Thursday 30 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊጥር 1 ) የዛሬው አዲሱ ትምህርታችን በማስታወቅያው መሠረት አንድ ብሎ በክፍል ስድስት ተጀምሯል በውኑ ድንግል ወደ እኛ በአሁኑ ሰዓት መምጣት ትችላለችን ? 1ኛ ) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) በተባለው የጸሎት መጽሐፍ ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ሲሉ ረጅሙን ዜማ እያዜሙ ይጸልያሉ በፍልሰታ ጸምና በዓቢይ ጾም እንዲሁም በሌሎች አጽዋማት ሳይቀር ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ይህንኑ ጸሎት በዚህ የሰዓታት መጽሐፍ መሠረት ያደርሳሉ 2ኛ ) ህዝባዊ መዝሙርም ወጥቶለት ፣ ህዝባችንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም እያለ በመዘመር ድንግልን ይማጸናል ይህ ለምን ይሆን ? የተወደዳችሁ ወገኖቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው ትምህርታችን ንዒ ኃቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ በሚለው የሰዓታት መጽሐፍ ቃል መሠረት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህናት ፣ የሰንበት ተማሪዎችና ሕዝበ ምዕመናን ጭምር ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ ፣ ነይ ነይ እምዬ ማርያም በማለት በመዝሙርና በአምልኮ ማርያምን ሲማጸኑና ሲጠሩ እንሰማቸዋለን :: በዚህ ትምህርት ውስጥ ግን ነይ ነይ እየተባለች የተጠራችው ማርያም በሞት የተወሰነችና ሞትም የከለከላት በመሆንዋ ልትመጣ እንደማትችል ትምህርቱ መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት አብራርቷል :: ይሁን እንጂ ይህንን የቃሉን እውነት ካለመረዳት የተነሳ ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ወይንም ነይ ነይ እናቴ ማርያም እያሉ አሁንም የኦርቶዶክስ ካህናትም ሆነ ሕዝበ ምዕመናን በዚህችው በማርያም ፍቅር ከመያዛቸው የተነሳ ቢቀጥሉ ሳያውቁት ወደ መናፍስት ጠሪና ወደ ሙታን ሳቢ መንፈስ ውስጥ ገብተው የጠረፍዋ ንግሥት መጫወቻ ሊሆኑ እንደሚችሉ መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት ንጉሥ ሳኦል ሳይቀር ሕይወቱ የተጎዳው በመናፍሥት ጠሪዎች መሆኑን ትምህርቱ አሁንም ማከያ ሃሳብ ሰጥቶ በአጽንኦት ይናገራል 1ኛ ሳሙኤል 28 በሙሉ ፣ 1ኛ ዜና መዋዕል 10 ፥ 13 እና 14 ን ይመልከቱ :: የተወደዳችሁ ቅዱሳን የዚህ ክፍል ዋና ትምህርት እንግዲህ ድንግል ማርያምን ንዒ ኃቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ ወይንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ሲሉ በመጣራት የሚመጣውን አደጋ የጠቆመን ብቻ ሳይሆን የመፍትሔውንም ዓይነት ደረጃ በደረጃ ነግሮናል 1ኛ ) በትንቢተ ኢሳይያስ 8 ፥ 19 መሠረት ከየትኛውም አቅጣጫ ጠይቁ የሚባል ነገር ሲመጣ ፣ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር መጠየቅ አለበት:: 2ኛ ) ወደ ሕጉና ወደ ምሥክሩ መሄድ አለበት ( ትንቢተ ኢሳይያስ 8 : 20 - 22 ) ወደ ሕጉና ወደ ምሥክሩ ስንል ፣ ጊዜ ወስዶ መጽሐፍቅዱስን ከሚያስጠኑና ከሚያስተምሩ ሰዎች በአግባቡ መማር ፣ በመጽሐፍቅዱስ ጥናቶች ሳይቀር ታማኝ ተማሪ መሆንን ያጠቃልላል :: 3ኛ ) ስንጠራው እግዚአብሔር የሚመልስልን አምላክ ነውና ፣ ነይ ነይ እምዬ ማርያም ከማለት ይልቅ እግዚአብሔርን መጣራት ዳግም ለተወለደ ለማንኛውም ክርስቲያን ድልን የሚያጎናጽፈው ነው በማለት የዛሬው ትምህርት በዚሁ ይደመደማል :: እነዚህ ጥቅሶች ለመጨረሻውና ለ3ኛው ቊጥር ማጠቃለያንና መደምደምያን የሚሰጡ ቊልፍ ሃሳቦች ስለሆኑ መጽሐፍቅዱሳችሁን በመግለጥ ጥቅሶቹን አንብቡአቸው ተባረኩ መዝሙር ( 91 ) : 15 እና 16 ፤ 2ኛ ሳሙኤል 22 ፥ 4 - ፍጻሜ ፤ 1ኛ ነገሥት 18 ፥ 20 _ 46 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 6 ፥ 9 ፤የማቴዎስ ወንጌል 7 ፥ 7 _ 12 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 6 ፣ 14 ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Tuesday 28 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 8 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፤ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ  5 : 10 - 12 ፋሲካን የሚያከብር ሰው ከፍርድ ያመለጠ ነው :: ታድያ እሥራኤላውያን ከአንድ ዓመት በኋላ በሲና ተራራ ላይ ፋሲካን ከማክበራቸው በፊት በእግዚአብሔር ላይ አምጸው ስለነበረ ተቀጡ ዘኊልቊ 14 : 21 - 23 ፤ 29 _ 35 :: ይሁን እንጂ ከፍርድና ከኩነኔ ያመለጠ ሰው ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ነው መኖር ያለበት :: ነገር ግን እሥራኤል ለእግዚአብሔር የታዘዙ ባለመሆናቸው በህይወታቸው ይሄ ሆነ :: ይህንን እውነታ ነበር አዲሱ ትውልድ በኢያሪኮ የፋሲካን በዓል ባከበረ ጊዜ ያልተገነዘበው :: ከዚህ የተነሳ ይህ አዲሱ ትውልድ ለሦስተኛ ጊዜ ፋሲካን በኢያሪኮ ሜዳ ያክብር እንጂ ለዚህ ለፋሲካው በዓል አከባበር በሕይወቱ ላይ ትርጉም መስጠት አቅቶት ነበር :: ፋሲካውንም በኢያሪኮ ሲያደርግ እንዲሁ በባህልና በቅብብሎሽ ላለመተው ሲል ብቻ አክብሮት አሳለፈው :: ይህ እንግዲህ የአዲሱ ትውልድ በራሱ ላይ ካለመጠየቅ ያመጣው የሕይወት ድክመት ነው :: ጠይቆ ቢሆን ኖሮ እውነታው ላይ በእርግጠኝነት ይደርስ ነበር :: በፋሲካ ምክንያት ከፍርድ ያመለጠ የመጀመርያውና ከግብጽም የወጣው የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ወደሚኖርበት ሕይወት መጥቶ ነበር :: ይሁን እንጂ በኢሳይያስ 1 ፥ 2 ላይ ልጆችን ወለድኩ አሳደግሁም እነርሱም አመጹብኝ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ፣ በእግዚአብሔር ላይ በማመጹ ምክንያት በምድረ በዳ ቀረ :: ጌታ እግዚአብሔር ከአመጽ ይጠብቀን :: በመሆኑም ለእግዚአብሔር ልጆች የሚበጀው መታዘዝ እንጂ ዓመጽ አይደለም :: መጽሐፍቅዱስ ትእዛዙን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና ትእዛዛቱ ከባባዶች አይደሉም ይለናል :: በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ስንሆን ትእዛዛቱን እንጠብቃለን :: ትእዛዛቱን በመጠበቅ ውስጥ እግዚአብሔር ሕይወታችንና የዘመናችንም ርዝመት ይሆናል :: እንደገናም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ውስጥ እግዚአብሔር ይወደናል ፣ ራሱንም ይገልጥልናል :: ስለዚህ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ደግሞ ትእዛዛቱ በእኛ ውስጥ ሊሆኑ ይገባል :: የዛሬው ትምህርት በአጭሩ የሚያስገነዝበን እንግዲህ ይህንን እውነት ነው :: ለተጨማሪ መረጃ የተለቀቀውን ቪዲዮ ይመልከቱ :: ፋሲካን አስመልክቶ ከቊጥር 1 _ 8 የተሰጡ ትምህርቶች በዛሬው የመጨረሻና የማጠቃለያ መልዕክት ተጠናቋል :: ሐሙስ ዕለት ዋናው የትምህርት አርዕስቴ እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ ንዑስ ክፍልና የትምህርት ሃሳብ እቀርባለሁ:: ልባችሁን አዘጋጅታችሁና ሰፋ ብላችሁ በሰዓታችሁ ተገኙ ተባረኩልኝ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Sunday 26 August 2018

