ማበጀታችን አይቀርም ለእኔ ኤልያስ የፈረሰ መሠውያ ማበጀቱ አይደለም የሚደንቀኝ መሠውያው ከዚህ በፊት በሥራ ላይ እንደነበረና አሁን ደግሞ እንደፈረሰ ማወቁና ለማበጀት መነሳቱ ነው የገረመኝ ስለዚህ ኤልያስ ዝም ብሎ መሠውያ ሊሰራ የተነሳና መሠውያውንም የሰራ አይደለም ከዚህ ጋር በተዛማጅነት ነህምያ 2 : 9 - ፍጻሜ የተጻፈውን እንመልከት ውድ ወገኖቼ ሆይ ብዙ ሰዎች በዚህ ዘመን መሠውያ ብቻ አይደለም ብዙ ነገር ሊሰሩ ተነስተውና ሊደመድሙ አቅቶአቸው አይተናል የሉቃስ ወንጌል 14 : 25 - 33 እንመልከት እንደገናም ብዙ ሰዎች እሄዳለሁ ካለ ጋር ሁሉ ሄደው ሆ ካለ ጋርም ሆ ብለው ተነስተው ጨለማና ጥፋት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሳይቀር የገቡ ብዙዎች ናቸው የዮሐንስ ወንጌል 21 : 1 - 14 ይመልከቱ ታድያ መጽሐፍ ቅዱሳችን የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል እንደሚል በእኛ የተጀመሩ ሥራዎች በእኛው እንዲፈጸሙ በእኛም የጀመረው እግዚአብሔር ጊዜውን ጠብቆ በእኛው ሥራውን እንዲፈጽም እኛም ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ተስማምተን መውጣትና እግዚአብሔርም አድርጉ ያለንን ብቻ ማድረግ እንዳለብን ይሄ መልዕክት በጽኑእ ያስታውሰናል ይመክረናል ( ዘካርያስ 4 : 6 - 10 / ፊልጵስዩስ 1 : 6 / የሉቃስ ወንጌል 17 : 10 ) የተጻፈውን እንመልከት እግዚአብሔር በዚህ የቃል እውነት ይገናኘን ይባርከን ተባረኩ አባ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 17 January 2019

የአረጋዊው አባት የአቶ ተፈራ የክፍል ሁለት ምስክርነት የአረጋዊው አባት የአቶ ተፈራ የክፍል ሁለት ምስክርነት ስላነበቡትና ስለመረመሩት መጻሕፍት በውስጡም ስላገኙት ጥቅም አጫውተውናል አሁን ላይ ያለ ትውልድም ጭፍን ተቃውሞን አስወግዶ መጻሕፍትን በማንበብ ለዘላለም ሕይወት የሆነውን እውነትና እውቀት እንዲያገኝ በጽኑ መክረዋል በወንጌል ሥራ ያሳለፉአቸውን ጊዜያት ፣ ይህንን ወንጌል ከነማን ጋር እንዳገለገሉ ፣ የት እንዳገለገሉና በአገልግሎታቸውም የመጣውን ለውጥ ም ነግረውናል እኚህ አባት አሁንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በፓልቶክ ፣ ባሉበት አጥቢያ ቤተክርስቲያንም ይሁን በተጋበዙበት ቦታ ሁሉ በማገልገል እና አባታዊ ምክራቸውንም በመስጠት ላይ ይገኛሉ ዕድሜና ዘመን ለአባታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጨመርላቸው እላለሁ ደግሞም እጸልይላቸዋለሁ እናንተም ጸልዩላቸው የተሃድሶን አገልግሎት አስመልክቶ በእርሳቸው በኩል ቤተክርስቲያንዋ መታደስ አለባት ሲሉ የያዙትን አቋምና የአገልግሎቱም ሂደት ሁኔታ ምን መምሰል እንዳለበት ከቆይታቸውና ከልምዳቸው ተነስተው የገባቸውን ያህል አጫውተውናል አባታዊ ምክርም ሰጥተውናል ቤተክርስቲያናችን ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃል እንድትመለስና ኢየሱስን ጌታዋና አዳኝዋ አድርጋ በመቀበል እንድትሠብክ ፍንጭ የሚሰጡ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመጻሕፍቶችዋ ተጽፈውና ሰፍረው ያሉትን ሃሳቦች ነበር በጥቂቱ ያነሳነው ለምሳሌ ነፍስ አባትነትን በተመለከተ ፣ ሊቀካህናትነትንም ሆነ አማላጅነትን በተመለከተ ፣ አዳኙም ነፍስ አባቱም አማላጁም ሆነ ሊቀካህናቱ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን የሚገልጹ ከመጽሐፍቅዱሱ ሌላ በቤተክርስቲያኒቱ ያሉ መጻሕፍትም ስላሉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ወደ መሠረትዋ ተመልሳና ተረቶችዋን ጥላ ብቸኛ አዳኛችንና አማላጃችን የሆነውን ኢየሱስን ብቻ ልትሠብክ ጊዜው አሁን ነው እንላለን ዘመኑ የጥልና የክርክር ሳይሆን የወንጌል ዘመን ስለሆነ ሁላችንም ለመከሩ ሥራ እንነሳ ወንጌሉንም ተነስተን እንስበክ የሚለውን መልዕክት ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ ተባረኩልኝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ

