Tuesday 7 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 2 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) 2ኛ ) ፋሲካ መታረድ ያለበት ነው ( ዘጸአት 12 ፥ 21 ) በመሆኑም ታድያ ድንግል ማርያም የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲ በተናገረው ቃል መሠረት በግዕዙ ቃል ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ብሎአልና ወደ አማርኛው ሲተረጎም የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ የሚል በመሆኑ ከተጻፈልን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር ስናነጻጽረው የኢየሱስ እናት ማርያም የእስራኤል ጠቦት ሆና ጠቦት የሆነችዋን ማርያምን ምረጡ ወስዳችሁም ለፋሲካ እረዱዋት በማለት የብሉይ ኪዳንም ሆነ የሐዲስኪዳን ፋሲካችሁ እናታችሁ ማርያም ናት አላለንም በመሆኑም ለአዳምና ለሔዋንም ሆነ ለሰው ልጆች ሁሉ ለራስዋ ለማርያምም ጭምር ፋሲካዋ ሆኖ በሸላቾቹ ፊት ሳይቀር ዝም እንደሚል በግ የታረደልን ጠቦታችን የሆነው የናዝሬቱ ኢየሱስ ብቻ ነው ከዚህ በመቀጠል ለትምህርታችን እንደ መንደርደርያ የሆኑትን ዋና ዋና ነጥቦች ፣ ለአማናዊው በግ ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደጥላ ሆነው ያገለገሉትን ፣ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ የቀረቡትን መሥዋዕቶች ከመሥዋዕታችን ከኢየሱስ ጋር በንጽጽር እያቀረብን ደረጃ በደረጃ እናያቸዋለን ሀ ) የሚታረደው ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ሲሆን ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ ይለናል ( ዘጸአት 12 ፥ 5 ፣ ዘሌዋውያን 4 ፥ 32 ) ለ ) ይህ ነውር የሌለበት ጠቦት ደግሞ በሐዲስኪዳን በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም የተዋጀንበት እውነት ነው ( 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 18 _ 19 ) ሐ ) ለቁርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በእግዚአብሔር ፉት ያቀርበዋል ይለናል ( ኦሪት ዘሌዋውያን 3 ፥ 7 ) መ ) ይህም በሐዲስ ኪዳን ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመጸኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት የሞተልን እርሱ ክርስቶስ ነው ( 1ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 18 _ 22 ) ሠ) በብሉይ ኪዳን ዘመን የቀረበው ይህ አንዱ ጠቦት ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት ተለውሶ የኢፍ መስፈርያ አስረኛ እጅ መልካም ዱቄት ጋር ለመጠጥ ቁርባን ይሆናል ይህንን ነው እንግዲህ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽቱ እንዲሆን የእሳት ቁርባን ይሆናል የሚለን ( ዘጸአት 20 ፥ 40 እና 41 ፤ ዘኊልቊ 28 ፥ 8 ) ረ ) ይህንን እውነታ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስናመጣው ክርስቶስ ለእግዚአብሔር የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ስለ እያንዳንዳችን ራሱን አሳልፎ የሰጠበትን ሕይወት እናይበታለን ( ኤፌሶን 5 ፥ 1 _ 3 ፤ ፊልጵስዩስ 4 ፥ 18 ) ሰ ) ይሄ የታረደው ጠቦት ስቡ ሁሉ ሳይቀር የሚቀርብ ስለሆነ ለደኅንነት መሥዋዕት የሚቀርብና ካህኑም ለእግዚአብሔር በእሳት በተቃጠለው ቁርባን በመሰውያው ላይ የሚያቃጥለው ፣ ካህኑም ስለተሠራው ኃጢአት የሚያስተሠርየውና እርሱም አብሮ ይቅር የሚባልበት ነው ( ዘሌዋውያን 4 ፥ 35 ፣ ዘሌዋውያን 4 ፥ 26 ) ሸ ) ይኸው ጠቦት አውራ ፍየልም ይሁን አውራ በግና በሬ በዘይት ከተለወሰው የእህል ቁርባን ጋር ለኃጢአት መሥዋዕት ሊሆን በእግዚአብሔር ፊት ይሰዋ ዘንድ የሚቀርብ ነው ( ዘሌዋውያን 9 ፥ 3 _ 4 ) ቀ ) ይሁን እንጂ እነዚህ በብሉይ ኪዳን ዘመን የቀረቡ የጥጆች የፍየሎችና የኮርማዎች ደም በረከሱት ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ብቻ ናቸው ነገር ግን ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ከዚህ ከብሉይ ኪዳኑ መስዋዕቶች ይልቅ በተለየ ሁኔታ ሕያው እግዚአብሔርን ልናመልክ ከሞተ ሥራ ሕሊናችንን ነጻ የሚያደርግ ነው ( ዕብራውያን 9 ፥ 13 እና 14 ) በ ) እንደገናም ሊቀካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መስዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪያደርግ ድረስ ወደፊት ይጠብቃል አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋል ይለናል ( ዕብራውያን 10 ፥ 11 _ 18 ) ተ ) ከዚህም ሌላ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለተጠራ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው ይለናል ( ዕብራውያን 7 ፥ 7 _ 10 ) ቸ ) ተጨነቀ ተሰቃየ አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም በማለት የሐዲስ ኪዳኑ ጠቦታችን የታረደው በግ የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደሆነ ይናገራል ( ኢሳይያስ 53 ፥ 7 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 29 ፤ የሐዋርያት ሥራ 8 ፥ 32 ) ጌታ እግዚአብሔር የምናነበውን ይህንን ጽሑፍም ሆነ የተለቀቀውን ቪዲዮ በማስተዋል ሰምተን እንድንጠቀም ይርዳን ተባረኩ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

No comments:

Post a Comment