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ.. የንስሓ አባት መሆን ያለበት ማን ነው ? የመልዕክት ርዕስ የንስሐ አባት ኢየሱስ ወይስ ኦርቶዶክሳዊው ቄስ ? የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን አላችሁ :: የንስሐ አባቱ ኢየሱስ ወይስ የኦርቶዶክሱ ቄስ ? በሚል ርዕስ ዙርያ ያነሳናቸውን ነጥቦች እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ስናያቸው በጣም አስተማሪና ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችን የምናገኝባቸው ጉዳዮች ሆነው አግኝተናቸዋል :: በመጀመርያው የጥያቄ መወያያችን ላይ ቄሶች የኢየሱስን ሥልጣነ ክህነት ለምን ይጋፋሉ ? ስንል በመጠይቅ መልክ ያነሳነው ሃሳብ ለቀሳውስቱ ምቾት ባይሰጥና ቀሳውስቱንም ሥልጣኔ ተነካ ፣ መብቴ ተደፈረ እያስባለ የሚያነጫንጫቸው ፣ የሚያተክናቸውና የሚያደብናቸው መሆኑን ብናውቅም እየተጋፉት ያሉት ፣ የማይጋፉትን ፣ ሊጋፉት ቢያስቡም እንኳ ጨርሶ ሊጋፉት የማይችሉትን እና የማይሆንላቸውን ከዚህም ሌላ በመጋፋታቸው ብዛት በራሳቸው ተጎድተው ከጥቅም ውጪ የሚሆኑበትን እውነት በመንገር ፣ የኢየሱስን የክህነት ሥልጣን ከሚጋፉበት ዓመጽ ወጥተውና አቅማቸውንም አውቀው በጨዋ ደንብ አርፈው እንዲቀመጡ ለማስገንዘብና ለመምከር ነው :: የኢየሱስን ሥልጣን በተመለከተ በተለይም የዛሬዎቹ ቀሳውስት ከእውቀት ነጻ በመሆናቸው መጽሐፍ ቅዱሱን በአግባቡ ሊያነቡት ቀርቶ የራሳቸውን የእምነት መግለጫ እንኩዋ ለማንበብ ጊዜ የሌላቸው:: በመሆኑ የእምነት መግለጫው ምን እንደሚልና በውስጡም ምን እንደተጻፈ አያውቁትም :: ምናልባትም እነዚህን ቀሳውስት እንዲህ ያባከናቸው የዝክሩና የተዝካሩ የድግሱም ብዛት ይሆናል ብዬ ገምታለሁ :: ዛሬ ግን ይህንን እውነት እኔ ወንድማቸው ላነቃቸውና ከተሳሳተው ተግባራቸውም ልመልሳቸው እናገረዋለሁ :: አመክንዮ ዘሐዋርያት የእምነት መግለጫ እንዲህ ይላል «ዘኪያሁ ይሴፈዉ ምጽአቶ ኲሎሙ አሕዛብ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሠረፀ እምይሁዳ ወእምሥርወ ዕሤይ ዘሥልጣኑ ዲበ መትከፍቱ ሎቱ ስብሐት ወአኰቴት ዕበይ ወባርኮት ውዳሴ ወማኅሌት ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን »ይህንን ወደ አማርኛው ስንተረጉመው «አሕዛብ ሁሉ መምጣቱን በተስፋ የሚጠባበቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ ከዕሤይም ሥር የተገኘ ሥልጣኑ በትከሻው ላይ የሆነ ነው ለእርሱ ምስጋና ገናንነት ክብር በረከት ውዳሴ ቃለ መዝሙርም ይገባዋል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን » ይለናል ::ከዚህ እንቊ ከሆነ እና መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት ሆኖም ከተጻፈ የቤተክርስቲያኒቱ የእምነት መግለጫ ተነስተን ነው እንግዲህ እኔና አባታችን አባ ተክለ ማርያም የኦርቶዶክስ ቄስ ሆይ ሕዝቤን ልቀቅ ይልሃል !!እግዚአብሔር ያልነው የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስን አይደለም ኦርቶዶክሳውያን አማኞች አሕዛብ ሳይቀር መምጣቱን በተስፋ የሚጠባበቁት ናቸው :: የመጣው ደግሞ ከሥልጣን ጋር ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ ከሤይም ሥር የተገኘ ሥልጣኑ በትከሻው ላይ የሆነ ነው ለእርሱ ምስጋና ገናንነት ክብር በረከት ውዳሴ ቃለ መዝሙርም ይገባዋል ሲል የእምነት መግለጫችን ነገረን:: ታድያ ይሄ ኢየሱስ ምስጋናና ገናናነት ሲባል ዝም ብሎ የተዘመረለት ጌታ እኮ አይደለም :: በሥልጣኑ የሠራው ትልቅ የማዳን ሥራ ስላለ ነው ውዳሴ ፣ ቃለ መዝሙርም ይገባሃል የተባለው :: በመሆኑም በሥልጣኑ ካደረገው የማዳን ሥራ አንጻር ዛሬ አይሁድ እንደሚገዘሩት እኛም እንደ አይሁድ አንገዘርም :: ለዚህም ነው ይኸው የእምነት መግለጫ ኢንትገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ ያለን :: ትርጉሙም እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን ማለት ነው :: አያ ቄሱ ግን ኦርቶዶክሳውያኑ ሥልጣኑ በትከሻው ላይ ሆኖ ነፍሳቸውን ለማዳን የመጣላቸውን ኢየሱስን ብቻ ተስፋ እንዳያደርጉ ፣ ይሄ ኢየሱስ ኦሪትና ነቢያትን እንዳልፈጸማቸው አድርጎ በመቁጠር ፣ ወደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት ተመልሶና የብሉይ ኪዳኑ የፍርባው ብዛትም ሆነ ተረፈ መስዋዕቱ ፊቱ ድቅን እያለበት ፣ ሽታውም ናላውን እያዞረው ፣ ውልም እያለው ስለተቸገረ ፣ ይህቺ ሁኔታ ደግሞ ለምዕመኑ ሳይቀር ምስጢር ሆና ለእርሱ ግን ትልቅ ጥቅም የምታስገኘው ፍርምባና ተረፈ መስዋዕት እንዳትቀርበት ፣ ኢየሱስ ሥልጣኔን እባክህ ተጋራኝ ወይንም አግዘኝ ያለው ይመስል ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ ከኢየሱስ ትከሻ ላይ ሥልጣኑን ሊያወርድ ሲጣጣር የኢየሱስንም ሥልጣን ሲጋፋ ይታያል :: ይህ ታድያ አንዳንድ ጩሉሌ የመርካቶ ኪስ አውላቂዎች በርቀት ሆነው በአንድ ሰው ላይ የሆነ ነገር ካዩ ፣ ጋሽዬ ይሄን ነገር እኮ እኔ ብይዘው ፣ ብረዳዎት እንደሚሉት ፣ ከቻሉም ደግሞ እንደ ጭልፊት ነጥቀው ለመብረር እንደሚጣደፉት ዓይነት በመሆኑ ፣ በኢየሱስ የክህነት ሥራም ላይ ያያቄሱ ድርጊት ከዚህ አይተናነስም እና እንዲሁ ነው :: እዚህ ላይ ለትምህርቴ ማጠናከርያ አንድ ምሳሌ በማከል መልዕክቴን እጠቀልላለሁ :: በአንድ መንደር ውስጥ ሕዝቡ የቅዳሜ ገበያ ሲል ከቤቱ እንደሚወጣ ያወቀች እብድ ማንም ሳይቀድማት በጠዋት ተነስታ « ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል አለች »አሉ :: መንደረተኛውም የዚህችን ዕብድ ብርቱ ማስጠንቀቅያ አላወቀም ፣ አልገባውምና ጀመራት ደግሞ ይህቺ ዕብድ ፣ ዛሬ ደግሞ ምኑን ከምን ይዛ ነው እንዲህ የሚያስለፈልፋት ? ብሎ ይህቺን ዕብድ ማንም ሰው አባከና ሳይላትና ቦታም ሳይሰጣት ሁሉም ወደ ገበያው ጥርግ ብሎ ሄደ :: ከዚያም መንገዱን እያጋመሰው እያለ ዕብዷ ሴት የእያንዳንዱን ሠፈረተኛ ሰው ቤት በእሳት ለኮሰችና እሳቱ ሲንቦገቦግና ቤታቸውን ሲያቃጥል ሠፈረተኛው ወየው ቤታችን ተቃጠለ ጉድ ሆንን ብሎና ከመንገዱም ተመልሶ ወደ ሠፈሩ ሲመለስ ይህቺ ዕብድ ጠዋት ማንም ከእንቅልፉ ሳይነሳ ትናገረው የነበረውን ቃል በመድገም «ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል » አለቻቸው ይባላል :: መልዕክቴን ስጠቀልለው እኔም ሆንኩ አባታችን አባ ተክለ ማርያም የምናስተላልፈው መልዕክት ዛሬም ይህንኑ ቃል በመድገም ነው «ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል » ተባረኩ እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ ፤ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች  5 : 13 - 15 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዘእንበለ ወላዲቱ ድንግል ወዘእንበለ መስቀሉ ክቡር አሜን