Monday 14 January 2019

የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን የክፍል ሦስት ትምህርት የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን የክፍል ሦስት ትምህርት የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን :: የኢየሱስ ደቀመዝሙር መሆን በሚለው የክፍል ሦስት ትምህርቱ መምህር ጌታቸው እንደ መግቢያና የትምህርቱም መንደርደርያ አድርጎ በማቅረብ ኢየሱስ ራሱ ሕይወቱ የሚጠና ሳብጀክት ነው በማለት ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁትም በእርግጥ ሰምታችሁታልና እውነትም በኢየሱስ እንዳለ ተምራችኋል በሚል ለኤፌሶን ክርስቲያኖች የተጠቀሰውን ቃል በመጥቀስ ክርስቶስን በትክክል እየተማርንና እያጣጣምን በፍቅር ተባብረን በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ የመረዳት ባለጸግነት እንድንደርስ የእግዚአብሔርንም ምስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንድናውቅ መጋደል እንደሚገባን አስታውሶናል :: ከዚህም ሌላ ይህንኑ አስመልክቶ ረቢ ወዴት ትኖራለህ ? ብለው ለጠየቁ ደቀመዛሙርት የሚኖርበትን መጥታችሁ እዩ በማለት መጥተው እንዲያዩ የተጋበዙ ደቀመዛሙርት ከእርሱ ጋር በመዋላቸው ያተረፉትን ነገር በመግለጽ ከጌታ ጋር በመዋል የሚያስገኘውን ጠቀሜታ ትልቅ ግንዛቤ በመስጠት እውነትን እንድንጨብጥ አድርጎናል :: ከዚህም ባሻገር ዛሬ ወዳዘጋጀልን የትምህርት ሃሳብ በመግባት እና በማብራራት ደግሞ ፣ እውነተኛ የጌታ ደቀመዝሙር ለመሆን ከራስ ባርነት ነጻ መውጣት ያስፈልጋል በማለት የዮሐንስ መጥምቁን የሕይወት ባግራውንድና አገልግሎቱንም ጭምር በመጥቀስ ፣ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ከራሱ ባርነት የተላቀቀ በመሆኑ ለኢየሱስና ለኢየሱስ ብቻ የኖረበትን ወርቃማ የቅድስና ሕይወት ከጥሩ ትንታኔ ጋር እንደሚገባ አብራርቶ አስተምሮናል :: ውድ ወገኖቼ ሆይ መምህር ጌታቸው ባስተማረን መሠረት እንግዲህ በሕይወታችን ለሌሎች መኖርን የከለከለን በእኛነታችን ውስጥ ያለና ሳናውቀው እኛነታችንን አስሮ የያዘን ፣ ለራሳችንም ብቻ ባርያ ያደረገን ነገር ነው :: እርሱም ስም ፣ ገንዘብ ፣ መልክ ፣ እውቀት ፣ ዝና የመሣሠሉት እና በሕይወታችንም በቅለው አልነቀል ያሉን ነገሮች ናቸው :: እንደ ጳውሎስ የወንጌሉ እውነት ገብቶን ለእኔ ረብ የሆነውን እንደ ጉድፍ እቆጥራለሁ ብለን እስካልተውነው ድረስ የእኛን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ሰዎች ሕይወት ጨምድደው የሚይዙ ትልቅ በሽታዎች እንደሆኑ መምህር ጌታቸው አጠንክሮ ነግሮናል :: ስለዚህ የምንለው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ይፈውሰን ነው :: ወገኖቼ እንግዲህ ይህንን አስደናቂ ትምህርት ከሰማንበት ጊዜ ጀምሮ ለሌሎች መኖርን መለማመድ ፣ የውድድር ሕይወትን ማቆም ፣ ሌሎችን ሪስፔክት እያደረጉ ማገልገልም ሆነ መገልገል ከዚህም ሌላ የደቀመዝሙር ሕይወት ለበላይ አካል መታዘዝ ብቻ ሳይሆን ለበታቾቻችንም ሳይቀር የመታዘዝ ሕይወት ስለሆነ በመታዘዝ ሕይወት ለመኖር ራስን መስጠት ፣ ሰልፊሽ ወይም ስግብግብ ከሆነ ሕይወት ለመላቀቅ መሞከር ፣ ሌላው ቀርቶ በተሰማራንበት በማንኛውም የሥራ ገበታ ጉልበታችንንም ሆነ እውቀታችንን አሟጠን መስራት እንጂ ለደሞዝና በደሞዛችን ልክ ብቻ ለመስራት መሞከር በራሱ የደቀመዝሙርነት ሕይወት አለመሆኑን በማስገንዘብ መምህር ጌታቸው አሁንም ከዚህ ቃል ጋር አያይዞ እንዲህ ሲል አስደናቂ ቃል