Friday 10 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 3 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) 3ኛ ) ፋሲካ መታረድ ያለበት ነው ( ዘጸአት 12 ፥ 21 ) የተወደዳችሁ ወገኖች በዚህ የቊጥር 3 ትምህርት ፋሲካ መታረድ ያለበት በዓል እንደሆነና ፋሲካ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የቂጣ በዓልን ጨምሮ ሰባት ቀን ሙሉ የሚቆየውን በዓል እንደሆነ ፣ ብዛት ያላቸው የፋሲካ ማዕዶችም በዚህ ወቅት እንደሚቀርቡ ትምህርቱ ይጠቁማል :: በብሉይ ኪዳኑ ዘመን ካህናቱ ፣ ሌዋውያኑም አንድ ሆነው ነጽተው ነበር :: ሁሉም ንጹሐን ነበሩ :: ለምርኮኞቹም ሁሉ ፣ ለወንድሞቻቸውም ፣ ለካህናቱ ለራሳቸውም ፋሲካውን አረዱ ይለናል ( መጽሐፈ ዕዝራ 6 ፥ 20 ) :: በመሆኑም ፋሲካ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ሁሉንም የሚመለከት ነው :: ፋሲካ የማይመለከተው ሰው ማንም የለም :: ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ወደ አማርኛው ስተረጉመው የአዳም ፋሲካው ማርያም ፣ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋንም መሻገርያዋ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ሲል የሰዓታት መጽሐፍ በመሳሳት የተናገረ ቢሆንም ፣ ፋሲካችን ግን ክርስቶስ ስለሆነ መጽሐፍቅዱሳችን በነገረን ቃል መሠረት ለማርያምም ጭምር የሚያስፈልግ ነው :: ታድያ በዕዝራ መጽሐፍ እና በሌሎችም በተጠቀሰው ቃል መሠረት በሐዲስ ኪዳን የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ከፋሲካ በፊት ከሀገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ ይለናል ( ዮሐንስ ወንጌል 11 ፥ 15 ) :: እንደገናም ደግሞ በዮሐንስ ወንጌል 18 ፥ 28 ላይ ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት ማለዳ ነበረ እነርሱም የፋሲካን በግ ይበሉ ዘንድ እንጂ እንዳይረክሱ ወደ ገዢው ግቢ አልገቡም ይለናል :: ታድያ እነዚህ ካህናት ፋሲካን በንጽሕና ያደረጉ መስለው ገዢው ከአሕዛብ ወገን በመሆኑና እነርሱም እሕዛብን የተጸየፉ ሆነው ከዚሁ ከፋሲካቸው የተነሳ ወደ ገዢው ግቢ ባለመግባታቸው ያልረከሱ ቢመስላቸውም ፣ በማርቆስ ወንጌል 15 ፥ 1 መሠረት ማለዳ ነበርና የካህናት አለቆች ለሠሩት ሥራ የሕግ ሽፋን ለመስጠት ሲሉ ለሁለተኛ ጊዜ በማለዳ የሸንጎ ስብሰባ አድርገዋል :: ኢየሱስንም አስረው በመውሰድ ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጥተውታል ስለዚህ የፋሲካን በግ ይበሉ ዘንድ እንጂ እንዳይረክሱ ወደ ገዢው ግቢ ያልገቡ ናቸው ስለተባሉ ብቻ የነጹ ናቸው ማለት አንችልም :: እነርሱ የረከሱት ገና መጀመርያ ላይ ሕጋቸውን ሽፋን አድርገው በደል የሌለበትንና ንጹሕ የሆነውን ጌታ ለሁለተኛ ጊዜ በማለዳ የሸንጎ ስብሰባቸው ላይ አሳልፈው ሊሰጡ በዶለቱ ጊዜ ነው :: በመሆንም ሕግንና በዓልን መደበቅያ ሽፋን አድርጎ ሲዶልት የነበረን ሰው የነጻ ነው ማለት ሌላውን ሳይሆን እራስን በራስ እንደማታለል የሚያስቆጥር ነገር ነው :: ዛሬም ታድያ ይህንን ሽፋን አሁን ላይ ወዳለች ቤተክርስቲያን ስናመጣው ፣ ይሄ ሁኔታ በተለይም በአብዛኛው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ያላዋቂ ሳይሆን የአዋቂ አጥፊነት አለና ይሄ ጉዳይ ምንም ሳይሸፈን ይፋ ሆኖ እየታየ ያለ ደግሞም በፍጥነት ሊስተካከል የሚገባው ጉልህ ስሕተት ሆኖ አግኝቼዋለሁ :: በቪዲዮው የትምህርት መልዕክቴ ላይ እንደዘረዘርኩትም ዛሬ ላይ ጥቅስን ፣ ኮንፍረንሶችንና ልዩ ልዩ ዓመታዊ የመነቃቅያ ፕሮግራሞቻችንን ሽፋን በማድረግ ከዚህ በተጨማሪም የጌታን እራትና ልዩ ልዩ የእርስ በእርስ መገባበዝንም ጨምሮ ያለው ፕሮግራማችን በአብዛኛው ልባዊ ያልሆነና እንዲሁ ሥርዓት በመፈጸም ብቻ ክርስቲያን የሚለውን ስም ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ሲባል የሚደረግ ለውጥ የሌለበት ፣ ማስመሰልም የታከለበት ውጫዊ እንቅስቃሴ መሆኑ ለሁሉም ሰው ግልጽ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው :: ከዚህ የተነሳ እንግዲህ በውጪ ባሉት ሰዎች ዘንድ ያለን ምስክርነት እየተበላሽ በመምጣቱ ምክንያት ፣ በአካባቢያችንና በዙርያችን ባሉት ሰዎች ዘንድ ሞገስን አላገኘንም :: ጌታም የሚድኑትን ነፍሳት በላያችን አልጨመረም :: ይህ እንግዲህ ትልቁና ዋነኛው የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት አማኞችና አገልጋዮች ችግር ነው :: ለዚህ አስከፊ ጉዳይ የሚባለው እንግዲህ ከዚህ ዓይነቱ ነቀፋ እግዚአብሔር ያውጣን ነው :: በዚህ ውስጥ ግን አሻግረን የታረደልንን በግ ስናይ የታረደው በግ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሥልጣን የጨበጠው በሞቱ ነው :: በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ኖሯቸው ወደ ምድር ሁሉ በተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ድል ነሺ ሆኖ የተገለጠ በመሆኑ እንደታረደ በግ ቆሞ የታየ ነው :: በዚህም ምክንያት መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ ይለናል ራዕይ 5 ፥ 6 _ 11 :: ከዚህም ሌላ በራዕይ 17 ፥ 14 ላይ ይኸው ጌታ ድል ነሺ እና አሸናፊ መሆኑን ሊያጠናክርልን ፣ እነዚህ በጉን ይወጋሉ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ እነርሱን ድል ይነሣል :: ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሳሉ ይለናል :: የምናነበውን ቃል እግዚአብሔር ይባርክልን ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

No comments:

Post a Comment