Thursday 16 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ  እግዚአብሔርን የተኩ  የአማልክት አምልኮዎች 

ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 5 )


ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ 
ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ


ትርጉም  የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 )


5ኛ ) ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት ( ዘኊልቊ 9  12 ) 











ወንድማችን የጥንቱና የጠዋቱ መጋቢና ዘማሪ ታምራት ኃይሌ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው :: በመዝሙሮቹ ውስጥ ያሉት መልዕክቶች መጽሐፍቅዱሳዊና ከመንፈስ ቅዱስ የተገኙ ከመሆናቸው የተነሳ ዘመናትን አቋርጠው አሁን ላይም እየተደመጡ ያሉ በመሆናቸው ትውልድን የሚመሠርቱ የሚያንጹና አቅጣጫንም ጭምር የሚያስይዙ መዝሙሮች ናቸው :: ታድያ እነዚሁ መዝሙሮች  መዝሙር ብቻ ሳይሆኑ   ስብከቶች መልዕክቶችና ትምህርቶችም ጭምር ናቸው :: በመሆኑም ዛሬ ላይ ባዘጋጀሁት ትምህርትም የወንድማችን መጋቢና ዘማሪ ታምራት ኃይሌ መዝሙር በእጅጉ የጠቀመኝ በመሆኑ ከትምህርቴ ጋር አያይዤ ይህን መዝሙር ለእናንተ ለአድማጮች ለመጋበዝ ወድጃለሁ እና እባካችሁ ተጋበዙልኝ ስል በፍቅር እጠይቃለሁ:: ወንድማችንንም ጌታ ይባርክህ ዕድሜና የአገልግሎት ዘመንም አብዝቶ አትረፍርፎ ይጨምርልህ በሉልኝ ተባረኩ 








በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ እግዚአብሔርን የተኩ የአማልክት አምልኮዎች 

( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 5 )


ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ 
ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ


ትርጉም የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 )


5ኛ ) ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት ( ዘኊልቊ 9 12 ) 


የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ በዘኊልቊ 9 12 ላይ የተጻፈው የብሉይ ኪዳን ቃል በጥላነት የሚያመለክተን የፋሲካ በጋችን የሆነውን ኢየሱስን ነው ( የዮሐንስ ወንጌል 1 29 )::  ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም ይለናል  ( 1 ቆሮንቶስ 5 7 እና 8 ) ::

እንደገናም በዘኊልቊ 9 12 መሠረት ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ :: ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ:: እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት የሚለው ቃል በዮሐንስ ወንጌል 19 36 እና 37 ለተጻፈው ቃል አሁንም በጥላነት የሚያገለግል ነው :: ቃሉም እንዲህ ይላል :: ይህ የሆነ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው :: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ የወጉትን ያዩታል ይለናል :: ይህ የሚያሳየን ታድያ ጌታ እኛን ከመውደዱና ለእኛም መሥዋዕት በመሆኑ  ምክንያት በኤፌሶን 5 2 ላይ በተጻፈው ቃል መሠረት ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ በፍቅር ተመላለሱ የሚለውን ቃል ያስጨብጠናል ::  ታድያ ክርስቶስ እኛን በመውደዱ ምክንያት ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ምልልሳችንን ሳይቀር ለውጦ የፍቅር ምልልስ አደረገው :: ከዚህም ሌላ እኛም እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ ተብለናልና በእግዚአብሔር በአምላካችን እንደተወደድን ገብቶን እግዚአብሔርን የምንከተል ሆንን :: ለዚህ ሁሉ ክብር የበቃንበት ምስጢር ግን  ክርስቶስ እኛን በመውደዱ ምክንያት ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ነው :: 

ሌላኛውና ሁለተኛው ሃሳብ አሁንም  በዘኊልቊ 9 12 በተጻፈው ሃሳብ መሠረት እስከ ነገ ድረስ ከእርሱ ምንም ካላስቀሩ ከእኛም ምንም መቅረት የለበትም የሚለውን ሃሳብ እንድንይዝ ቃሉ ያስገነዝበናል :: ይህ ማለት ደግሞ እኛም ፈጽመን ወይንም ጨርሰን መለወጥ እንዳለብን የሚጠቁመን ቃል ነው :: 

በዘጸአት 12 14 እና 15 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን :: ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤቶቻችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ።

እርሾን በተመለከተ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ እርሾ በመጽሐፉ ቃል መሠረት ያልተፈለገ በመሆኑ ለብሉይ ኪዳኑ እሥራኤል ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤቶቻችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ የሚል ትዕዛዝ ተላለፈ :: ይህንን እውነታ አሁንም ወደ ሐዲስኪዳኑ ሕይወት ስናመጣው ፣ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም የሚለውን እውነተኛውን ትምህርታዊ የሆነ የሕይወት መርሆና ትርጉምን ይሰጠናል :: ዛሬ ታድያ ክርስቶስን ባመኑ ፣ በሚያገለግሉም ክርስቲያኖችና አገልጋዮች ሳይቀር  ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶ ሳለ በእነዚሁ ወገኖች ሕይወት ላይ ግን   ክፉ የሆነ አሮጌ  የግፍ ፣ የቅንዓት የክፋትና የዓመጸኝነት…. እርሾ አለ :: እንደገናም በእውነትና በቅንነት ቂጣ በዓልን ማድረግ የለም :: 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ ፣ ደቀመዛሙርቱን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንዲጠበቁ አስጠነቀቀ ( የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 6 ፤ 12 ):: ለዚህም ነው ጳውሎስ በዘመናችን  ላለን  ጤናማ ክርስቲያኖች ጭምር መልዕክት ስለነበረው ፣ የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኛለሁና የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር ፍርዱን ሊሸከም ነው በማለት የነገረን ( ገላትያ 5 ፥ 9 ) ::

በክቡር በክርስቶስ ደም እንደ ተዋጀ ያወቀ ሰው በሕይወቱ እርሾ እንዲኖርበት አይፈቅድም ፣ መፍቀድም የለበትም ( ዘዳግም 16 ፥ 3 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 19 ) 

ከዚህ በመቀጠል ለዚህ ትምህርት ማጽኛ እንዲሆን ፣ ጌታ በሌሊት ከመኝታዬ ቀስቅሶ የተናገረኝን ቃል እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ ::


ለቤተክርስቲያንና ለቅዱሳን ዕድገት እንዲሁም የሕይወት ከፍታ አስቸጋሪ የሆኑ ፣ ለዘመናት አልለወጥ ብለው በቤቱ እንደ ጉቶ ተተክለው ለቀሩ ክርስቲያኖች ፣

1ኛ ) በግድ በመከራና በጣር እንደሚለወጡ ጌታ ይናገራል ( ዘፍጥረት 32 ፥ 22 _ ፍጻሜ ፤ ትንቢተ ኤርምያስ 31 ፥ 18 _ 20 )::

2ኛ ) በበቃኝ እና በልመለስ እንደሚለወጡም  ጌታ ይናገራል ( የሉቃስ ወንጌል 15 ፥ 11 _ ፍጻሜ ፤ ሰቆቃወ ኤርምያስ 5 በሙሉ )::