ነገረን በዚሁም ቃል ወንድምህ አንድ ምዕራፍ እንድትሄድ ቢጠይቅህ ሁለተኛውን ሂድለት በማለት ታዛዥነታችን ፍጹምና ምሉዕ ማድረግ እንዳለብንም ከብዙ ማስተዋል ጋራ መከረን ጌታ ዘመኑን ይባርከው :: ወንድማችን መምህር ጌታቸውን ስላስተማርከን ትምህርት አሁንም ጸጋው በእጥፍ ይብዛልህ ልለው እፈልጋለሁ :: ተከታዩ የክፍል አራት ትምህርት ሰኞ ይቀጥላል ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ጸልዩ:: ሰዎችንም መጋበዝ አትርሱ :: ትምህርቶቹም በፌስቡክ ብቻ ሳይሆን በዩቲዩብም ጭምር ስለሚለቀቁ እየገባችሁ መከታተል ትችላላችሁ :: ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ :: ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Saturday 12 January 2019

አስደናቂ የሆነውና ወደ ጌታም ማዳን የመጡበት የመሪጌቶች የሕይወት ምስክርነት ( ክፍል አንድ )አስደናቂ የሆነውና ወደ ጌታም ማዳን የመጡበት የመሪጌቶች የሕይወት ምስክርነት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን::ከዚህ በመቀጠል አስደናቂ የሆነውን የእነዚህን መሪጌቶች ወደጌታ ማዳን የመጡበትን የሕይወት ምስክርነት አቅርበናል :: ከዚያ በፊት ግን ፦————————————— 1ኛ ) የሕይወት ታሪካቸውን ፣ ከተማሩበት ትምህርት አንጻርም ያላቸው ሞያ ምን እንደሚመስል በዝርዝር አቅርበውልናል :: ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት አዋቂና ባለሞያ ነን ሊሉ ሞያቸውንም ሊያሳዩ ፈልገው ሳይሆን አንዳንድ ሰነፍ ኦርቶዶክሳውያን የወንጌልን እውነት ላለመስማት ሲሉ ጆሮዎቻቸውንም በመድፈን በምትኩ የእነዚህን በወንጌል እውነት የተዋጁ መሪጌቶች ፣ የእኛ መሪጌቶች አይደሉም ፣ ሻሹንም ከመርካቶ ገዝተው የጠመጠሙ ናቸው በማለት ስም እያጠፉ ስላሉ እነዚህ መሪጌቶች በዚህ የምርግትና ትምህርት ውስጥ ለዓመታት ዋጋ ከፍለውና በብዙ እንግልት ተምረው አልፈው የሞያው ባለቤት መሆናቸውን ለመጠቆም ሲባል ሞያውንና ይትበሃሉን ከነዜማው ከነአቋቋሙና ከነቅኔው በትክክል ሊያስደምጡን ችለዋል :: 2ኛ ) እንደገናም የክርስቶስ ሕይወት እንዴት እንደበራላቸውና እንዴት ወደ ጌታ ማዳን እንደመጡ መስክረውልናል :: በዚህም ውስጥ ከነገረ ድኅነት አንጻር የተሃድሶ እንቅስቃሴ እንዴት እንደሆነና ምን እንደሚመስል ፣ ቤተክርስቲያኒቱም መሠረታዊውን የእግዚአብሔር ቃል እውነት የለቀቀችና ከእውነትም ቃል የወጣች በመሆንዋ ወደ ትክክለኛ መሠረትዋ መመለስ እንዳለባት የሚጠቁሙ እውነቶችን በመናገር መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል ተሃድሶ ማድረግ እንዳለባት በጽኑ ተናግረዋል ፣ አስረድተውማል :: 3ኛ ) አዋልድ መጻሕፍት በመጽሐፍቅዱሱ ቃል ሲመዘን የሚል ዲቪዲ ከቁጥር አንድ እስከ አራት የሠሩ ሲሆን ፣ አዋልድ መጽሐፍ ምን እንደሆነና የመጽሐፍቅዱሱ ቃል ደግሞ ምን እንድሚመስል ትርጉሙንና ዝርዝር ሃሳቡን ጭምር በአጭሩ አቅርበዋል :: በቀጣዩ ክፍለ ጊዜያቸው ደግሞ በውስጡ ያለውን ሃሳብ ከመጽሐፍቅዱሱ ቃል ጋራ ምን ያህል የሚጋጭ መሆኑን ሊያሳዩን ይሞክራሉ :: ስለዚህ ቅዱሳን ወገኖች ለእነዚህ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር ባሮች ወደፊት ባለ ዘመናቸው ፣ ከፊት ለፊታቸው ብዙ ነገር የሚጠብቃቸው ሰዎች ስለሆኑ በጽናት ቆመው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲሰሩና አገልግሎታቸውንም እንዲፈጽሙ በትጋት ልንጸልይላቸው ልናበረታታቸውም ይገባል እላለሁ:: በክፍል ሁለት መልዕክታቸውና ትምህርታቸው እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑ የምላችሁ አባ ዮናስ ጌታነህ የስምዓ ጽድቅ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ተሃድሶ መሥራችና መሪ ተባረኩ