በመቀጠልም የተባረከው የጥንቱና የጠዋቱ ዘማሪ የሆነው መጋቢ ታምራት ኃይሌ ፦


በእንባና በጣር በጭንቅ በመከራ 

በእሳት ውስጥ አልፎ ሕይወቴ ተገራ 

ማዕበሉም ነፋሱም ሰራኝ ደህና አድርጎ 

ጠላት ለክፉ ሲል ሆነልኝ ለበጎ………. የሚለውን 

መዝሙር ከትምህርቴ ጋር ስለሚሄድ እርሱን በመጋበዝ 

የቊጥር 5 ትምህርቴን አጠቃልላለሁ ተባረኩ 





ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ 

አገልግሎት


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው


በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) (...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 5 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) 5ኛ ) ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት ( ዘኊልቊ 9 ፥ 12 ) የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ በዘኊልቊ 9 ፥ 12 ላይ የተጻፈው የብሉይ ኪዳን ቃል በጥላነት የሚያመለክተን የፋሲካ በጋችን የሆነውን ኢየሱስን ነው ( የዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 29 ):: ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም ይለናል ( 1ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 7 እና 8 ) :: እንደገናም በዘኊልቊ 9 ፥ 12 መሠረት ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ :: ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ:: እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት የሚለው ቃል በዮሐንስ ወንጌል 19 ፥ 36 እና 37 ለተጻፈው ቃል አሁንም በጥላነት የሚያገለግል ነው :: ቃሉም እንዲህ ይላል :: ይህ የሆነ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው :: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ የወጉትን ያዩታል ይለናል :: ይህ የሚያሳየን ታድያ ጌታ እኛን ከመውደዱና ለእኛም መሥዋዕት በመሆኑ ምክንያት በኤፌሶን 5 ፥ 2 ላይ በተጻፈው ቃል መሠረት ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ በፍቅር ተመላለሱ የሚለውን ቃል ያስጨብጠናል :: ታድያ ክርስቶስ እኛን በመውደዱ ምክንያት ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ምልልሳችንን ሳይቀር ለውጦ የፍቅር ምልልስ አደረገው :: ከዚህም ሌላ እኛም እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ ተብለናልና ፣ በእግዚአብሔር በአምላካችን እንደተወደድን ገብቶን ፣ እግዚአብሔርን የምንከተል ሆንን :: ለዚህ ሁሉ ክብር የበቃንበት ምስጢር ግን ክርስቶስ እኛን በመውደዱ ምክንያት ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ነው :: ሌላኛውና ሁለተኛው ሃሳብ አሁንም በዘኊልቊ 9 ፥ 12 በተጻፈው ሃሳብ መሠረት እስከ ነገ ድረስ ከእርሱ ምንም ካላስቀሩ ከእኛም ምንም መቅረት የለበትም የሚለውን ሃሳብ እንድንይዝ ቃሉ ያስገነዝበናል :: ይህ ማለት ደግሞ እኛም ፈጽመን ወይንም ጨርሰን መለወጥ እንዳለብን የሚጠቁመን ቃል ነው :: በዘጸአት 12 ፥ 14 እና 15 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን :: ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤቶቻችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ። እርሾን በተመለከተ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ እርሾ በመጽሐፉ ቃል መሠረት ያልተፈለገ በመሆኑ ለብሉይ ኪዳኑ እሥራኤል ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤቶቻችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ የሚል ትዕዛዝ ተላለፈ :: ይህንን እውነታ አሁንም ወደ ሐዲስኪዳኑ ሕይወት ስናመጣው ፣ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም የሚለውን እውነተኛውን ትምህርታዊ የሆነ የሕይወት መርሆና ትርጉምን ይሰጠናል :: ዛሬ ታድያ ክርስቶስን ባመኑ ፣ በሚያገለግሉም ክርስቲያኖችና አገልጋዮች ሳይቀር ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶ ሳለ በእነዚሁ ወገኖች ሕይወት ላይ ግን ክፉ የሆነ አሮጌ የግፍ ፣ የቅንዓት የክፋትና የዓመጸኝነት…. እርሾ አለ :: እንደገናም በእውነትና በቅንነት ቂጣ በዓልን ማድረግ የለም :: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ ፣ ደቀመዛሙርቱን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንዲጠበቁ አስጠነቀቀ ( የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 6 ፤ 12 ):: ለዚህም ነው ጳውሎስ በዘመናችን ላለን ጤናማ ክርስቲያኖች ጭምር መልዕክት ስለነበረው ፣ የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኛለሁና የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር ፍርዱን ሊሸከም ነው በማለት የነገረን ( ገላትያ 5 ፥ 9 ) :: በክቡር በክርስቶስ ደም እንደ ተዋጀ ያወቀ ሰው በሕይወቱ እርሾ እንዲኖርበት አይፈቅድም ፣ መፍቀድም የለበትም ( ዘዳግም 16 ፥ 3 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 19 ) ከዚህ በመቀጠል ለዚህ ትምህርት ማጽኛ እንዲሆን ፣ ጌታ በሌሊት ከመኝታዬ ቀስቅሶ የተናገረኝን ቃል እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ :: ለቤተክርስቲያንና ለቅዱሳን ዕድገት እንዲሁም የሕይወት ከፍታ አስቸጋሪ የሆኑ ፣ ለዘመናት አልለወጥ ብለው በቤቱ እንደ ጉቶ ተተክለው ለቀሩ ክርስቲያኖች ፣ 1ኛ ) በግድ በመከራና በጣር እንደሚለወጡ ጌታ ይናገራል ( ዘፍጥረት 32 ፥ 22 _ ፍጻሜ ፤ ትንቢተ ኤርምያስ 31 ፥ 18 _ 20 ):: 2ኛ ) በበቃኝ እና በልመለስ እንደሚለወጡም ጌታ ይናገራል ( የሉቃስ ወንጌል 15 ፥ 11 _ ፍጻሜ ፤ ሰቆቃወ ኤርምያስ 5 በሙሉ ):: በመቀጠልም የተባረከው የጥንቱና የጠዋቱ ዘማሪ የሆነው መጋቢ ታምራት ኃይሌ ፦ በእንባና በጣር በጭንቅ በመከራ በእሳት ውስጥ አልፎ ሕይወቴ ተገራ ማዕበሉም ነፋሱም ሰራኝ ደህና አድርጎ ጠላት ለክፉ ሲል ሆነልኝ ለበጎ………. የሚለውን መዝሙር ከትምህርቴ ጋር ስለሚሄድ እርሱን በመጋበዝ የቊጥር 5 ትምህርቴን አጠቃልላለሁ ተባረኩ ወንድማችን የጥንቱና የጠዋቱ መጋቢና ዘማሪ ታምራት ኃይሌ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው :: በመዝሙሮቹ ውስጥ ያሉት መልዕክቶች መጽሐፍቅዱሳዊና ከመንፈስ ቅዱስ የተገኙ ከመሆናቸው የተነሳ ዘመናትን አቋርጠው አሁን ላይም እየተደመጡ ያሉ በመሆናቸው ትውልድን የሚመሠርቱ የሚያንጹና አቅጣጫንም ጭምር የሚያስይዙ መዝሙሮች ናቸው :: ታድያ እነዚሁ መዝሙሮች መዝሙር ብቻ ሳይሆኑ ስብከቶች መልዕክቶችና ትምህርቶችም ጭምር ናቸው :: በመሆኑም ዛሬ ላይ ባዘጋጀሁት ትምህርትም የወንድማችን መጋቢና ዘማሪ ታምራት ኃይሌ መዝሙር በእጅጉ የጠቀመኝ በመሆኑ ከትምህርቴ ጋር አያይዤ ይህን መዝሙር ለእናንተ ለአድማጮች ለመጋበዝ ወድጃለሁ እና እባካችሁ ተጋበዙልኝ ስል በፍቅር እጠይቃለሁ:: ወንድማችንንም ጌታ ይባርክህ ዕድሜና የአገልግሎት ዘመንም አብዝቶ አትረፍርፎ ይጨምርልህ በሉልኝ ተባረኩ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Monday 13 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 4 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) 4ኛ ) እሥራኤል ያደረጉት ፋሲካ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው ሙሴም ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ተናገራቸው በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ ይለናል ( ዘኍልቍ 9 ፥ 4 እና 5 ) የመጀመርያው ፋሲካ የተደረገው በግብጽ ነበር ( ዘጸአት ምዕራፍ 12 ን በሙሉ ተመልከቱ ) ውጤቱ ፦ 1ኛ ) የእሥራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ አደረጉ እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ :: በዚያም ቀን እግዚአብሔር የእሥራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብጽ ምድር አወጣ የሚል ነው ( ዘጸአት 12 ፥ 50 እና 51 እንመልከት ) 2ኛ ) በመጀመርያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእሥራኤል ልጆች ግብጻውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለ እጅ ወጡ :: በዚያም ጊዜ ግብጻውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኩሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው ይለናል ( ዘኊልቊ 9 ፥ 3 እና 4 ) ፋሲካ ታድያ እንዲሁ ዝም ተብሎ ፣ ወርና ዓመት ተቆጥሮ የሚደረግ አይደለም :: ወራትንና ዓመታትን ቆጥረን ዘመናትንም ቀምረን የምናደርገውን ፋሲካ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ካላደረግነው በሕይወታችን ላይ ለውጥንና መሻገርንም የሚያመጣ አይሆንም :: የባሕል ፋሲካ ብቻ ሆኖ ይቀርና እኛም ዕለታዊ ሳይሆን ዓመታዊ ኑዛዜዎችን የለመድን ስለሆንን ፣ ከአልጋ ወድቄያለሁና የመሣሠሉትን ኑዛዜዎች ለነፍስ አባት ተብዬዎች ለይስሙላ ያህል እየተናዘዝን ፣ ለዚህም ማካካሻ ቅጣት የሚሆነንን ጥብጣቤ ስንል ጀርባችንን በወይራ ተቸብችበንና ተጠብጥበን አርባ ፣ ሰማንያ ፣ መቶና ከዚያ በላይ እየሰገድን ፣ ከዚያም መልስ ወደ ቤታችን ሄደን በቤታችን የተዘጋጀውን ጉልባን እየሰለቀጥን ፣ ከዚህም ሌላ ትንሣኤ ላይ ደረስን ስንል ደግሞ ዶሮአችንን ፣ ክትፎአችንንና ግብዣችንን ከምናሳድድ ውጪ ሌላ ነገር አናውቅምና በሕይወታችን የሚታይብን ለውጥ የለም :: በዚህ ውስጥ ግን ኢየሱስ በእኛ ጥብጣቤና ስግደት የሚገለጽ ባሕላዊ ፋሲካችን ስላልሆነ ለእኛ ለሁላችን በደል በብረት ጅራፍ ተገርፎ ደማልን:: አልፎም በመስቀል ላይ በመሞት ደሙ እንደ ጅረት ፈሶ የኃጢአትን ሥርየት ሰጠን :: ከዚህም ሌላ ኢየሱስ ሞቶ አልቀረም ፣ ለአንቀላፉት ሁሉ በኩራት ሆኖ ከሙታን በመነሳት እኛን ያመንበትን አጸደቀን ( ሮሜ 4 ፥ 24 እና 25 ) ከዚህ የተነሣ ፋሲካ ዛሬ ለእኛ ባሕላዊ አይደለም :: ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ሙሴ በግብጽ በተደረገው የመጀመርያው ፋሲካ ላይ አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨት በእምነት አደረገ የሚለን:: ስለዚህ ሙሴ በጊዜው ያደረገው ፋሲካ ባሕላዊ የወይራ መቸብቸብና ጥብጣቤ ያለበት ፣ ጉልባን የተበላበት ፣ ከዚያም መልስ እንኳን አደረሳችሁ እየተባለ በየትያትር ቤቱ ሳይቀር ኮንሰርት ተዘጋጅቶ እስክስታና ጭፈራ ስካርና ዳንኪራ የተካሄደበት ፋሲካ አልነበረም :: ሙሴ ባደረገው ፋሲካ ውስጥ ደም መርጨት ስለነበረ አጥፊው የበኩሮችን ልጆች አልነካም ( ዕብራውያን 11 ፥ 23 _ 30 ) :: ይህንን ሃሳብ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስናመጣው በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች ፥ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል የሚለን ለዚህ ነው ዕብራውያን 12 ፥ 22 _ 24 በመሆኑም እኛ የሐዲስ ኪዳን አማኞች ዛሬ ላይ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሰናል ይሁን እንጂ ከዚያም መልስ በሙሴ የደም መርጨት ዘመን የታየውን ውጤት ስንመለከተው የእሥራኤል ልጆች ግብጻውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለ እጅ ወጡ :: በዚያም ጊዜ ግብጻውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኩሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን :: በመሆኑም ዛሬም ላይ ፋሲካ ይህንን ቃል በሰማነው ሰዎች ሕይወት ላይ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሆኖና ተደርጎ እንዲህ ዓይነቱን ለውጥ ካላመጣ ( ራዕይ 12 ፥ 7 _ 12 ) ፣ እኛንም አሻግሮ ወደምንናፍቃት ጽዮንና አዕላፋት የበኩራት ማኅበር ካላደረሰን ( ዕብራውያን 12 ፥ 18 _ 24 ) ፋሲካው አሁንም ባሕላዊ ነው ሁለተኛው ፋሲካ የተከበረው ከአንድ ዓመት በኋላ በሲና ነበረ በእስራኤል አለመታዘዝና እግዚአብሔር በእርስዋ ላይ በወሰነው ፍርድ ምክንያት እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር እስከምትገባ ድረስ ፋሲካን አላከበረችም ( ዘኊልቊ ምዕራፍ 14 ን በሙሉ እንመልከት ) ስለዚህ አሁንም የእኛ ፋሲካ በቃሉ መሠረት የተደረገና በተስፋ ቃል የሆነ ነውና ከእኛነታችን አልፎ ሌሎችንም የሚወርስ ነው :: ስለዚህ ለዚህ ጉዳይ እኛ ሁላችን ክርስቲያኖች ልንነሳና ውስጣችንንም በዚህ በተሰጠው የተስፋ ቃል ልናጸና ፣ የተናገረንንም የተስፋ ቃል እስከመጨረሻው በማመን አጽንተን ልንይዝ ይገባል:: የተወደዳችሁሁ ወገኖች ትምህርቱ በዚህ ያልተቋጨ በመሆኑ በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜያችን ቁጥር 5 ብለን እንቀጥላለን ተባረኩ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Friday 10 August 2018

በአባቶች እግር ሥር ተቀምጠው ሳይማሩ ፣ የቤተክርስቲያኒቱንም መሠረታዊ ትምህርት ሳያውቁ ለሚያሳስቱ ሐሰተኛ አ...

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 3 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) 3ኛ ) ፋሲካ መታረድ ያለበት ነው ( ዘጸአት 12 ፥ 21 ) የተወደዳችሁ ወገኖች በዚህ የቊጥር 3 ትምህርት ፋሲካ መታረድ ያለበት በዓል እንደሆነና ፋሲካ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የቂጣ በዓልን ጨምሮ ሰባት ቀን ሙሉ የሚቆየውን በዓል እንደሆነ ፣ ብዛት ያላቸው የፋሲካ ማዕዶችም በዚህ ወቅት እንደሚቀርቡ ትምህርቱ ይጠቁማል :: በብሉይ ኪዳኑ ዘመን ካህናቱ ፣ ሌዋውያኑም አንድ ሆነው ነጽተው ነበር :: ሁሉም ንጹሐን ነበሩ :: ለምርኮኞቹም ሁሉ ፣ ለወንድሞቻቸውም ፣ ለካህናቱ ለራሳቸውም ፋሲካውን አረዱ ይለናል ( መጽሐፈ ዕዝራ 6 ፥ 20 ) :: በመሆኑም ፋሲካ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ሁሉንም የሚመለከት ነው :: ፋሲካ የማይመለከተው ሰው ማንም የለም :: ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ወደ አማርኛው ስተረጉመው የአዳም ፋሲካው ማርያም ፣ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋንም መሻገርያዋ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ሲል የሰዓታት መጽሐፍ በመሳሳት የተናገረ ቢሆንም ፣ ፋሲካችን ግን ክርስቶስ ስለሆነ መጽሐፍቅዱሳችን በነገረን ቃል መሠረት ለማርያምም ጭምር የሚያስፈልግ ነው :: ታድያ በዕዝራ መጽሐፍ እና በሌሎችም በተጠቀሰው ቃል መሠረት በሐዲስ ኪዳን የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ከፋሲካ በፊት ከሀገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ ይለናል ( ዮሐንስ ወንጌል 11 ፥ 15 ) :: እንደገናም ደግሞ በዮሐንስ ወንጌል 18 ፥ 28 ላይ ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት ማለዳ ነበረ እነርሱም የፋሲካን በግ ይበሉ ዘንድ እንጂ እንዳይረክሱ ወደ ገዢው ግቢ አልገቡም ይለናል :: ታድያ እነዚህ ካህናት ፋሲካን በንጽሕና ያደረጉ መስለው ገዢው ከአሕዛብ ወገን በመሆኑና እነርሱም እሕዛብን የተጸየፉ ሆነው ከዚሁ ከፋሲካቸው የተነሳ ወደ ገዢው ግቢ ባለመግባታቸው ያልረከሱ ቢመስላቸውም ፣ በማርቆስ ወንጌል 15 ፥ 1 መሠረት ማለዳ ነበርና የካህናት አለቆች ለሠሩት ሥራ የሕግ ሽፋን ለመስጠት ሲሉ ለሁለተኛ ጊዜ በማለዳ የሸንጎ ስብሰባ አድርገዋል :: ኢየሱስንም አስረው በመውሰድ ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጥተውታል ስለዚህ የፋሲካን በግ ይበሉ ዘንድ እንጂ እንዳይረክሱ ወደ ገዢው ግቢ ያልገቡ ናቸው ስለተባሉ ብቻ የነጹ ናቸው ማለት አንችልም :: እነርሱ የረከሱት ገና መጀመርያ ላይ ሕጋቸውን ሽፋን አድርገው በደል የሌለበትንና ንጹሕ የሆነውን ጌታ ለሁለተኛ ጊዜ በማለዳ የሸንጎ ስብሰባቸው ላይ አሳልፈው ሊሰጡ በዶለቱ ጊዜ ነው :: በመሆንም ሕግንና በዓልን መደበቅያ ሽፋን አድርጎ ሲዶልት የነበረን ሰው የነጻ ነው ማለት ሌላውን ሳይሆን እራስን በራስ እንደማታለል የሚያስቆጥር ነገር ነው :: ዛሬም ታድያ ይህንን ሽፋን አሁን ላይ ወዳለች ቤተክርስቲያን ስናመጣው ፣ ይሄ ሁኔታ በተለይም በአብዛኛው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ያላዋቂ ሳይሆን የአዋቂ አጥፊነት አለና ይሄ ጉዳይ ምንም ሳይሸፈን ይፋ ሆኖ እየታየ ያለ ደግሞም በፍጥነት ሊስተካከል የሚገባው ጉልህ ስሕተት ሆኖ አግኝቼዋለሁ :: በቪዲዮው የትምህርት መልዕክቴ ላይ እንደዘረዘርኩትም ዛሬ ላይ ጥቅስን ፣ ኮንፍረንሶችንና ልዩ ልዩ ዓመታዊ የመነቃቅያ ፕሮግራሞቻችንን ሽፋን በማድረግ ከዚህ በተጨማሪም የጌታን እራትና ልዩ ልዩ የእርስ በእርስ መገባበዝንም ጨምሮ ያለው ፕሮግራማችን በአብዛኛው ልባዊ ያልሆነና እንዲሁ ሥርዓት በመፈጸም ብቻ ክርስቲያን የሚለውን ስም ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ሲባል የሚደረግ ለውጥ የሌለበት ፣ ማስመሰልም የታከለበት ውጫዊ እንቅስቃሴ መሆኑ ለሁሉም ሰው ግልጽ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው :: ከዚህ የተነሳ እንግዲህ በውጪ ባሉት ሰዎች ዘንድ ያለን ምስክርነት እየተበላሽ በመምጣቱ ምክንያት ፣ በአካባቢያችንና በዙርያችን ባሉት ሰዎች ዘንድ ሞገስን አላገኘንም :: ጌታም የሚድኑትን ነፍሳት በላያችን አልጨመረም :: ይህ እንግዲህ ትልቁና ዋነኛው የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት አማኞችና አገልጋዮች ችግር ነው :: ለዚህ አስከፊ ጉዳይ የሚባለው እንግዲህ ከዚህ ዓይነቱ ነቀፋ እግዚአብሔር ያውጣን ነው :: በዚህ ውስጥ ግን አሻግረን የታረደልንን በግ ስናይ የታረደው በግ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሥልጣን የጨበጠው በሞቱ ነው :: በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ኖሯቸው ወደ ምድር ሁሉ በተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ድል ነሺ ሆኖ የተገለጠ በመሆኑ እንደታረደ በግ ቆሞ የታየ ነው :: በዚህም ምክንያት መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ ይለናል ራዕይ 5 ፥ 6 _ 11 :: ከዚህም ሌላ በራዕይ 17 ፥ 14 ላይ ይኸው ጌታ ድል ነሺ እና አሸናፊ መሆኑን ሊያጠናክርልን ፣ እነዚህ በጉን ይወጋሉ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ እነርሱን ድል ይነሣል :: ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሳሉ ይለናል :: የምናነበውን ቃል እግዚአብሔር ይባርክልን ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

Tuesday 7 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል አምስት ) ( ቊጥር 2 ) ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ትርጉም ፦ የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ ( መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 79 ) 2ኛ ) ፋሲካ መታረድ ያለበት ነው ( ዘጸአት 12 ፥ 21 ) በመሆኑም ታድያ ድንግል ማርያም የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲ በተናገረው ቃል መሠረት በግዕዙ ቃል ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ ብሎአልና ወደ አማርኛው ሲተረጎም የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ከጎኑም ለወጣችዋ ለሔዋን መሻገርያዋ የሆንሽ ማርያም ደስ ይበልሽ የሚል በመሆኑ ከተጻፈልን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር ስናነጻጽረው የኢየሱስ እናት ማርያም የእስራኤል ጠቦት ሆና ጠቦት የሆነችዋን ማርያምን ምረጡ ወስዳችሁም ለፋሲካ እረዱዋት በማለት የብሉይ ኪዳንም ሆነ የሐዲስኪዳን ፋሲካችሁ እናታችሁ ማርያም ናት አላለንም በመሆኑም ለአዳምና ለሔዋንም ሆነ ለሰው ልጆች ሁሉ ለራስዋ ለማርያምም ጭምር ፋሲካዋ ሆኖ በሸላቾቹ ፊት ሳይቀር ዝም እንደሚል በግ የታረደልን ጠቦታችን የሆነው የናዝሬቱ ኢየሱስ ብቻ ነው ከዚህ በመቀጠል ለትምህርታችን እንደ መንደርደርያ የሆኑትን ዋና ዋና ነጥቦች ፣ ለአማናዊው በግ ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደጥላ ሆነው ያገለገሉትን ፣ ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ የቀረቡትን መሥዋዕቶች ከመሥዋዕታችን ከኢየሱስ ጋር በንጽጽር እያቀረብን ደረጃ በደረጃ እናያቸዋለን ሀ ) የሚታረደው ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ሲሆን ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ ይለናል ( ዘጸአት 12 ፥ 5 ፣ ዘሌዋውያን 4 ፥ 32 ) ለ ) ይህ ነውር የሌለበት ጠቦት ደግሞ በሐዲስኪዳን በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም የተዋጀንበት እውነት ነው ( 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 18 _ 19 ) ሐ ) ለቁርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በእግዚአብሔር ፉት ያቀርበዋል ይለናል ( ኦሪት ዘሌዋውያን 3 ፥ 7 ) መ ) ይህም በሐዲስ ኪዳን ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመጸኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት የሞተልን እርሱ ክርስቶስ ነው ( 1ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 18 _ 22 ) ሠ) በብሉይ ኪዳን ዘመን የቀረበው ይህ አንዱ ጠቦት ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት ተለውሶ የኢፍ መስፈርያ አስረኛ እጅ መልካም ዱቄት ጋር ለመጠጥ ቁርባን ይሆናል ይህንን ነው እንግዲህ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽቱ እንዲሆን የእሳት ቁርባን ይሆናል የሚለን ( ዘጸአት 20 ፥ 40 እና 41 ፤ ዘኊልቊ 28 ፥ 8 ) ረ ) ይህንን እውነታ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስናመጣው ክርስቶስ ለእግዚአብሔር የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ስለ እያንዳንዳችን ራሱን አሳልፎ የሰጠበትን ሕይወት እናይበታለን ( ኤፌሶን 5 ፥ 1 _ 3 ፤ ፊልጵስዩስ 4 ፥ 18 ) ሰ ) ይሄ የታረደው ጠቦት ስቡ ሁሉ ሳይቀር የሚቀርብ ስለሆነ ለደኅንነት መሥዋዕት የሚቀርብና ካህኑም ለእግዚአብሔር በእሳት በተቃጠለው ቁርባን በመሰውያው ላይ የሚያቃጥለው ፣ ካህኑም ስለተሠራው ኃጢአት የሚያስተሠርየውና እርሱም አብሮ ይቅር የሚባልበት ነው ( ዘሌዋውያን 4 ፥ 35 ፣ ዘሌዋውያን 4 ፥ 26 ) ሸ ) ይኸው ጠቦት አውራ ፍየልም ይሁን አውራ በግና በሬ በዘይት ከተለወሰው የእህል ቁርባን ጋር ለኃጢአት መሥዋዕት ሊሆን በእግዚአብሔር ፊት ይሰዋ ዘንድ የሚቀርብ ነው ( ዘሌዋውያን 9 ፥ 3 _ 4 ) ቀ ) ይሁን እንጂ እነዚህ በብሉይ ኪዳን ዘመን የቀረቡ የጥጆች የፍየሎችና የኮርማዎች ደም በረከሱት ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ብቻ ናቸው ነገር ግን ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ከዚህ ከብሉይ ኪዳኑ መስዋዕቶች ይልቅ በተለየ ሁኔታ ሕያው እግዚአብሔርን ልናመልክ ከሞተ ሥራ ሕሊናችንን ነጻ የሚያደርግ ነው ( ዕብራውያን 9 ፥ 13 እና 14 ) በ ) እንደገናም ሊቀካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መስዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪያደርግ ድረስ ወደፊት ይጠብቃል አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋል ይለናል ( ዕብራውያን 10 ፥ 11 _ 18 ) ተ ) ከዚህም ሌላ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለተጠራ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው ይለናል ( ዕብራውያን 7 ፥ 7 _ 10 ) ቸ ) ተጨነቀ ተሰቃየ አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም በማለት የሐዲስ ኪዳኑ ጠቦታችን የታረደው በግ የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደሆነ ይናገራል ( ኢሳይያስ 53 ፥ 7 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 29 ፤ የሐዋርያት ሥራ 8 ፥ 32 ) ጌታ እግዚአብሔር የምናነበውን ይህንን ጽሑፍም ሆነ የተለቀቀውን ቪዲዮ በማስተዋል ሰምተን እንድንጠቀም ይርዳን ተባረኩ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው